Followers

Thursday, October 2, 2014

አስጠራዡ ሲጠረዝ!!!

የዉጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት በኢኮኖሚ ድፕሎማሲ አተኩሮ እንደሚሰራ እና ባላ ሃብቶችን ከየሃገራቱ  እንደሚስብ መደስኮር ከጀመረ ሰነባብቶል፡፡ ነገር ግን ይህ እቅድ ከተስፋ ባለፈ መሬት ላይ ለመውረድ ፈርጀ ብዙ ችግሮች ይኖሩበታል፡፡ አንዱ ምክንያት ደግሞ መንግስት ብቃት ያለዉን ባለሙያ ከመቅጠር ወደ ብሄር ኮታ በመዉረድ ለብሄር ብሄረሰቦች ያከፋፍላል፡፡ ይህም ቢሆን ሕወሃት/ኢህአዴግ ያለዉን ረጅም እጅ እየተጠቀመ በየሃገራቱ ያሉ አምባሳደሮች ሳይሆኑ ከታች የተቀመጡ የህወሃት ሰዎች መዘዉሩን ይዘዉታል፡፡
በመካከለኛዉ ምስራቅ ያሉ ኤምባሲ ሰራተኞች ለስደተኛዉ ወኪል መሆናቸዉን እረስተዉ በእጅ አዙር የጉዞ ወኪል በመክፈት በሴት እህቶቻችን ላብ በመነገድ ላይ ይገኛሉ፡፡ የኤምሲዎችን እርዳታ  ለመጠየቅ ወደ ኤምባሲዎች በር የሚሄዱ ኢትዮጵያዊያንን የቦንድ ግዢ እንዲያደርጉ ይጠየቃሉ በአንጻሩ ግን በኤምባሲያችን በር ላይ በአረብ ወሮ በሎች ሴት እህታችን ስትደፈር የወያኔ አምባሳደሮች የሚያዩበት አይን የሚሰሙበት ጀሮ አልነበቸዉም፡፡
ከሶስት አመት በፊት በዋሽንግተን የኤትዮጵያ ኤምባሲ ባልደረባ (ዲፕሎማት ለማለት ቃሉ ስለማይመጥኑ ነዉ) የነበረች አንዲት ኢት ዮጵያዊት እጽ በማዘዋወር በለንደን አዉሮፕላን ማረፊ እጅ ከከፈንጂ ተይዛ ዘብጥያ ወርዳለች ፤ ሰሞኑን እዚያዉ ዋሽንግተን በሰላማዊ ሰልፈኛ ኢትዮጵያዊያን ላይ ሶስት ጥይት ተኩሶ የሳተዉ ሰዉ ተጠርዞ ወደኢትዮጵያ እንዲመጣ ተደርጎል፡፡ ለካ መጠረዝ  በየተራ ለሁሉም ይደርሳል፡፡

ሕወሃት/ኢህአዴግ የያዘዉን የዘር ፖለቲካ ወደ ጎን ብሎ  ሁሉን አሳታፊ የሆነ መንገድ ቢከተል የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲዉ ብቻ ሳይሆን የአገሪቱ ዚጎችም በሚወዶት ሃገራቸዉ መስራት እና ማደግ ስለሚፈልጉ ለውጡ እጥፍ ድርብ ነዉ፡፡