Followers

Saturday, March 21, 2026

ወድቃ በተነሳችው ባንዲራ ይዣችኋለሁ?

 

ወድቃ በተነሳችው ባንዲራ ይዣችኋለሁ?

 

ይኸን ይግባኝ የሚያሰሙት ከነፃነት በኋላ (ከአምስት አመት የጣሊያን ፋሺስት ዓመታት በኋላ) የወረራው ትዝታው ያላቸው ትውልዶች ይመስሉኛል፡፡  እና እኔም  ይኸን ለመጥቀስ የተገደድኩት ስለ ወያኔ ህገ-መንግስት ፤ የህገ-መንግስቱ ዋልታና ማገር የሆነው ብያኔው  የኢትዮጵያ ባለቤቶች ብሄር ብረሰሰብና ህዝቦች በማለት ለዜጎች ደንታ ቢስ የሆነው ህገ-መንግስት ዋቢ ማድረግ ስለፈለግሁ ነው፡፡

 

ዋናው ጉዳይ የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 43 ፤ ንኡስ አንቀፅ 2 የመልማት መብት በሚለው ስር ማናኛውም ዜጋ፤ ሲቪል ማህበረሰብ ፤ እንዲሁም ማንኛውም ባለድርሻ አካል በኢትዮጵያ በሚወጡ ህጎች ላይ ሃሳብ የመስጠት፤ የመምከር መብት ፤ የመደመጥ መብት እንዳለው ይደነግጋል፡፡ በሰኔ 2017 ፀድቆ ቅርቡ መተግበር የጀመረው የደረቅ ቆሻሻ  አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383_2017 Proc.No 1383-2025 Solid Waste Management and Disposal.pdf ላይ የፌስታል አምራች ኩባንያዎች ምንም እንኳን ባለድርሻ አካለል ብንሆንም ህገ-መንግስታዊ የመሳተፍ ፤ የመምከር መብታችን አልተከበረም የሚል ፅኑ ተቃውሞቸውን አቅርበዋል፡፡  ነገርግን ከህገ መንግስቱ በተጨማሪ የንገግድና ዘርፍ ማህበራት በመንግሰት ፖሊሲ ላይ የሚወያዩበትና ሃሳብ የሚያቀቡበት በንግድና ዘርፍ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 341-2003 Chambers of Commerce and Sectorial Association Establishtrient Proclamation No. 341/2003.የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 341/1995.የተደገፈ ነው፡፡

 

በምላሹ ስለ-ህገ መንግስታዊ መብት ጥያቄ ሃሳብን በሀሳብ ከመሞገት፤ የግል ባለሃብቱን የሚሻማቅቅ የካድሬ ድንፋታ መስማት በጣም ያሳምማል፡፡ ጉዳዩን መርምሮ ከመረዳትና በሃሳብ የበላይነት ከማሸነፍ ይልቅ ካድሬዋች ባለአደራ መንግስት (public choice theory-Public choice - Wikipedia) እኛ ነን፤ ከእኛ በላይ ለህዝብ እና ለአካባበቢ የሚቆረቆር የለም እያሉን ነው፡፡ ማስፈራሪያው ሲሰፋ ፤ እነዚህ ባለሀብቶች እየተጠቀሙት ያለው ዘመኑን ያልዋጀ ቴክኖሎጂ ነው፤ ኢትዮጵያን ያረጀ ቴክኖሎጂ ማራገፊያ እያደረጉት ነው፤ ሜዲያ እየገዙ አዋጁ ተራዝሞል ወዘተ እያሉ መንግስት ህግ እየሸረሸሩ ይገኛል ይላል ውንጀላው፡፡(465) ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 እና በድምጽ ብክለት እርምጃ አወሳሰድ ላይ ዉይይት ሲያደርግ - YouTube የግሌ አመለካከት የደረቅ ቆሻሻ አየያዝና አወጋገድ አዋጅ ከፖሊሲ ረቂቅ ሃሳብ እስከ ትግበራው ጉድለት ያለበት ነው፡፡ ለዚህ ደገሞ ዋና ማሳያው የዝግጅት ጉድለት ነው፡፡ ፖሊሲን በቁጥጥር (በደንብ ማስከበር) ብቻ እተገብራለሁ የሚል ድንዛዜ ያለበት ስርዓት ፤ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ዘንግቶል፤ አማራጭ ምርቶችንም ለማቅረብ አልተታሰበትም፡፡ ሱሪ በአንገቴ ነው፡፡ ቆጮም የሸንኮራ አገዳም ለአማራጭ ከረጢት ይውላሉ ከሚለው የካድሬ ወሬ በስተቀር አፍታቶ መሬቴት ላይ ወረደ ነገር የለም፡፡ እናም ትልቁን የአካባቢ ጥበቃ አጀንዳ የጨረባ ሆኖል፡፡ ፖሊሲን በቁጥጥር ማስከበር ወጪው ከባድ ነው፤ ለተቋጣጣሪ አካላትም የሙስና በር ይከፍታል፡፡ የመልካም አስተዳደደር ችግር መቆለል ማለት ይኸ ነው፡፡

የአካባቢ እንክብካቤ ህግም  ሆነ ምርጫን የማራዘም ህግ የህዝብ ተሳትፎ፤ የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ በግልፅ በህገ-መንግስቱ ሰፍሮል፡፡ በርግጥም ይኸን ምርጫም ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር  ማራዘም ያስፈልጋል ባይ ነኝ፡፡ ነፃ፤ ገለልተኛ እና ርትኡ ምርጫ ቀላል ነገር አይደለም፡፡ በኮቪድ የተራዘመ ምርጫ ዛሬ ኦሮሚያ፤ አማራና ትግራይ  ውስጥ ባልተሞላ የምርጫ ቅድመ ሁኔታ እንዴት ይሆል፡፡ በሚቀጥለው ጦማሬ በዚህ ጉዳይ እመለስበታለሁ፡፡


Wednesday, February 25, 2026

ጉደኛ ሺፈራዎች !! አብራሃም ለቤዛ

 ጉደኛ ሺፈራዎች !!



ሰሞኑን መጀመሪያ አንድ ቪዲዮ አየሁ ፤ አንዱ ሺፈራው ሚኒስተር ዴኢታ ተብየ (ጉራ ፈርዳ አስፈፃሚ) እስስ አሁን ፎርጂድ ካላችሁ መዝግበን እናልፋችሆለን ይላል፤ ሌላው ሺፈራው በጎዳ በር ለአደጋ ጊዜ መጠባበቂያ (በኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ አዋጅ ቁጥር 1386/2025 እና በደንብ ቁጥር 576/2025 መሰረት ) ደሃውን ከየትም አምጥተህ ትከፍላታለህ እያለ ነው፡፡


ጉደኛው1 ሺፈራው!!!
______________________

___________________________
ጉደኛው2 ሺፈራው!!!
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ……………..ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!
ውድ የባንካችን ደንበኞች፤
******
በኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ አዋጅ ቁጥር 1386/2025 እና በደንብ ቁጥር 576/2025 ሁሉም ባንኮች እና ማይክሮ ፋይናንስ ተቋማት ከሚሰጡት ብድርና ከዲጂታል ባንኪንግ የአገልግሎት ክፍያዎች ላይ በደንቡ ላይ በተቀመጠው ስሌት መሰረት ከደንበኞች ላይ ክፍያዎችን በመሰብሰብ በብሔራዊ ባንከ በተያዘው የኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ ፅ/ቤት ሂሳብ ገቢ እንዲያደርጉ ተደንግጓል፡፡
በመሆኑም ከየካቲት 1 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ ባንካችን ከሚሰጠው ማንኛውም አይነት መደበኛ ብድር ላይ የሚለቀቀውን መጠን 1% (አንድ በመቶ)፣ እንዲሁም በሁሉም የባንካችን የዲጂታል ባንኪንግ አገልግሎቶች ደንበኞች ከሚከፍሉት የአገልግሎት ክፍያ ላይ 5% (አምስት በመቶ) እየተጨመረ የሚሰበስብ እና ለኢትዮጵያ አደጋ ስጋትና ምላሽ ፈንድ ፅ/ቤት ገቢ የሚያደርግ መሆኑን በአክብሮት ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡
ለተጨማሪ መረጃ ደንበኞች ወደአቅራቢያቸው የሚገኝ ቅርንጫፍ በመሄድ ወይም ወደ 951 የደንበኞች አገልግሎት የጥሪ ማዕከል በመደወል መጠየቅ የሚችሉ መሆኑን እንገልፃለን።
*********
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
ሁሌም የሚተማመኑበት ባንክ!

Wednesday, February 4, 2026

ወልቃይት አማራ-ለቅሶችን አማራ ሰርጋችን አማራ ቋንቋች አማራ በአብራሀም ለቤዛ

 



ስለ ወልቃቴ ግዟት በመጀመሪያ ማንበብ የቻልኩት ከፕሮፌሰር ዓለም እሸቴ ነው፤

እናም ይኸ ግጥም መታሰቢያነቱ ለፕሮፌሰር ዓለም እሸቴ ነው፡፡

ወልቃይት አማራ-ለቅሶችን አማራ ሰርጋችን አማራ ቋንቋች አማራ በአብራሀም ለቤዛ

---------------------------------////--------------------------------

ወልቃይት ፀጋዴ  የአማራዎች ርስት፤

መልካ ምድርሽ ምሽግ  አይመች ለጠላት፤

ወዲያ ከጣሊያን ወዲያ ከደርቡሽ፤

ፍላፃው ይረገፋል  ገና በተራሮችሽ ፤

ወንዞችሽ ተገርተው ሲፈሱ ከሜዳው፤

ተከዜን ጨምሮ ሲሳይ ሆነው ሄደው፤

ሰሊጡና ጥጡ ሃብትሽብ በጉያሽ፤

ስርቶ አዳሪው መጥቶ ቤት የሰራብሽ፤

ወዲያ መዳረሻ  ከተከዜ ማዶ ከራማው ደብር ፤

ፀሎት ሚሰማው ለፈጥኖ ደራሽ ገብርኤል፤

በማህፀንሽ ይዘሽ አበው ገዳምሽን፤

አብረታንት ዋልድባ ቃልኪዳን ያለበት፤

የአባቶችሽ ፀሎት ጠብቆሽ ከመዓት፤

ትህነግ ወያኔ ስግብግነቱ አይሎ ፤

ወልቃይት ገሎ በገፍ አፈናቅሎ፤

ወልቃይት አማራም ጠፋ ጠፋ ሲሉት፤

ወልቃይት አማራ ፤

ለቅሶችን አማራ ሰርጋችን አማራ ቋንቋች አማራ አለና በኩራት፤

የትህነግ  ትዕቢት አስተነፈሰለት፤

ገና ይንሰራራል በሃብትና በእመነት ፤

ወትሮም አባቶቹ ያደሩ ናቸው በእመነት፤

ቋርፍ በልተው ያደረሱት ፀሎት፤

ፈጣሪ ይደርሳል መቼ ይወድቅና ፤

ያ የደም አባላ የማይካድራ ግፍ፤

የንፁሃን እልቂት መቼም አይረሳም ተበዳይ ሳይካስ፤

ትህነግ በሃጢያቶ መች መባዘኖ አበቃ፤

መሆን ስለማራት በሱዳን ተረድታ የጎበዝ አለቃ፤

ሳዳሙሴንም ላይታደጋት ወይም ጋዳፊ ላይመጣ፤

ሞችን እየጠራች  ይኸው ታጣጥራለች፤

Friday, January 30, 2026

ኖሮ ኖሮ ከሞት፤ ዞሮ ዞሮ አዙሪት በአብራሃም ለቤዛ

 


ኖሮ ኖሮ ከሞት፤ ዞሮ ዞሮ አዙሪት

በአብራሃም ለቤዛ

የሜሮን ጌትነትን ግጥም እያዳመጥኩ የፃፍኩት

------------------////----------------------

ያ ስዩም መስፍን  ባድሜ ተሰጠን ፤

የጦር ሜዳ ድሉን በአደባባይ ደገምን፤

ውጣና ተደሰት ዘምባባውን ይዘህ ፤

ተሸከርክና ጨፍር ፈንዲሻህን ደፍተህ፤

የሚል ሳክስ ነበር በቲቪው የነፋው፤

ዲጂታል ሳይበዛ ካድሬና ወረፋው፤

ይኸን ሳንረሳው በዚያኛው ዘመን፤

እነቶኔ ሆነው ከወያኔ ነፃ አውጭ፤

ተረታቸው ሆነ በረጂሙ ትግል ስላደሩት ውጭ፤

ጦርነት አውርደው ደም እንዳላፈሱ፤

በአንዴ እጥፍ ብለው ጲላጦስን ሆነው፤

እኛ መቼ ለኳስን ነው ግፋ በለው ናቸው ብለው አላከኩ ፤

ሰው እንዳለለቀ በነሱ ዳፋ ጦስ፤

እስክስ፤

ይኸው ታረቅን ኢትዮጵያ አሸነፈች፤

አራት ኪሎም አለች፤

ማንም ሳይጠየቅ የሞተ ተጎዳ፤

እንዲሆን ተረቱ የሀገሬው ፍዳ፤

ፕሪቶሪያ ሄደው ፤ሃላላ ተዝናንተው፤

ውስኪ እየተራጩ  አንሶላ ተጋፈው፤

ዛሬም ተመልሰው ይኸው አየናቸው ፤

ከአዙሪቱ ወድቀው፤