Followers

Sunday, September 6, 2015

ፈዉስ ያልተገኘለት በሽታ፤ ዘረኝነት







የኢፌድሪ መካላከያ ሚኒስትሩ አቶ ሲራጅ ፈጌሳ ባንድ ወቅት የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊት ከብሄር ብሄረሰቦች የተዉጣጣ ህዝባዊ ሰራዊት ነዉ ለማለት ብሄሮችን እየጠቀሱ ከእያንዳንዱ ብሄረሰብ ተዉጣጣ የሚሉትን በቁጥር አስቀምጠዉ ነበር፡፡ ነገር ግን የኢፌድሪ መከላከያ ሰራዊት ከፈንጅ ረጋጩ የበታች ሰራዊት ባለፈ የአመራር ቦታዉን የአንድ ቋንቋ (ትግርኛ) ተናጋሪዎች ብቻ እንደተቆጣጠሩት የአደባባይ ሚስጥር ነዉ፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ በሕወሓት/ኢሀአዴግ ሰራዊት 19 83 / ፈረሰ ብለን ብናስብ እንኳን ኢህአዴግ የገነባዉ የኢትዮጵያ መካላከያ ሰራዊት 23 አመታት ዉስጥ እንዴት ከትግሪኛ ቋንቋ ተናጋሪ ዉጭ ያለን የሰራዊት አባል ለከፍተኛ አመራር ማብቃት ተሳነዉ፡፡
ከላይ እንደ መንደረደሪያ የሆነኝን ሀሳብ ለማንሳት የተገደድኩት ሰሞኑን በጀርመን ድምጽ ራድዮን በተከታታይ በአሚሶም ጥላ ስር ከተሰማራዉ የኢትዮጵያ መከላካያ ሰራዊት የድሃዉ ኢትዮጵያዊ ልጆች የሚሰማዉ ሮሮ ነዉ፡፡ እነዚህ ወታደሮች ሙያቸዉ በሚጠይቀዉ ግዳጅ የተሰማሩ ቢሆንም በሰራዊቱ አመራራ ላይ ባላዉ የነቀዘ የሙስና ችግር ምክንያት መከላከያ የሚሰፍርላቸዉን ድርጓቸዉንም ሆነ ተያያዥ ጥቅማ ጥቅሞቻቸዉን እንደማያገኙ ይገልጻሉ፡፡ እንደ ሰራዊቱ አባላት ክስ ከሆነ በተሰማሩበት አስቸጋሪ ግዳጅ ዉስጥ ሊሞሉላቸዉ ከሚገቦቸዉ  ነገሮች ትንሹ እንደማይሟላላቸዉ ይገልጻሉ፡፡
በሰራዊቱ አመራር አባላት ላይ የሚታየዉ ቅጥ ያጣ የሙስና ችግር አመራሩን ባለ ሰማይ ጠቀስ ፎቅና ባላሃብት ያደረገ ሲሆን የበታች ሰራዊቱን ግን በምሬትና በተስፋ ማጣት ህይወቱን እንዲገፋ ምክንያት ሁኖል፡፡  
የኢፌድሪ መካላካያ  የሰላም ማስከበር ተልኮዎችን በመምራት የሚታወቁት የህወሓት/ወያኔ ታጋዮች በሄዱበት ሁላ በተጠናወታቸዉ ንቅዘት የሰራዊቱን ተስፋ እንዳጨለሙበት ነዉ፤ ሰላም ማስከበር ወይንም አለም አቀፈ ተልኮ ለህወሓት/ወያኔ የተተወ በሚመስል መልኩ በኢቦላ በሽታ የተጎዱ የምዕራብ አፍሪካ አገራትን ለመደገፍ ወደ ሴራሊዮን እና ላይቤሪያ የሄደዉን የኢትዮጵያ ህክምና ቡድን ሳይቀር ሻለቃ ፍስሃ ትኩ እና አቶ ህንጻ ሃዱሽ የተባሉ የህወሓት አባላት ናቸዉ የመሩት፡፡ 
ምን አይነት ልማታዊ ዲሞክራሲ ነዉ? እንዲህ አይነት ዘረኛ ስርዓት እንዴት ነዉ ብሄር ብሄረሰቦች የሚል ካባ የሚደርበዉ? ይህ ነገር ወዴት ይሆን የሚወስደን? ይህ መልስ የሚያሻዉ ጉዳይ ነዉ?



አብራሃም ለቤዛ

እግዚአብሄር ኢትዮጵያን ይባርክ!!!