Followers

Friday, December 29, 2017

ሆዳም ፍቅር አያውቅ አሉ! ትናንት ሌላ ዛሬ ሌላ! አቻምየለህ ታምሩ(September 6 ·, 2017 )



ሆዳም ፍቅር አያውቅ አሉ! ትናንት ሌላ ዛሬ ሌላ! 


ቅማንትን ከዐማራ የሚለይ ቢኖር የሰይጣን ስራ ነው አላልኸንም እንዴ? 
የታለ ሀሞቱ የተኩራራህበት፣
ትናንትና እንደዚያ የደነፋህበት፣ 
ወይንስ ጨጓራ ነው ሀሞትም የነበት? 
አወ ቢሆን እንጂ የጨጓራ ክርም! 
ሀሞትማ ቢኖር መረር ይልህ ነበር። 
የታለች ልቢቱ፣ 
የደነፋችቱ፣ 
ሸፈናት ቀፈቱ? 
ቢሸፍናት እንጂ የቀፈት ኩይታህ፣
ልቢቱማ ብትኖር ትናንትን ባልረሳህ! 
አዎ ትናንትና! ትናንት እንበለው፣
ጀምበር ዘቅዘቅ ካለች የቀትሩም ታሪክ ነው፤ 
ትናንት ሌላ ዛሬ ሌላ! ሆዳም ፍቅር አያውቅ አሉ!