Followers

Monday, January 23, 2017

አምባገነኖች ባሉበት የአገርም ክብር ከፍ አይልም፡፡


በአሃጉራችን አፍሪካ በሚጥጥየዎ ጋምቢያ ምርጫ በተደረገ ማግስት 22 ዓመት የገዙት መሪ ያህያ ጃሜህ ሽንፈታቸውን መቀበላቸው አጀብ አሰኝቶ ነበር፡፡ በዚህ አምባገነን መሪ የተገረሙትም አድናቆታቸውን ችረዎቸው ነበር፡፡ የጃሜህ ቃል ግን ቀናትን አልፎ ሳምንታት መቆየት አልቻለም ምርጫው ተጭበርብሮል ይጣራልኝ ብለው አረፉት፡፡
ምንም እንኳን የምርጫው ሂደት ከጅምሩ ነፃ እና ገለልተኛ አይደለም የአምባገነኑ መሪ ረጅም እጅ አለበት እየተባለ ቢብጠለጠልም፤ በተጨማሪም የኢኮዎስም ሆነ የአውሮፓ ህብረት የታዛቢዎች ቡድን ለመታዘብ ባይችሉም የጋምቢያ ተፎካካሪዎች ግን ልዩነታቸውን ወደ ጎን በማድረግ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ተጠናክረው ነበር ያህያ ጃሜህን የተፋለሙት፡፡
በድጋፍ ህዝባዊ ሰልፍ ቲያትራቸውን ለዓለም መንግስታት የሚተዉኑት ያያህ ጃሜህ በወሳኞ የምርጫ ቀን ይህ በድጋፍ ሲያስፈነድቃቸው የነበረ ህዝብ አይቀጡ ቅጣት ቀጣቸውና ድምጹን ከዝቅተኛ አመራር የመጣ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ዕጩው አዳማ ባሮው ሰጠ፡፡
ያህያ ጃሜህ በአፍሪካ እየተወገዱ እነዳሉት አብዛኞቹ ፕሬዜዳንቶች በመፈንቅለ መንግስተ የመጡ ሲሆን የእሳቸውም መጨረሻ ውርደትን ተከናንበው መሰናበት ሁኖል፡፡ እስቲ ያሳያችሁ 22 ዓመት በላይ ስንት ዓመት ሊገዛ ነው?
አምባገነኖች ባሉበት የአገርም ክብር ከፍ አይልምና፤ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዘዳንትም ቃለ መሃላ የፈፀመው በአገሪቱ ስታዲየም በጦሩ አጀብ በማርሻል ባንድ ታጅቦ ሳይሆን በስደት በሴኔጋል በሚገኘው የጋምቢያ ኤምባሲ ነው፡፡ በአንጻሩ የልዕለ ሃያሎ አሜሪካ የስልጣን ሽግግር በሰላማዊ መንገድ 250 ዓመታት በላይ መዝለቁ በቅናት ልብን ያበግናል፡፡ መንፈሳዊ ቅናት፡፡
አዳማ ባሮው ለአገራቸው መልካም ምኞት እንዳላቸው በበዓለ ሲመታቸው ላይ ተናግረዎል፡፡ የሃብት ክፍፍል ፍትሃዊ እንደሚሆን፤ ስልጣናቸውም ገደብ እንደሚኖረው፡፡ እንደ ቃልዎ ብያለሁ፡፡ የአፍሪካ መሪዎች ቃላቸውን አይጠብቁም ያያህ ጃሜህ በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን ለተገደበ ሰልጣን ዘመን እንደሚቆይ ቃል ገብቶ ነበር ፡፡

በአፍሪካችን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ምሳሌ የሚሆኑ አገሮች አሉ፡፡ ጋና፤ ቦትሰዎና፤ደቡብ አፍሪካ፤ ዛምብያ በምሳሌነት ይጠቀሳሉ በአንፃሩ ደግሞ በአብዛኞቹ የአፍሪካ አገሮች የስልጣን ሽግግሩ መቆራቆስ  እንደሆነ ቀጥሎል፡፡ ለዜጎች መፈናቀል ምክንያት ነው፡፡ መቼ ነው አፍሪካ ከዚህ አዙሪት የምትወጣዉ?