ኢትዮጵያ በረዥም ዘመን ታሪኳ አባጣና ጎርባጣዉን የታሪክ ምንጣፍ አልፋ ዛሬ ደርሳለች፡፡ ይህን የታሪክ አካላችንን ኢትዮጵዊያን ከፊሉን በንጉሳዊያን ዜና መዎዕል ፤ እንዲሁም ሌሎች የታሪክ ድርሳናትን አቆይተዉናል፡፡ ከኢትዮጵያዊያን በተጨማሪም ኢትዮጵያን የጎበኙ አሳሾችም ሆነ ሚሺነሪዎቸ ስለኢትዮጵያ ታሪክ ጥናቶቸን አድርገዎል፡፡ ነገር ግን ከምእራብያዊያን መስፋፋት ጋር በተገናኘ ከፊሎች የዉጭ ሃገር ጸሃፊዎች የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ ያልሆነ ህዝብ ፤ የባሪያ ፍንገላ የሚከናወንበት ፤ በሃገሩ ንጉሶችችቆና የሚደርስበት የእራሳቸዉን ሃገር በወረሪነት በመምጠት ሊታደጋቸዉ እንደሚገባ ወትዉተዎል፡፡ ይህ የታሪክ ትርክት እዉነትነት ቢኖረዉ እንኳን በጸሃፊዎች ድብቅ አጀንዳ ምክንየት ተጋኖና ተዘብቶ እንደሚቀርብ መረዳት አያዳግትም፡፡
ታዲያ እነዚን የመሳሰሉ የታሪክ ጸሃፊዎች የጻፉትን የታሪክ መጸሃፈት በመያዝ ነዉ አንዳንድ ልሂቃን እንወክለዎለን የሚሉትን ህዝብ ሲያወናብዱት የሚታዩት፡፡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ የተለያዩ ዘዉጌ ማህበረሰቦችን የተለያዩ እና እራሳቸዉን የቻሉ ብሄራዊ ህዝቦች በማድረግ ለዘመናት በጋራ የኖረዉን ህዝባችንን እያመሱት ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵዊያን በረዥም ዘመን ታሪካቸዉ በተለያዩ በጎም ሆነ አጥፊ መንገዶች ተጉዘዉ የተቀላቀሉ ህዝቦች ናቸዉ‹፡፡ ቢያንስ በነዚህ ሁለት ምክንያቶች የተዎሃድን ህዝብ መሆናችንን ማየት ይቻላል፡፡
ጦርነት
የኢትዮጵያ ታሪክ የጦርነት ታሪክ እንደሚበዛዉና ኢትዮጵያዉያንም ሰላም ያገኙበት ዘመን የቅንጦት ዘመናቸዉ እንደነበር አንጋፋዉ የኢትዮጵያዊነት አርአያ ፕሮፌሰር መስፍን በመጽሃፋቸዉ (መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ) ይገልጻሉ፡፡ ኢትዮጵያዊያን አንድ ጊዜ እርስ በእርሳቸዉ ሌላ ጊዜ ከወራሪዎችና ከተስፋፊዎች ጋር የሚያደርጎቸዉ ጦርነቶች የሰላም ህይወትን ቅንጦት እንዲሆን አድጎታል ፡፡ በእርስ በእርስ ጦርነቶች ጊዜ በጦርነት ያሸነፈዉ ወገን ተሸናፊዉን በምርኮ በመያዝ ፡ ምርኮኛዉ ካቆየ በሆላ የራሱን ባህልና ቋንቋ እንዲላመድ አድርጎ የጎሳዉ አካል አድርጎ ይቀበለዎል፡፡ የቅርቦቹን ነገስታት ታሪክ ከተመለከትን ደግሞ በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱባቸዉን ተቀናቃኝ የልዑላን ቤተሰብ ለማለዘብ ሴት ልጆቻቸዉን በመስጠት ተቀናቃኞቻቸዉን ታማኝ ለማድረግ በሚፈጥሩት መላ ኢትዮጵያዊያን የመቀላቀል እድላቸዉ ሰፊ ነዉ፡፡ አንድ የንጉስ ልጅ ወደ ተቀናቃኙ መሳፍንት ስትሄድ ደንገጡሮቾን ጨምራ ብዙ ጋሻጃግሬዎች እንደሚኖራት ጥርጥር የለዉም ፤ ታዲያ ይህ ሁሉ የስኮዱ አባላት የቀቅልቅሉ አካል ናቸዉ፡፡
በሌላ መልኩ ኢትዮጵያዊያን እርስ በርሳችን ተናቁረን ተናቁረን የዉጭ ወራሪ ወይም ተስፋፊ ሲመጣ በጋራ የመከትንባቸዉ አጋጣሚዎች ከታሪካችን ማህደር ይመዘዛሉ፤ ይህ ማለት ደግሞ በየጎበዝ አለቃዉ የሚመራዉ የኢትዮጵያ ጦር ረዥሙን የዘመቻ ጉዞ ሲያካሄድ በሚንቀሳቀስባቸዉም ሆነ ስንቁን ለመቆጠር በሚያርፍባቸዉ አካባቢዎች ከአካባቢዉ ህዝቦች ጋር የመቀላቀል እድሉ ሰፊ ነዉ፡፡ ይህ ጉዳይ ክብደት የሚሰጠዉ ኢትዮጵያዊያን በተደጋጋሚ ወረራዎች ይሞከሩብን ስለነበረ ነዉ፡፡
በቅርብ ጊዜ ታሪካችን እንኳን ብንመለከት በኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት መቆያነት ያገለገሉት አዘዞ (ጎንደር)፡ አሰብና ነገሌ ቦረናን የመሳሰሉ ቦታዎች የኢትዮጵያዊያን ቅልቅልነት የሚያሳዩ ቦታዎች ናቸዉ፡፡
ገበያ
የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆነዉ ተማራማሪዉ ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን ታላቋ ኢትዮጵያ በሚለዉ መጽሃፋቸዉ ኢትዮጵያ የህዝቦችና የባህሎች ሙዚየም መሆኖን ጠቅሶ ኢትዮጵያዊያን ህዝቦች በጋራ የሚወራረሶቸዉ በጣም ብዙ ነገሮች በመኖራቸዉ ኢትዮጵያዊያን የተለያዪ ህዝቦች ሳይሆኑ አንድ እንደሆኑ የቋንቋ፤ ባህልና እሴቶች ዉርርሶችን እያጣቀሱ ያብራራሉ፡፡ ኢትዮጵያዊያን አሞሌ ጨዉ፤ ቡና፡ ሸማ፡ እደ ጥበቦች፡ የእርሻ ቁሳቁሶችና የመሳሰሉትን በሲራራ ነጋዴዎቻቸዉ አማካኝነት በጋራ የሚገበያዩባቸዉ ትላልቅ ገበያዎች እንደነበሩ ይጠቅሳሉ፡፡ በእነዚህ ትላልቅ ገበያዎች ለመሳተፍ ከኢትጵያ ሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ ጫፍና ከምዕራብ ጫፍ እስከ ምስራቅ ጫፍ ሁሉም ያለዉን ይዞ የሌለዉን ለማምጣት ስለሚሄድ ሃገረዊ ቅልቅል ለመፈጠሩ አንዱ ማሳያ ነዉ፡፡