Followers
Tuesday, September 24, 2024
Wednesday, September 11, 2024
የኢትዮጵያ ወራት እና ስያሜያቸው…!!!(ዳዊት ከበደ ወየሳ)
የኢትዮጵያ ወራት እና ስያሜያቸው…!!!
Sunday, September 8, 2024
መሸቀጫ ሆንሽ!!! አብራሃም ለቤዛ
መሸቀጫ
ሆንሽ!!! አብራሃም ለቤዛ
ሰንደቅ አላማ የሚጥሉሽ የሚያነሱሽ፤
የጭንቅ ቀን ያስታወሱሽ፤
ሲፈለጉ የሚረግጡሽ፤
የሚበጥሱሽ፤
ያ ያየነው በመስቀል በዓል፤
በአድዋ ክብር በዓል፤
ፖሊስ ከካድሬ ተናቦ ሰንደቅ ዓላማ ሲያረክስ፤
ከመኪና ሰንደቅ ጌጥ ሲልጥ ሲያሻው በመቀስ
ሲመቅስ፤
ዛሬ ስልጣን የሚያጣ መስሎት ፤
በእምየ ኢትዮጵያ ተከልልሎ፤
ሰንደቅ ሰንደቅ ሰንደቅ ዓላማየ፤
እንዴት ተደረጎ ይደፈራል ይላል ፤
ሰንደቅ ይዘምራል፤
ሰንደቅ ይንከባከባል፤ ይሰቅል ያወረዳል፤
እባክህን እባክሽን አታዋክቡን፤
እንደለመድከው እንደለመድሽው የካድሬነት ወጉን ፤
ለሰንደቅ ዓላማ ስትጠሩን ፤
ምናለ ብታስታዉሱ የረገጣችኋትን፤
ሰንደቅ ዓላማዋን የረገጣችኋትን የመቀሳችኋትን፤
ከወጣቱ አንገት ከሚሞተው ከሰንደቅ ዓላማ
በፊት፤
ከከበዎሮ ከዕምነት ተቋም ከሚተጉት በፀሎት
ፍታት፤
ከቀሚሷ መቅሳችሁ እናት ባገር እንዳንመስል፤
ያስደፋችሁ የእናት አንገት የአገር ክብር፤
ይረሳል ወይ ድርጊታችሁ ለራሳችሁ፤
ካድሬም ሾርት ሚሞሪ ነው ለካን፡፡
Sunday, July 28, 2024
ኢትዮጵያዊው ሠማዕት፡-አቡነ ጴጥሮስ ስሜነህ ደስታ (ዘመን መጽሔት ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም )
የ20ኛው ክፍለ ዘመን መጀመሪያ ታላቅ ሠማዕት የሆኑት አቡነ ጴጥሮስ በ1875 ዓ.ም በቀድሞ አጠራር በሸዋ ጠቅላይ ግዛት በፍቼ ከተማ ተወለዱ። አቡነ ጴጥሮስ በሠማዕትነት እንደሚሞቱ መምህራቸው በትንቢት ነግሯቸውም ነበር። አለቃ ተጠምቀ የተባሉ ቅድስናን ከሊቅነት ጋር አስተባብረው የያዙ የቅኔ መምህራቸው አንድ ቀን አቡነ ጴጥሮስን ጠርተው ‹‹ሀይለማሪያም፣ አንተ ወደፊት ጳጳስ ትሆናለህ፤ በወቅቱም አረመኔ በዚች አገር ላይ ይሰለጥናል። ታዲያ አንተ ያኔ በነፍስህ ሳትሳቀቅ በሠማዕትነት እለፍ። ሠማዕትነት ክፍልህ ነው። አደራ!›› ብለዋቸውም እንደነበር ይነገራል።
ይኸውም ትንቢት ደርሶ አቡነ ጴጥሮስ በሠማዕትነት ለማለፍ በቅተዋል። አቡነ ጴጥሮስ የጵጵስና ስማቸውን ከማግኘታቸው በፊት መምህር ሀይለማሪያም ይባሉ ነበር። በልጅነታቸው ወላጆቻቸው ወደ ደብረሊባኖስ ገዳም በመውሰድ በሀይማኖትና በምግባር ተኮትኩተው እንዲያድጉ አድርገዋቸዋል። የቤተክርስቲያን ሥርዓተ ትምህርት ከንባብ እስከ ቅኔ ያሉትን ትምህርቶች በሚያስገርም ፍጥነት ከተማሩ በኋላ ወደ ቅኔው አውድማ ጎጃም በመሄድ በዋሸራ የቅኔ ትምህርታቸውን ፈፅመው መምህርም ሆነዋል። የዜማውንም ትምህርት ወደ ጎንደር በመሄድ
ተምረዋል። በመቀጠልም ወሎ ቦሩ ሜዳ ላይ ወንበር ዘርግተው የመጽሐፍት ሚስጢር ይመግቡ ወደ ነበሩት ወደ ሊቁ አካለወልድ በመሄድ ዋና ዋናዎቹን የመጽሐፍት ትርጓሜ ማለትም ብሉያትን፣ ሐዲሳትን እና ሊቃውንትን በሚገባ አካሂደዋል።
ከዚህ በኋላ በ1900 ዓ.ም ወሎ አማራ ሳይንት ሄደው በምስካበ ቅዱሳን ገዳም ገብተው ወንበር ዘርግተው ለዘጠኝ ዓመታት ቅኔንና መጻሕፍትን አስተማሩ። በ1910 ዓ.ም ወደ ደብረሊባኖስ መጥተው ሥርዓተ ምንኩስናን ፈፀሙ። ከዚያም በመምህርነት ተሹመው ደብረ መንክራት ምሁር ኢየሱስ ገዳም ሄደው ለስድስት ዓመታት ካስተማሩ በኋላ በ1916 ዓ.ም እንደገና በዝዋይ ደብረጽዮን ቅድስተ ማሪያም ገዳም በመምህርነት ተሹመው ለሶስት ዓመታት አገልግለዋል። በ1919 ዓ.ም ወደ አዲስ አበባ በመምጣት የመንበረ ልዑል ቅዱስ ማርቆስ መምህርና በቤተ መንግስት የቀዳማዊ ኃይለ ሥላሴ የንስሀ አባትም ሆኑ።
ኢትዮጵያ በራሷ ተወላጅ ጳጳሳት ልጆች እንድትመራ ከ1600 ዓመታት በኋላ ስለተፈቀደላት በሀይማኖታቸውና በስነምግባራቸው የተመሰከረላቸው አምስት ደጋግ አባቶች ሲመረጡ አንዱ አቡነ ጴጥሮስ ነበሩ። በዚህ መሰረት ኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ የራሷን ጳጳስ ስትሾም አቡነ ጴጥሮስ ግንቦት 18 ቀን 1921 ዓ.ም ጵጵስና ተሾሙ። ከዚህ በኋላ አቡነ ጴጥሮስ ጳጳስ ዘምስራቀ ኢትዮጵያ ተብለው ተሹመዋል። ቤተክርስቲያንንና አገራችንን በፀሎታቸው፤ ሕዝብን በትምህርታቸው እየጠበቁ በተጋድሎ እየኖሩ ሳለ አረመኔው የኢጣሊያ ፋሺስት በ1928 ዓ.ም. በኢትዮጵያ ላይ የግፍ ጦርነት አውጆ ሕዝቡንም በግፍ ይገድል ጀመር።
አቡነ ጴጥሮስ ይህንን ግፍ በማየታቸው ከአገራችን አርበኞች ጋር በመሆን በፀሎታቸው ሊዋጉት ተነሱ። ቀዳማዊ ኃይለሥላሴን ተከትለው ወደ ማይጨው ዘመቱ። ፋሺስቱ በማይጨው በመርዝ ጋዝ የተደገፈ ጦርነት ከማድረጉ የተነሳ የኢትዮጵያ ሠራዊት ቢበታተንም ከንጉሰ ነገስቱ ጋር ወደ አዲስ አበባ የተመለሱት አቡነ ጴጥሮስ ወደ ደብረሊባኖስ ሄደው ለሀገርና ለነፃነት መሞት ቅዱስ ተግባር መሆኑን ለሰላሌ አርበኞች በሚገባ አስተምረዋል። በደብረሊባኖስ ጫካዎች ውስጥ መሽጎ የነበረውን የእነ ደጅአዝማች አበራ ካሳ አርበኛ ጦር እና በሸንኮራ በኩል መሽጎ የነበረውን የእነ ፍቅረማሪያም አርበኛ ጦር እንዲሁም በምዕራብ ይመራ ከነበረው የእነ ደጃዝማች አባነብሶ ጦር ሶስቱም በአንድ ጊዜ ወደ መሃል አዲስ አበባ በመግባት አዲስ አበባ ላይ ሰፍሮ የነበረውን ፋሺስት ለመውጋት ታቅዶ የነበረውን እቅድ በመረጃ ክፍተት ምክንያት ውጤታማ ሳይሆን ቀረ።
መጀመሪያ የእነ ፍቅረማሪያም አርበኛ ጦር በኮተቤ አድርጎ የካ ሚካኤል ላይ ሲደርስ ተመትቶ ተመለሰ። ይሄኛው እንዳለቀ የእነ አባነብሶ ጦር በባቡር ጣቢያ መጣሁ ቢልም በጠላት ጦር ድጋሚ ተመትቶ ተመለሰ። መጨረሻ ላይ የእነ ደጃዝማች አበራ ካሳ አርበኛ ጦር በእንጦጦ በኩል ቢመጣም እሱም በጠላት ጦር ተመትቶ ተመለሰ። በዚህ አይነት ሁኔታ ሶስቱም የአርበኞች ጦር በመረጃ ክፍተት ምክንያት እየተመታ ወደ መጣበት ሲመለስ አቡነ ጴጥሮስ አብረው ከአርበኞች ጦር ጋር መመለሱን አልፈለጉትም። ይልቁንም ብችል ጠላት በኢትዮጵያ ላይ እያደረሰ ያለውን ግፍ በቅርብ እርቀት ሆኖ የሚመለከተውን ሕዝብ በማትጋት ጠላት ላይ እንዲነሳ አደርጋለሁ። ካልሆነም ደግሞ እዚሁ እሞታለሁ። በማለት ከአርበኞቹ ተነጥለው አዲስ አበባ ቀሩ።
ይሁን እንጂ ጠላት በመላው ከተማ ያሰማራቸው ባንዳዎች አቡነ ጴጥሮስን እንዳሰቡት ሊያንቀሳቅሷቸው አልቻሉም ነበር። በመሆኑም አቡነ ጴጥሮስ የሀገሬ ህዝብ ለጠላት እንዳይገዛ በአደባባይ አውግዤ ጠላትን ረግሜ በሠማዕትነት ባልፍ ይሻለኛል ብለው ራሳቸውን ለጠላት አሳልፈው ለመስጠት ወሰኑ። የፋሺስት ኢጣሊያ እንደራሴ ለነበረው ለራስ ኃይሉ ሄደው እጃቸውን ሰጡ። እሱም አቡነ ጴጥሮስን ወስዶ ለግራዚያኒ ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም. አሳልፎ ሰጣቸው። ግራዚያኒም ግማሽ ቀን ባልሞላ ጊዜ ውስጥ እንዲገደሉ ወሰነባቸው።
አቡነ ጴጥሮስ በፈቃዳቸው እጃቸውን አሳልፈው ከሰጡበት ጊዜ ጀምሮ በጠላት የጥይት እሩምታ በሠማዕትነት እስካለፉበት ጊዜ ድረስ የነበረውን ሂደት ኮሪየሬ ዲላ ሴራ የተባለ ጋዜጣ ወኪልና የምስራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው ፓጃሊ የተባለ ጋዜጠኛ እ.ኤ.አ ሰኔ 15 ቀን 1936 በአዲስ አበባ በነበረበት ጊዜ በአቡነ ጴጥሮስ ላይ የተሰጠውን ፍርድና የተፈፀመውን የግፍ ግድያ ባየውና በተመለከተው መንገድ እንደሚከተለው ጽፎት ነበር።
‹‹ሐምሌ 22 ቀን 1928 ዓ.ም አቡነ ጴጥሮስ ተይዘው ወደ ግራዚያኒ ቀረቡ። በዚህም ጊዜ አቡነ ቄርሎስ የተባሉት ግብፃዊ ጳጳስ ቀርበው ለእስክድርያው መንበረ ፓትሪያርክ ምክር ቤት ሳታሰማ በአቡነ ጴጥሮስ ላይ አንዳች ነገር ማድረግ አይገባህም ሲሉ ለግራዚያኒ ነገሩት። አቡነ ቄርሎስ ይህን ማለታቸው በዲፕሎማቲክ ደረጃ ለዓለም ለማሰማትና የአቡነ ጴጥሮስ ህይወትን ለማትረፍ አስበው ነበር። ነገር ግን ግራዚያኒ የአቡነ ጴጥሮስን የሞት ፍርድ እንኳንስ እስከ ግብፅ ከአዲስ አበባ ውጪ ከመሰማቱ በፊት በግማሽ ቀን ውስጥ እንዲፈፀም መመሪያ አስተላለፈ።››
የምስራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ ፓጃሊ የአቡነ ጴጥሮስን መልካቸውንና ተክለ ቁመናቸውን ሲገልጽ ‹‹አቡነ ጴጥሮስ ቁመታቸው ረጅም፣ ፊታቸው ዘለግ ያለ፣ መልካቸውም ጠየም ያለ፣ አዋቂነታቸውና ትህትናቸው ከገፃቸው የሚነበብ ሲሆን በወቅቱ ለብሰውት የነበረው ልብስ የጵጵስና ጥቁር ካባ ያውም በጭቃ የቦካ ነበር።›› በማለት ይገልፀዋል።
በዚህ ሁኔታ ወደ ችሎት ቀረቡ። በችሎቱ የተሰየሙት ዳኞች ሶስት ሲሆኑ ጣሊያኖችና የጦር ሹማምንቶች ናቸው። የመሃል ዳኛው ኮሎኔል ነበር። የቀረበባቸው ወንጀል ሕዝብ ቀስቅሰዋል፣ ራስዎም አምፀዋል፣ ሌሎችም እንዲያምፁ አድርገዋል የሚል ነበር። ዳኛው ‹‹ካህናቱም ሆኑ የቤተክህነት ባለስልጣኖች፣ ሊቀጳጳሱ አቡነ ቄርሎስ የጣሊያንን መንግስት ገዢነት አሜን ብለው ሲቀበሉ እርስዎ ለምን አመፁ? ለምን ብቻዎን አፈንጋጭ ሆኑ? ›› ሲል ጠየቃቸው። አቡነ ጴጥሮስም በቆራጥነት ‹‹አቡነ ቄርሎስ ግብፃዊ ናቸው። ስለኢትዮጵያና ስለኢትዮጵያዊያን የሚገዳቸው ነገር የለም። እኔ ግን ኢትዮጵያዊ ነኝ። ኃላፊነትም ያለብኝ የቤተክርስቲያን አባት ነኝ። ስለዚህ ስለ አገሬና ስለ ቤተክርስቲያኔ እቆረቆራለሁ። ከዚህ በቀር ለእናንተ ችሎት የማቀርበው ነገር የለኝም። ለፈጣሪዬ ብቻ የምናገረውን እናገራለሁ። እኔን ለመግደል እንደወሰናችሁ አውቃለሁ። ስለዚህ በእኔ ላይ የፈለጋችሁትን አድርጉ። ግን ተከታዮቼን አትንኩ›› አሉ።
በጥይት ተደብድበው ሲገደሉ እንዲመለከት ተጋብዞ ለተሰበሰበው ሕዝብ ‹‹አረማዊ የሆነው የፋሺስት መንግሥት ቤተክርስቲያንን ለማቃጠል፣ ሕዝበ ክርስቲያንን ለመግደል፣ ሀይማኖትን ለማጥፋት፣ ታሪካችንን ለማበላሸት የመጣ ነው እንጂ በጎ ለመሥራት ስላልመጣ ለዚህ ለግፈኛ አትገዙ፤ ስለውድ አገራችሁ፣ ስለቀናች ሀይማኖታችሁ ተከላከሉ። ነፃነታችሁን ከማርከስ ሙታችሁ ስማችሁ ቢቀደስ ታላቅ ዋጋ ያለው ክብር ታገኛላችሁ። የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዚህ ለጠላት እንዳይገዛ አውግዣለሁ። የኢትዮጵያ መሬት ጠላትን ብትቀበል የተረገመች ትሁን። በፈጣሪዪ በኢየሱስ ክርስቶስ ስም የተገዘተች ትሁን›› ብለው አወገዙ።
ቀጥለውም አቡነ ጴጥሮስ ችሎቱ ላይ እንዳሉ ሕዝቡ ሁሉ ስለሳቸው እያዘነ ሳለ መስቀላቸውን አውጥተው እየፀለዩ ሕዝቡን ባረኩት። ወዲያው የሞታቸው ፍርድ ሲሰማ ሕዝቡ በኢጣሊያ የእጅ ሰላምታ አይነት እጁን እንዲያነሳ ታዘዘ። በዚያን ጊዜ አቡነ ጴጥሮስ የሞታቸው ሰዓት መድረሱን አውቀው ሰዓታቸውን ከኪሳቸው አውጥተው ተመለከቱ። በወቅቱ ምንም ፍርሀት አይታይባቸውም ነበር። የሞታቸውን ፍርድ ያነብ የነበረ ኢጣሊያዊ ዳኛ ግን ይንቀጠቀጥ ነበር። ታላቅ ፍርሀትም በፊቱ ላይ ይታይ ነበር። የሞታቸው ፍርድ ከተነበበ በኋላ የፈረዱባቸውን ዳኞች ፀልይው በመስቀላቸው ባረኳቸው።
አቡነ ጴጥሮስ ሊገደሉ ሲወሰዱ ጥይት አልፎ ሌላ ሰው እንዳይመታ ግንብ ይፈለግ ጀመር፡ሩቅ ባለመሄድ ከመካነ ፍትሁ አስር ሜትር ግንብ ያለው መግደያ ቦታ ተገኘና ወደዚያው ተወሰዱ። ከገዳዮቻቸው አንዱ ‹‹ ፊትዎን መሸፈን ይፈልጋሉን ?›› ሲል ጠየቃቸው። ‹‹ይህ ያንተ ሥራ ነው›› ሲሉ መለሱለት። ወዲያው ቦታው እንደደረሱ ወንበር ቀረበላቸውና ፊታቸውን ወደ ግንቡ ጀርባቸውን ወደ ሕዝቡ አድርገው እንዲቀመጡ ተደረጉ። ከዚያም ስምንት ወታደሮች በስተጀርባቸው ሃያ እርምጃ ርቀው ተንበርክከው በተጠንቀቅ ቆሙ። ወዲያው አዛዡ ተኩስ በማለት ትእዛዝ ሲሰጥ ስምንቱም ተኩሰው መቷቸው። ነገር ግን በስምንት ጥይት ሳይሞቱ ቀሩ። መሞታቸውንና አለመሞታቸውን ለማረጋገጥ ዶክተር ተጠራ። ዶክተሩም እንዳልሞቱ አረጋገጠ። ከዚያ በኋላ አንድ ወታደር በሶስት የሽጉጥ ጥይት ራስ ቅላቸውን መትቶ ገደላቸው።
አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉበት ቦታ መሀል አዲስ አበባ ዛሬ መታሰቢያ ሀውልታቸው ቆሞ በሚገኝበት ቦታ ላይ ነው በማለት የጋዜጣ ወኪልና የምስራቅ አፍሪካ ዜና መዋዕል አዘጋጅ የነበረው ጋዜጠኛ ፓጃሊ ስለ አቡነ ጴጥሮስ ሠማዕትነት ምስክርነቱን ሰጥቷል። በተጨማሪም ደራሲና ጋዜጠኛ ጳውሎስ ኞኞ አቡነ ጴጥሮስ እንዴት ሞቱ ? ሲል በወቅቱ አቡነ ጴጥሮስ ሠማዕትነት ሲቀበሉ በቦታው በአካል በመገኘት ሁኔታውን ይከታተሉት የነበሩትን ሙሴ ፓይላክን ጠይቋቸው ሲመልሱ፣ ‹‹ አቡነ ጴጥሮስ የተገደሉ እለት እዚያው ነበርኩ። መጀመሪያ በእጃቸው ይዘው የነበረውን መጽሐፍ ቅዱሳቸውን ተሳለሙት። ቀጥለው በያዙት መስቀል አማትበው ሕዝቡን ባረኩ። የኪሳቸውን ሰዓት አውጥተው ካዩ በኋላ መልሰው ከተቱት። ወዲያው ወታደሮች በእሩምታ ተኩስ ገደሏቸው። ይህ እንደሆነ አስገዳዩ ኮሎኔል ተመልካቹን ህዝብ አጨብጭቡ ብሎ አዘዘና ተጨበጨበ። ማታ ከአስገዳዩ ኮሎኔል ጋር ተገናኝተን ስንጫወት ‹በዚህ ቄስ መገደል እኮ ሕዝቡ ተደስቷል› አለኝ። ‹እንዴት? ›ብለው ‹አላየህም ሲያጨበጭብ !›አለኝ ‹ባታውቀው ነው እንጂ ሕዝቡ ሲናደድም ያጨበጭባል› አልኩት። እንዴት ቢለኝ እጄን አጨብጭቤ አሳየሁት። ከዚህ በኋላ የሆነው ቢሆን ትልቅ ማስታወሻ አግኝቻለሁ ብሎ አቡነ ጴጥሮስ ሲገደሉ ይዘውት የነበረውን መስቀል፣ መጽሐፍ ቅዱስ እና የኪሳቸውን ሰዓት አሳየኝ›› ብለዋል።
አቡነ ጴጥሮስ ሠማዕትነትን በተቀበሉበት ቦታ ላይ የመታሰቢያ ሀውልት ቆሞላቸዋል። የእኚህን ታላቅና ቅዱስ ሠማዕት አባት ክብርና ተጋድሎ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን ቅዱስ ሲኖዶስ ከዘጠኝ ዓመት በፊት ቅዱስ ሰማዕት ብሎ በማፅደቅ በስማቸው በቅድስና ማዕረግ በስማቸው ታቦት ተቀርፆ ቤተክርስቲያን እንዲሠራላቸው ወስኗል። ይህም በተወለዱበት በሰሜን ሸዋ ስላሴ ሀገረስብከት በፍቼ ከተማ የቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ ተግባራዊ ሆኗል። ጉምቱ ባለቅኔ ፀጋዪ ገብረመድህን በግጥሙ ህያው አድርጓቸዋል። ይሁንና አፅማቸው የት እንደወደቀ ዛሬም ድረስ ሚስጢር እንደሆነ አለ። ደራሲ ፀሀይ መላኩ በአንድ ወቅት በኢቢኤስ ቴሌቭዥን ለብራና ልጆች ፕሮግራም በሰጠችው ቃለ ምልልስ የአቡነ ጴጥሮስ አስክሬን ፉሪ አካባቢ መኒሳ በምትባል ጉብታ ላይ ስለመቀበሩ የነገሯት አባት ስለመኖራቸው ተናግራለች።
በሰላሌ ዩኒቨርሲቲ የታሪክና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል ረዳት ፕሮፌሰር ስዩም መርጊያ አቡነ ጴጥሮስ ከህጻንነታቸው ጀምሮ ፆመኛና ፀሎተኛ እንደነበሩ እንዲሁም መንፈሳዊ ህይወት እንደሚታይባቸው፤ ዕድገታቸው በሀይማኖት ትምህርትና በመንፈሳዊ ህይወት የታጀበ እንደነበረ በመግለጽ ስለዕድገታቸው ያስረዳሉ። ከስጋዊው ይበልጥ መንፈሳዊው ህይወት ስለማረካቸው በፆም በጸሎት መወሰን ብቻ ሳይሆን፤ዓለም በቃኝ ብለው ምንኩስናን ተቀብለው በመምህርነት ከማገልገላቸው በተጨማሪ በወቅቱ አልጋ ወራሽ በነበሩት በራስ ተፈሪ ተመርጠው ቅዱስ ቄርሎስ መጽሐፍን ወደ አማርኛ እንዲተረጉሙ ከተመረጡ አምስት ሊቃውንት መካከል አንዱ ሆነው መሥራታቸውን ይገልጻሉ።
ረዳት ፕሮፌሰር ስዩም አቡነ ጴጥሮስ ለጣልያን አገዛዝ ባለመሸነፍ በአደባበይ ሕዝብ በተሰበሰበበት በጥይት ተደብድበው መሞታቸው በመንፈሳዊው ዓለም ሠማዕት እንደሚያደርጋቸው ጠቅሰው፤ በሠማዕትነታቸውም ፍቼ ከተማ ላይ በስማቸው የተሰየመ ካቴድራል መኖሩን እና በቅጥር ግቢው ውስጥ አዲስ አበባ ከተማ ያለውን የሚመስል ሀውልት በመታሰቢያነት የቆመላቸው መሆኑን ይናገራሉ። በፍቼ ከተማ ላይ በከተማ አስተዳደሩ በሰላሌ ኦሮሞ ማዕከል ውስጥ በስማቸው የተሰየመ የመሰብሰቢያ አዳራሽ እንዳለም ይገልጻሉ።
የአቡነ ጴጥሮስ ተጋድሎ ከጥቅምና ከማዕረግ በላይ ኢትዮጵያን ማስቀደም እንደሚገባ እና አገርን ከጠላት ለመከላከል ሀይማኖትም ሆነ ብሔርን ወይም ሌላ ነገርን ማዕከል አድርጎ መነሳት እንደማያስፈልግ የሚያሳይ ነው በማለት ረዳት ፕሮፌሰር ስዩም ያስረዳሉ።
በጅማ ዩኒቨርሲቲ በታሪክ ትምህርት ክፍል በተባባሪ ፕሮፌሰርነት መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶክተር ፀጋዬ ዘለቀ የአቡነ ጴጥሮስ የሠማዕትነት ተግባር በወቅቱ ለነበሩ ኢትዮጵያውያን፣ ለኢትዮጵያ መሞት ክብር እንደሆነ በማሳያነት የሚጠቅሱት መሆኑን እና የአርበኝነት ትግሉ እንዲፋፋም ከፍተኛ መነቃቃት የፈጠረ እንደሆነ ይጠቅሳሉ። በወቅቱ ለነበሩት ብቻ ሳይሆን የአሁኑም ሆነ የቀጣዩ ትውልድ የእሳቸውን ተግባር በማየት አገርን መውደድና ለአገር መቆም ምን እንደሚመስል ሊማርበት የሚያስችለው ነው ይላሉ።
ስሜነህ ደስታ
ዘመን መጽሔት ግንቦት 20 ቀን 2014 ዓ.ም
Friday, January 12, 2024
A reform culminated in changing logos
Abiy Administration in the name of reform, he is aggressively engaged in changing organization logos and in some case seems elimination of long held and accustomed logos that bear the lion. A reform culminated in changing logos Abiy who claimed a master of all, call his log changing reform ergonometric that bring mood of employees hardworking and then he dragged the nation in to defaulted. An extravagant expenditure on non-strategic areas such as lavish palace to bring his mood of primer tenure.The argument by some institutions like federal police doesn't hold water
Sunday, October 15, 2023
ኤርትራና ሲንጋፖር -አብራሃም ለቤዛ
ኤርትራ ከሲንጋፖር ጋር ለመተረክ የፈለግኩት
ከሰሞኑን የኤርትራ የተባበሩት መንግስታት ተቀማጭ አማባሳደር ከሲንጋፖር ጠቅላይ ሚኒስተር Mr. Yap Ong Heng ጋር ተገናኙና ተወያዩ የሚል
ዜና ነው፡፡ ነገር ነገር ያነሳዎል እንዲሉ ለመተረክ የፈለግኩት ስለሁቱ
አገሮች ግንኙነት ሳይሆን የምስራቅ አፍሪካ ሲንጋፖር እንሆናለን
ይል ስለነበረው የኤርትራዊያን ቅዠት ነው፡፡
የኤርትራ መንግስት ከኢትዮጵ ለመገንጠል በሚያደርገው ጥድፈት ዋዜማ ኤርትራን የምስራቅ አፍሪካ ሲንጋፖር እናደርጋታል ይል ነበር፡፡ የየደቡብ ምስራቅ ኤሺያ አገሮች በአጭር ጊዜ ከድህነት ስለወጡ ለብዙ የአፍሪካ አገሮች መቅኛ ነበሩ፡፡ ፈጣን እድገትና ልማት ግን ትክክለኛ የፖሊሲ አቅጣጫ በመያዝ የሚመጣ እንጂ በማለም ብቻ የሚሆን አይደለም፡፡ የኤርትራዊን የምስራቅ አፍሪካ ሲንጋፖር የመሆን ምኞት የመጣው ራሳቸውን ከሌላው ሀባሻ የኢትዮጵ ህዝብ እንዲሁም ከትግሬ ወንድሞቻቸው ለይተው ማየታቸው ነው፡፡ የ60 ዓመት የጣሊያን ቅኝ ገዢ ፖሊሲ በኤርትራዊያን ላይ ይኸ አስተሳሰብ እንዲጫን አድረጎል፡፡ ፕሮፌሰር ተከስተ ነጋሽ “Ethiopia and Eritrea- The Federal Experience” በሚለው ጥናታዊ ፅሁፋቸው ኤርትራዊያን ከኢትዮጵያ ለመነጠል ዳግም የሄዱበት መንገድ እኛ የተለየን ነን ፤ ከሃበሻ እኛ የሰለጠንን ነን፤ እኛ ከተገነጠልን በፍጥነት እንበለፅጋለን የሚለው አስተሳሰብ ስለሰረፀባቸው ነው ይላል፡፡
የሆነው ግን ኤርትራ የአፍሪካ ሲንጋፖር ሳይሆን
የአፍሪካ ሰሜን ኮርያ ሆነ፡፡ የሃበሻ ምቀኝነት እንዲሉ ለዚህ ደግሞ የወያኔ ኢተዮጵያ ኤርትራን በማሳጣት ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጋለች፡፡
የደቡብ ምስራቅ ኤሽ አገሮች ሲንጋፖር ፤ ማሌዥያ፤ ቬትናም፡ታይላድ ፤ኢንዶኔዢያና ፊሊፒንስ ሲሆኑ ፤ በአጭር ጊዜ ከድህነት በመውጣታቸው ምክንያትም የኤሽያ ታይገር የሚል የዳቦ ስም ወጥቶላቸዋል፡፡ የወያኔዎ ኢትዮጵያ ልማታዊ መንግስትን በመከተል የደቡብ ምስራቅ ኤሽያ አገሮች መንገድ እከተላለሁ ብትልም፤ ነገር ግን የኢትዮጵያ ፖሊሲ በጎሳ ፖለቲካ ፤ የጋራ መግባባት የሌለው ፖለቲካ ሃይል እና በሙስና የተጨማለቀ ፖለቲካ ሃይል የተተበተ ስለሆነ የደቡብ ምስራቅ ኤሽያ አገሮችን ፈለግ መከተል አልቻለችም፡፡ ነገር ግን ኢትዮጵያ ለራሷ የአፍሪካ ላይዮን የሚል የዳቦ ስም አውጥታለች፡፡ ለከታታይ 14 ዓመት (2005-2019) በሁለት ዲጂት ያደገ ኢኮኖሚ ባለቤት የሚል የተለመደ የወያኔዎች የአፍ ማሞሻ ጥቅስ ነበር፡፡
ፅንፈኛው ጃ-War መሃመድ የኦሮሞ ፖለቲከኛም በሲንጋፖር ኢኮኖሚ እምርታ እንደሚማረክና ሲንጋፖር እየተማረ
የሲንጋፖርን እድገት እናዳጠናዉም በተደጋጋሚ ይገልፃል፡፡ ችግሩ የሲንጋፖርና የደቡብ ምስራቅ ኤሽያ አገሮች ሲንጋፖር አገሮች መመንደግ
ሳይሆን እነሱ የሄዱበትን እኛ እንዳንሄድበት ራሳችንን አድርገናል፡፡ የእኛ መንገድ ማለት በህገመንግስታችንም ሆነ በኢኮኖሚ
ፖሊሲያችን ኢትዮጵያዊነት በዜጋነት እንዲደራጁ አንፈቅድም፡፡ የብሄር
ፖለቲካ ይዘን እንደ ዝንጀሮ መንጋ ባለች ሃብት (ክምር) ላይ ሰፍረን መበዝበዝ እንጂ ምርታማነትና ዕድገትን አናመጣም፡፡
Wednesday, August 30, 2023
የኦሮሞ ብሔርተኞች ተቃርኖ [Hypocrisy]! – አቻምየለህ ታምሩ
የኦሮሞ ብሔርተኞች ተቃርኖ [Hypocrisy]! – አቻምየለህ ታምሩ
በኢትዮጵያ ምልሰት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራችውን የኦሮሞ ጀግኖች እንደ ኦነግ ያዋረደ ድርጅት የለም። በቤተ ኦነግ የጀግኖቹ ጀግና፣ የራሶቹ ራስ የራስ ጎበና ስም ስድብ ነው። እኛ ከፍ ስናደርጋቸው እነሱ ዝቅ ሲያደርጓቸው የኖሩትን የኢትዮጵያ ጀግኖች እፍረተ ቢሶቹ ኦነጋውያን ዛሬ ስማቸው ሳይጠራ የኖሩ ኦሮሞዎች አድርገው ለመተረክ ይቃጣቸዋል። ብሔርተኞቹ ነውረኞች ስለሆኑ በንጉሡ ስር የአድዋ ዘመቻ ጠቅላይ ጦር አዛዥ የነበሩትን የራስ መኮነንን መታሰቢያ ሐውልት በቅርቡ በሐረር ከተማ አናታቸው ይፍረስና ማፍረሳቸውን እንኳ የረሳነው ይመስላቸዋል።
ለመሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኦሮሞ ጀግኖችን አስተዋጽኦ ከኦነግ በላይ የረሳና ያዋረደው ማነው? ከኦነግ በተጨማሪ የኦነግ ፕሮግራም አቀንቃኝ ብሔርተኞች አይደሉምን? አገራቸው ያቆመችላቸውን ሐውልትና ስም የደመሰሱ እነዚህ ነውረኞች አይደሉምን?
በክርስትና ሃይማኖት የቤተ ክርስቲያን መሰረት የሚባሉ አራት ጉባኤዎች አሉ። ቤተክርስቲያን የፀናችው በነዚህ አራት ጉባኤዎች ነው ተብሎ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ይታመናል። ይህንን framework በመጠቀም በ1927 ዓ.ም. ከዛሬ 84 ዓመታት በፊት የጎጃሙ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ራስ ጎበናን የኢትዮጵያን ምልሰት ካቆመው አራቱ ጉባኤ መካክል አንዱ ያደርገዋል። በወቅቱ የነበረው የመንፈስ ድክመት አገራችንን አደጋ ላይ ቢጥላት ኢትዮጵያ ምህርት ወይንም መዳን ታገኝ ዘንድ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ የጠራው የኢትዮጵያ ብርታት የቆመበትን የነራስ ጎበናን መንፈስ ነበር። እንዲህ ሲል. . .

አጥንቱን ልልቀመው መቃብር ቆፍሬ፣
ጎበናን ከሸዋ አሉላን ተትግሬ፤
ስመኝ አድሬአለሁ ትናንትና ዛሬ፣
ጎበናን ለጥይት አሉላን ለጭሬ፤
****
ተሰበሰቡና ተማማሉ ማላ፣
አሉላ ከትግሬ ጎበና ከጋላ፤
ጎበና ሴት ልጁን ሊያስተምር ፈረስ፣
አሉላ ሴት ልጁን ጥይት ሊያስተኩስ፤
አገሬ ተባብራ ካልረገጠች እርካብ፣
ነገራችን ሁሉ የእንቧይ ካብ የእንቧይ ካብ፤
***
[የኔ ራስ] ጎበና ከፈረስህ ጋራ ተነስ እንደገና፣
ትምህርት እንዲስፋፋ ጉልበት እንዲጠና፣
አራቱ ጉባኤ ይነሱልንና፣
መኮንን ደረሶ አሉላ ጎበና፣
አገራችን ትማር አሁን እንደገና፤
[የኔ ራስ]ጎበና ከፈረስህ ጋራ ተነስ እንደገና።
በዚህ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ገድልና ጀብዱ ላይ የሸፈቱት ኅሊና ቢሶች ኦነጋውያንና የርዕዮታለም መንትዮቻቸው ናቸው። የእነ ራስ ጎበናና የተቀሩት የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞችን አገርና ታሪክ ለማፍረስ እነ ኦነግ ሞቃዲሾ ሲከትሙ፣ እነ ኢሕአፓ ወደ አሲምባ ሲኮበልሉ፣ እነ ሕወሓት ደደቡት ሲወርዱ የራስ ጎበናንና የሌሎችን ኢትዮጵውያን ጀግኖች አርበኞች ታሪክ ጠብቆ ያቆየው እንደ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ አይነቱ አማራ ነው።
ዐፄ ዮሐንስ ምንም እንኳ ጎጃምና ወሎን ቢጨፈጭፉም መተማ ላይ ሰማዕት በመሆናቸው አማራው የሚያከብራቸውን ያህል በፋሽስት ወያኔዎች ዘንድ ክብር የላቸውም። አማራው መተማ ዮሐንስ የሚል ከተማ በስማቸው ሲጠራ ፋሽስት ወያኔዎች ግን በባለሟላቸው በራስ አሉላ ስም የተሰየመውን ትምህርት ቤት የትግራይን ሪፑብሊክ ለመመስረት ደደቢት በወረደው መለስ ዜናዊ ስም ለውጠውታል።
የኦሮሞ ብሔርተኞች ከሰሞኑ የአድዋን ድል ዋነኞቹን የጦሩ አዛዦችን ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክንና እቴጌ ጠሐይቱን ትተው የኦሮሞ ጀግና ፈረሰኛ ወታደሮች ድል እንደሆነ አድርገው እየተናገሩ ናቸው። እንደሚታወቀው የአድዋ ጦርነት ጥሊያን የተጨፈጨፈበት ድል ነው። የኦሮሞ ብሔርተኞች እየነገሩን ያለው ይህንን የጥሊያን ጭፍጨፋ ያካሄዱት የኦሮሞ ፈረሰኛ ወታደሮች ናቸው የሚል ነው። ጥሩ። ይህንን የሚሉትን የኦሮሞ ብሔርተኞች አኖሌና ጨለንቆ ላይ ተካሄዱ ለሚሏቸው ጦርነቶች ተደረገ ለሚሉት ጭፍጨፋ ግን ኃላፊነቱን የዳግማዊ ምኒልክ ያደርጉታል።
በታሪክ ሞቅ ሲል በማንኪያ፤ ሲቀዘቅዝ በእጄ አይሰራም። በአድዋ ድል የኦሮሞ ፈረሰኛ ወታደሮች ከሆነ የአርሲና የሐረር «ጭፍጨፋ» የተባለውንም የፈጸሙት እነዚህ የአድዋ ድል ባለቤት የተደረጉት ጀግና የኦሮሞ ፈረሰኛ ወታደሮች ናቸው። ለአድዋው ድል ሲሆን እውቅናው ከሁሉ በላይ ለጀግና የኦሮሞ ፈረሰኛ ወታደሮች፤ እነኚህ ወታደሮች አርሲና ሐረር ባካሄዱት የማስገበር ዘመቻ ደረሰ ለሚባለው «ጭፍጨፋ» እና «ቅኝ ግዛት» ግን ተጠያቂው ዳግማዊ ምኒልክ ሊሆኑ አይችሉም!
«ሰውን ሲወዱ ከነንፍጡ እና ልጋጉ ነው» ይላል ያገሬ ሰው። በአድዋ ላይ የተመዘገበውን ድል ከሁሉ በላይ የኦሮሞ ጀግና ፈረሰኛ ወታደሮች የሰጠ አንድ ሰው፤ ከአድዋው ድል ጥቂት አመታት በፊት እነዚሁ የኦሮሞ ፈረሰኛ ወታደሮች በአርሲና ሐረር ያደረሱትን «ጭፍጨፋም» የራሱ ወገን የሆኑ ሰዎች ያደረሱት መሆኑን አምኖ ትክሻውን ደልደል በማድረግ መቀበልና ተፈጸመ ላለው ጭፍጨፋም ተጠያቂ ማድረግ ካለበት እነሱኑ ነው እንጂ ሌላ አካል ተጠያቂ ማድረግ የለበትም።
ስለዚህ ዛሬ የኦሮሞ ብሔርተኞች በአድዋው ድል እውቅና እየሰጧቸው ያሉት የኦሮሞ ፈረሰኛ ወታደሮች ከአድዋ ድል ጥቂት አመታት በፊት እነዚሁ የኦሮሞ ወታደሮች ሐረርና አርሲ ላደረሱት «ጭፍጨፋ» እና «ቅኝ ግዛት» ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ተጠያቂ የሚሆኑበት አመክንዮ ሊኖር አይችልም! ስለሆነም ወይ የአድዋውን ድልም እንደ አኖሌውና ሐረሩ ጭፍጨፋ ሁሉ ለምኒልክ ተውት አልያም በነዚሁ አድዋ በዘመቱ የኦሮሞ ጀግና ፈረሰኞች የተካሄደውን የአርሲና የሐረሩ ጭፍጨፋ ያላችሁትንም እንደ አድዋው የጥሊያን ጭፍጨፋ ሁሉ ኃላፊነቱን በመውሰድ ተጠቃለሉትና ምኒልክን ለቀቅ አድርጓቸው Otherwise it is pure hypocrisy to make such a sudden U-turn 213