የወያኔ ስርዓት
በ1983 ዓ/ም ትልቋን ኢትዮጵያን ማስተዳደር ሲጀምር ኢትዮጵያዉያን ያለፈዉ ገዳይና የአፈና ስርዓት ለአንዴና
ለመጨረሻ ያከትማል ብለዉ አስበዉ ነበር፤ ነገር ግን ወያኔ ብዙም ሳይዘልቅ የሽግግር መንግሰቱን
ለብቻዉ የተዘጋጀ ድግስ በማድረግ አላማዉን የሚደግፉትን የጎሳ ፖለቲከኞች (ኦነግ ፤ ኦብነግ የመሳሰሉትን) ብቻ በማሰባሰብ ነገር
ግን ብዙሃን ኢትዮጵያዉያንን በማግላል ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ኃይሎች ቅንጅት (ኢ.ዴ.ኃ.ቅ. ) የመሳሰሉት የአንድነት ሃይሎች በሽግግሩ
ሂደት እንዳይሳተፉ በሩን በማለዳዉ ዘጋ፡፡ ወያኔ ከዚህ ጊዜ ጀምሮ በጦር ሜዳ ያገኘዉን ድል በሰላማዊ መድረክ መድገም አልቻለም፡፡
በዚህ ሁኔታ ነዉ ወያኔ የኢትዮጵያ ታሪካዊ አካል የሆነችዉን ኤርትራን በማስገንጠል የ80 ሚሊዮን ህዝብ ሃብት የሆነችዉን ኢትዮጵያን
ያለባህር በር አስቀርቶል፤ የኤርትራን መገንጠል ተቃዉመዉ በወጡ ሰላማዊ ሰልፈኞች ጨፈጨፈ፤ ለራሱ የሚመቸዉን ነገር ግን እራሱ የማይገዛበትን
ህገመንግስት አፀደቀ፡፡
ወያኔ የኢትዮጵያ ማህበረ-ፖለቲካዊ
ችግር በአማራ ህዝብ የተፈጠረ በማድረግ አማራዉ ከሌላዉ ኢትዮጵያዊ ወገኑ ጥላቻ እንዲደርስበት እየታተረ ይገኛል፤ ከአዲስ አበባ
ዮንቨርስቲ በኤርትራ ጉዳይ በደረሰበት ተቃዉሞ 43 የሚደርሱ ኢትዮጵያ ብዙ ወጭ ያወጣችባቸዉ ምሁራንን በ 1984 ዓ/ም በአንድ
ጀምበር እንዲባረሩ አድርጎል፡፡
ከዕዉቀት ጋር የተጣላ የሚመስለዉ
ወያኔ ከኤርትራ ጋር በድንበር ዉዝግብ በገባ ማግስት እንኳን ለአልጀርስ ስምምነት ሲጠራ ኢትዮጵያ የታሪክም ሆነ የአለም አቀፍ ህግ ምሁራን የሆኑ ዜጎች ሳታጣ የዉጭ ዜጎችን
በመቅጠር ኢትዮጵያ በጦር ሜዳ ያገችዉን ድል በሰላማዊ መድረክ እንድታጣ አድርጎል፡፡
ወያኔ የኢትዮጵያዉያን አንድነት
ለማናጋትና ለሙስና መደላድል የሚሆነዉን ስልጣን ለማራዘም የጎሳ ፌዴራሊዝም ተግባራዊ ያደረገ ሲሆን ኢትጵያዊነትንም ባንዲራ ጨርቅ
ነዉ፤ ኢትዮጵያ የ100 አመት ብቻ ታሪክ ነዉ ያላት፤ አክሱም ለትግሬዉ እንጂ ለጉራጌዉ ምኑ ነዉ እያለ እያንኮሰሰ ያለ ሃይል ነዉ፡፡
የወያኔ ሃይል ለምራብያዊን ባለዉ
ተመችነት በሚጎርፍለት ከፍተኛ ዕርዳታና ከቻይና ከሚሰጠዉ ከፍተኛ አስገዳጅ ብድር (ከቻይና በሚገኝ ብድር ቻይናዉያን ብቻ ያለ ተወዳዳሪ
የሚሳተፉባቸዉ ኮንትራቶች ናቸዉ፡፡) አንጻር እያሳየ ያለዉ የመንገድ ዝርጋታ ፤ የሃይል ልማት እና ሌሎች የመንግስት ልማቶች እዚህ
ግባ የሚባል አይደለም ምክንያቱም በሙስና ምክንያት ከሀገር ዉጭ የሚወጣዉ ገንዘብ በጣም ከፍተኛ እንደሆነ ግሎባል ፋይናንሺያል ኢንተግሪቲ
ያረጋገጠዉ ሃቅ ነዉ፡፡
ጎበዝ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዉያን
ጥቃቅን ልዩነቶቻችንን ወደ ወደ ጎን በማድረግ ሰላማዊ በሆነዉ የተቃዉሞ ፖለቲካ እንቅስቃሴ ብንሳተፍ የጋራ ቤታችንን ኢትዮጵያን
ከጥፋት መታደግ እንችላለን፡፡ ኢትዮጵያን የጋራችን ማድረግ እንችላለን እንዲል መራራ ገዲና፡፡
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!
ከዚህ በታች የምታዩት ስም ዝርዝር
ከአዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ ወያኔ መንግስት የሚከፍለዉ ደመወዝ እንደሌለ ሰበብ ፈጥሮ ያባረራቸዉ ምሁራን ናቸዉ፡፡