የወያኔ
ፈሊጥ!!!
የወያኔ ፈሊጥ
ያልቦካ የሚኮመጥጥ
ያልተገራ
የሚጎረብጥ
ያልላመ የሚንቀረጨጭ
ያልጎመራ
ፍሬ የማይሰጥ
ሱሪ ባንገቴ
ረብ የለሽ
ቀኖናዊ ፍልስፍና
ወጥ ያልሆነ
ድሪቶ አቢዮታዊ
አመንክዮ
አልባ ግብታዊ
ህዝባዊ ያልሆነ ቡድናዊ
ድንቄም ዲሞክራሲ
ከወረቀት
አልፎ መሬት የማይወርድ
የፕሮፓጋንዳ
ፍጆታ
ከፋፍለህ
ግዛ መርህ
ከአንድነት
በላይ ለልዩነት
የወያኔ መፈክራዊ
ስሌት
ቅሉ ቢሆንም
አንድነት ከነልዩነት
የአንድነት
ጠላት አንድነት አፍራሽ
ታሪክን ከላሽ
አርበኛ ከሳሽ
የተከበበ
በአፋሽ አጎንባሽ
እኔ አዉቃለሁ
ባይ
ከእኛ በላይ
ቆራሽ ማዕድ አበላሽ
ከእኛ በላይ
EFFORT ጥገኛ ባለሀብት
ከእኛ በላይ
EQUALITY ጠባብነት
ከእኛ በላይ
UNITY ትምህክተኝነት
የወያኔ ፈሊጥ
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!