የኦሮሞ ብሔርተኞች ተቃርኖ [Hypocrisy]! – አቻምየለህ ታምሩ
በኢትዮጵያ ምልሰት ውስጥ ከፍተኛ አስተዋጽኦ የነበራችውን የኦሮሞ ጀግኖች እንደ ኦነግ ያዋረደ ድርጅት የለም። በቤተ ኦነግ የጀግኖቹ ጀግና፣ የራሶቹ ራስ የራስ ጎበና ስም ስድብ ነው። እኛ ከፍ ስናደርጋቸው እነሱ ዝቅ ሲያደርጓቸው የኖሩትን የኢትዮጵያ ጀግኖች እፍረተ ቢሶቹ ኦነጋውያን ዛሬ ስማቸው ሳይጠራ የኖሩ ኦሮሞዎች አድርገው ለመተረክ ይቃጣቸዋል። ብሔርተኞቹ ነውረኞች ስለሆኑ በንጉሡ ስር የአድዋ ዘመቻ ጠቅላይ ጦር አዛዥ የነበሩትን የራስ መኮነንን መታሰቢያ ሐውልት በቅርቡ በሐረር ከተማ አናታቸው ይፍረስና ማፍረሳቸውን እንኳ የረሳነው ይመስላቸዋል።
ለመሆኑ በኢትዮጵያ ታሪክ ውስጥ የኦሮሞ ጀግኖችን አስተዋጽኦ ከኦነግ በላይ የረሳና ያዋረደው ማነው? ከኦነግ በተጨማሪ የኦነግ ፕሮግራም አቀንቃኝ ብሔርተኞች አይደሉምን? አገራቸው ያቆመችላቸውን ሐውልትና ስም የደመሰሱ እነዚህ ነውረኞች አይደሉምን?
በክርስትና ሃይማኖት የቤተ ክርስቲያን መሰረት የሚባሉ አራት ጉባኤዎች አሉ። ቤተክርስቲያን የፀናችው በነዚህ አራት ጉባኤዎች ነው ተብሎ በእምነቱ ተከታዮች ዘንድ ይታመናል። ይህንን framework በመጠቀም በ1927 ዓ.ም. ከዛሬ 84 ዓመታት በፊት የጎጃሙ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ ራስ ጎበናን የኢትዮጵያን ምልሰት ካቆመው አራቱ ጉባኤ መካክል አንዱ ያደርገዋል። በወቅቱ የነበረው የመንፈስ ድክመት አገራችንን አደጋ ላይ ቢጥላት ኢትዮጵያ ምህርት ወይንም መዳን ታገኝ ዘንድ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ የጠራው የኢትዮጵያ ብርታት የቆመበትን የነራስ ጎበናን መንፈስ ነበር። እንዲህ ሲል. . .

አጥንቱን ልልቀመው መቃብር ቆፍሬ፣
ጎበናን ከሸዋ አሉላን ተትግሬ፤
ስመኝ አድሬአለሁ ትናንትና ዛሬ፣
ጎበናን ለጥይት አሉላን ለጭሬ፤
****
ተሰበሰቡና ተማማሉ ማላ፣
አሉላ ከትግሬ ጎበና ከጋላ፤
ጎበና ሴት ልጁን ሊያስተምር ፈረስ፣
አሉላ ሴት ልጁን ጥይት ሊያስተኩስ፤
አገሬ ተባብራ ካልረገጠች እርካብ፣
ነገራችን ሁሉ የእንቧይ ካብ የእንቧይ ካብ፤
***
[የኔ ራስ] ጎበና ከፈረስህ ጋራ ተነስ እንደገና፣
ትምህርት እንዲስፋፋ ጉልበት እንዲጠና፣
አራቱ ጉባኤ ይነሱልንና፣
መኮንን ደረሶ አሉላ ጎበና፣
አገራችን ትማር አሁን እንደገና፤
[የኔ ራስ]ጎበና ከፈረስህ ጋራ ተነስ እንደገና።
በዚህ የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞች ገድልና ጀብዱ ላይ የሸፈቱት ኅሊና ቢሶች ኦነጋውያንና የርዕዮታለም መንትዮቻቸው ናቸው። የእነ ራስ ጎበናና የተቀሩት የኢትዮጵያ ጀግኖች አርበኞችን አገርና ታሪክ ለማፍረስ እነ ኦነግ ሞቃዲሾ ሲከትሙ፣ እነ ኢሕአፓ ወደ አሲምባ ሲኮበልሉ፣ እነ ሕወሓት ደደቡት ሲወርዱ የራስ ጎበናንና የሌሎችን ኢትዮጵውያን ጀግኖች አርበኞች ታሪክ ጠብቆ ያቆየው እንደ ቀኝ ጌታ ዮፍታሔ ንጉሴ አይነቱ አማራ ነው።
ዐፄ ዮሐንስ ምንም እንኳ ጎጃምና ወሎን ቢጨፈጭፉም መተማ ላይ ሰማዕት በመሆናቸው አማራው የሚያከብራቸውን ያህል በፋሽስት ወያኔዎች ዘንድ ክብር የላቸውም። አማራው መተማ ዮሐንስ የሚል ከተማ በስማቸው ሲጠራ ፋሽስት ወያኔዎች ግን በባለሟላቸው በራስ አሉላ ስም የተሰየመውን ትምህርት ቤት የትግራይን ሪፑብሊክ ለመመስረት ደደቢት በወረደው መለስ ዜናዊ ስም ለውጠውታል።
የኦሮሞ ብሔርተኞች ከሰሞኑ የአድዋን ድል ዋነኞቹን የጦሩ አዛዦችን ንጉሠ ነገሥት ዳግማዊ ምኒልክንና እቴጌ ጠሐይቱን ትተው የኦሮሞ ጀግና ፈረሰኛ ወታደሮች ድል እንደሆነ አድርገው እየተናገሩ ናቸው። እንደሚታወቀው የአድዋ ጦርነት ጥሊያን የተጨፈጨፈበት ድል ነው። የኦሮሞ ብሔርተኞች እየነገሩን ያለው ይህንን የጥሊያን ጭፍጨፋ ያካሄዱት የኦሮሞ ፈረሰኛ ወታደሮች ናቸው የሚል ነው። ጥሩ። ይህንን የሚሉትን የኦሮሞ ብሔርተኞች አኖሌና ጨለንቆ ላይ ተካሄዱ ለሚሏቸው ጦርነቶች ተደረገ ለሚሉት ጭፍጨፋ ግን ኃላፊነቱን የዳግማዊ ምኒልክ ያደርጉታል።
በታሪክ ሞቅ ሲል በማንኪያ፤ ሲቀዘቅዝ በእጄ አይሰራም። በአድዋ ድል የኦሮሞ ፈረሰኛ ወታደሮች ከሆነ የአርሲና የሐረር «ጭፍጨፋ» የተባለውንም የፈጸሙት እነዚህ የአድዋ ድል ባለቤት የተደረጉት ጀግና የኦሮሞ ፈረሰኛ ወታደሮች ናቸው። ለአድዋው ድል ሲሆን እውቅናው ከሁሉ በላይ ለጀግና የኦሮሞ ፈረሰኛ ወታደሮች፤ እነኚህ ወታደሮች አርሲና ሐረር ባካሄዱት የማስገበር ዘመቻ ደረሰ ለሚባለው «ጭፍጨፋ» እና «ቅኝ ግዛት» ግን ተጠያቂው ዳግማዊ ምኒልክ ሊሆኑ አይችሉም!
«ሰውን ሲወዱ ከነንፍጡ እና ልጋጉ ነው» ይላል ያገሬ ሰው። በአድዋ ላይ የተመዘገበውን ድል ከሁሉ በላይ የኦሮሞ ጀግና ፈረሰኛ ወታደሮች የሰጠ አንድ ሰው፤ ከአድዋው ድል ጥቂት አመታት በፊት እነዚሁ የኦሮሞ ፈረሰኛ ወታደሮች በአርሲና ሐረር ያደረሱትን «ጭፍጨፋም» የራሱ ወገን የሆኑ ሰዎች ያደረሱት መሆኑን አምኖ ትክሻውን ደልደል በማድረግ መቀበልና ተፈጸመ ላለው ጭፍጨፋም ተጠያቂ ማድረግ ካለበት እነሱኑ ነው እንጂ ሌላ አካል ተጠያቂ ማድረግ የለበትም።
ስለዚህ ዛሬ የኦሮሞ ብሔርተኞች በአድዋው ድል እውቅና እየሰጧቸው ያሉት የኦሮሞ ፈረሰኛ ወታደሮች ከአድዋ ድል ጥቂት አመታት በፊት እነዚሁ የኦሮሞ ወታደሮች ሐረርና አርሲ ላደረሱት «ጭፍጨፋ» እና «ቅኝ ግዛት» ዳግማዊ አጤ ምኒልክ ተጠያቂ የሚሆኑበት አመክንዮ ሊኖር አይችልም! ስለሆነም ወይ የአድዋውን ድልም እንደ አኖሌውና ሐረሩ ጭፍጨፋ ሁሉ ለምኒልክ ተውት አልያም በነዚሁ አድዋ በዘመቱ የኦሮሞ ጀግና ፈረሰኞች የተካሄደውን የአርሲና የሐረሩ ጭፍጨፋ ያላችሁትንም እንደ አድዋው የጥሊያን ጭፍጨፋ ሁሉ ኃላፊነቱን በመውሰድ ተጠቃለሉትና ምኒልክን ለቀቅ አድርጓቸው Otherwise it is pure hypocrisy to make such a sudden U-turn 213
No comments:
Post a Comment