የተስፋዎ ምድር እስራኤል ዛሬ የተስፋ ምድር ሳትሆን ከ60ዓመት በፊት ዜጎቾ እንደጨዉ ዘር ተበትነዉ የሂትለርን ጭፍጨፋ ጭምር ለማስተናገድ ተገደዎል፡፡ ዛሬ እስራኤል መሰል ታሪኳን አስቀድማ ለመከላከል ለሚሰነዘርባት ጥቃት የምትወስደዉ እርምጃ ከእጥፍ በላይ ነዉ፡፡ የኒዉክለር መሳሪያ ባለቤት የሆነችዉስ ለማስፈራራት ሳይሆን ይቀራል፡፡ በጉልበት ለሚያምን ዓለም ጉልበት፡፡
ዛሬ እስራኤል ያሳለፈችውን የመከራ ዘመን ተራዉ ተከባብሮ መኖር ላልቻለ አገር ዜጋ ነዉ፡፡ በአገሩ መኖር ባለመቻሉ የተስፋዎን ምድር እስራኤልን ለመግባት የግብፅን የሲናይ በርሃ አቆርጠዉ የሚሄዱ የኤርትራ፣ ሱዳንና ኢትዮጵያ ስደተኞች በግብፅ ድንበር ጠባቂዎች እጅ ላይ ሲወድቁ ሰብዓዊነት የጎደለዉ አስከፊ ስቃይ ይጠብቃቸዎል፡፡ በጣም ዘግናኙ ደግሞ የበደዊን ጎሳዎች እጅ ላይ ከወደቁ ነዉ፡፡ የሰውነት ክፍሎቻቸዉ በማፊያ ስራ ላይ በተሰማሩ ተንቀሳቃሽ ዶክተሮች (ድምበር የለሽ ዶክተሮች አላልሁም) ኩላሊትና ጣፊያ እየወጣ ይሸጣል፡፡ ጎበዝ ይህን ዘግናኝ አጭር ፊልም ስታዩ (ማስፈንጠሪያዉን
በመጫን) ምን እንደሚሰማችሁ መገመት አያዳግትም፡፡ እኔን የተሰማኝ ሃዘንና ቁጭት ነው፡፡ ኢትዮጵያን የሁላችንም፣ዜጎች የሚኖሩባት፣ ስደትን የማይመርጡባት ምቹ አገር ማድረግ ይጠበቅብናል፡፡ ለዚህ ያበቃንን ዘረኛዉን የወያኔ መንግስት በመታገል፡፡ አበቃሁ፡፡
No comments:
Post a Comment