እንቦጭን ከጣና ወያኔን ከአፍር
ላይ ነቅለን የጣልን ለት፤
የባህርዳር ፈርጥሽ የአፋር ገሞራ አለት፤
ታትሞ ይቀራል በአለም-አቀፍ
መዝገብ ይሆናል ቅርስ ውበት፤
መቼ ይጎልና አሳውም ከጣና በከል
ወተቱ አፋር ቤት፤
ሕብረታችን ይታይ አንዱ ለአንዱ ይድረስ ፤
ዋጋ ያስከፍላል መታገስ እኛ
ዘንድ አስቲደርስ ፡፡
የማህበራዊ ልማት ልማት አጥኝዎች
ጥናቶቻቸውን ተደራሽነት ለመጨመር የገጠሩን ማህበረሰብ አሳታፊ የሆነ የጥናት መንገድ (Participatory Rural
Appraisal) መጠቀምን ይመክራሉ፡፡ እነዚህ የጥናት መንገዶች ተግባራዊ ማደረግ ለጥናታችን ግብዓት የሚሆነን መረጃ ማንበብና
መጻፍ ከማይችለው (However, literacy and numeracy are quite different) የማህበረሰብ ክፍል ለጥናታችን
ግብዐት የሚሆነንን መረጃ በአግባቡ ለማግኘት ያግዘናል፡፡ ለጥናታችን ግብዓት መረጃ ማግኘታችን ለጥናታችን የመፍትሄ አቅጣጫ ለማመላከት
የራሱ ጉልህ አስተዎጽኦ አለው፡፡
የገጠሩን ማህበረሰብ አሳታፊ
የሆነ የጥናት መንገድ (Participatory Rural Appraisal) ውስጥ ለወሳኝ ክስተቶች መረጃ ማግኛ ዘዴ (Timeline/Historical
Mapping) አንዱ ሲሆን የማህበራዊ ልማት ልማት አጥኝዎች በጥናታቸው አካባቢ ወደ ሆላ ተጉዘው ምን ምን ክስተቶች እንደነበሩ
የጥናቱ ተሳታፊዎችን የሚጠይቁበት መንገድ ነው፡፡
ከላየ ያለውን ሃተታ ያነሳሁት
በአፋር ክልል ላይ ስለተከሰተው “PROSOPIS” የተባለ አረም
የማህበራዊ ልማት አጥኝዎች የተቸገሩበትን ጉዳይ ስላየሁ ነው፡፡ ይህ
ዓረም ወያኔ እየተባለ በአፋር ነዎሪዎች ዘንድ የሚታወቅ ቢሆንም
አንዳንድ የማህበራዊ ልማት አጥኝዎች የጥናት ወረቀቶች ስመለከት ደርጊ
እያሉ በጥናታዊ ፅሁፋቸው ገልጠውታል፡፡ በአፋር የሚገኘው ወያኔ የተባለው አረም ከወያኔ ጋር አብሮ መጣ ብለው ስለሚያምኑ
እና ለ26 ዓመት በአፋር የሚገኝ ሆኖ በአርብቶ አደሩ የግጦሽ መሬት ላይ ወረራ በማካሄድ ለአርብቶ አደሩ የራስ ምታት ሆኖበታል፡፡
እንቦጭ በጣና ስንት ዓመት ሆኖት ይሆን?
ብዙ ብር ወጥቶባቸው ጥናት የምታደርጉ
ተቋማት ወደ እውነታው ተመለሱ፡፡ ጥናት ማድረግ ሌላ ፤ ፖለቲካ ሌላ ነው የእኔ መልዕክት፡፡
የመንግስት መገናኛ ብዙሃን ደግሞ በእንግሊዘኛ መጠቀም መርጠዎል (http://www.ena.gov.et/index.php/economy/item/11520-2017-02-05-17-32-42)፡፡
ምናልባት የመገናኛ ብዙሃን ሪፎርም እየተዘጋጀ ነው ተብሎ የተራገበለት ይኸን ይቀርፍ ይሆን? አብረን እናያለን፡፡ አብራሃም ለቤዛ