Followers

Friday, March 1, 2019

የመቀሌ ምሽግ! አብራሃም ለቤዛ


የመቀሌ ምሽግ!
ትህነግ/ህወሓት መቀሌ መሽጎ የተለያየ እቅድ እያወጣ የፌዴራል መንግስትን እጅ ለመጠምዘዝ እየሞከረ ነው፡፡ ጊዜ መግዣ የመሰለው አመራጭ ሁላ በመደመርና ትዕግስት ፍልስፍና ለተለጎመው ለአብይ አህመድ አስተዳደር ፈተና ሆኖል፡፡   ዛሬ ትህነግ/ህወሓት በሚመራው ክልል በጉልበት በጠቀለላቸው የወልቃይት እና ራያ አማራ ህዝብ ላይ እልቂተ እያደረሰ ይገኛል፡፡  መቀሌ የመሸገው ሃይል የመጨረሻ ካርዱን የትግራይ ህዝብን ጭዳ ለማድረግ የጦርነት ዝግጅት እደረገ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የመጣውን አቃፊ የለውጥ ጅማሮ ከጅምሩ እያጣጣለ ፤ትህነግ/ህወሓት  የማይዘውራት ኢትዮጵያ በአፍንጫ ትውጣ እያለ ነው፡፡ እኛ የገነባባት ኢትዮጵያ ካላከበረችን ፤ የትግራይ ሪፐፕሊክ መስርተን ከጎረቤት ኢትዮጵያ በተሸለ ከጎረቤት ሱዳን  ጋር  እንወዳጃለን እያሉ ነው፡፡  በ27 ዓመት ዘርፈው ያጎጎዙት ሃብት የትግራይ ሪፐፕሊክ ለመመስረት እና በእራሳችን ለመቋም ያስችለናል እያሉ ነው፡፡  ትህነግ/ህወሓት እራሱን የትግራይ ህዝብ ጠበቃ አድርጎ ሲያቀርብ ፤ በትህነግ/ህወሓት ቀንበር ስል ያለው የትግራይ ህዝብ ስሜቱን የሚገልፅበት ምንም ምርጫ የለውም፡፡ አምባገነኖች የእራሳቸውን ድርሰት በማንበብ ስለሚፅናኑ‹‹ ትህነግ/ህወሓት ከተነካ የትግራይ ህዝብ ቀፎው እንደተነካ ንብ ሆ ብሎ ይነሳል›› በሚል ቅዠት ውስጥ ገብተዋል፡፡
እቴጌ ጣይቱ   የጦርነትን  አስከፊነት  እና የነፃነትን አስፈላጊነት ከመቶ አመት በፊት  በዚህ ሀረግ ነበር የገለፁት፡፡‹‹ እኔ ሴት ነኝ ጦርነት አልወድም፡፡ ሆኖም ይህን ኢትዮጵያን የኢጣሊያ ጥገኛ (ውጫሌ ውል) የሚያደርግ ውል ከመቀበል ጦርነትን እመርጣለሁ››   ምንም እንኳን ጦርነት አስከፊ እና አጥፊ ቢሆንም አያቶቻችን የነፃነት ትርጉም ስለገባቸው ፤ በመካከላቸው ያለ ልዩነት ትተው፤ እንዲሁም ከንጉስ ሚኒሊክ ጋር ቅራኔ የነበራቸው የጦር አበጋዞች ሳይቀር ወራሪውን ሃይ ለመመከት ተሰልፈዎል፡፡ አፄ ሚኒልክም ‹‹ አመልህን በጉያህ ፤ ስንቅህን በአህያህ  ይዘህ ተከተለኝ ›› የሚል ጥሪ ነው አቃፊ የሆነና ይቅርታ ታከለበት አርቆ አሳቢነታቸው ያሳየ አዋጅ ያስተላለፉት፡፡
በውጫሌ ውል ሸፍጥ ምክያት የተቀሰቀሰው ጦርነት በመጀመሪያው አውደ ውጊያ  አምባላጌ ተራራ ላይ የተጠላትን ጦር ካስለቀቀ በኋላ ሁለተኛው ግንባር የመቀሌን ምሽግ ማስለቀቅ ነበር፡፡ የጠላት ጦር የእንዳ እየሱስን ተራራ ደጀን አድርጎ በመቀሌ ላይ የሰራው ምሽግ በግንብ ፤ ሽቦ አጥር የተጠናከረ ሲሆን ፤ በባዶ እግሩ የዘመተውን የሃበሻን ጦር ለመመከት የጠላት ጦር በፋሽኮ ጠርሙስ ስብርባሪ ምሽጉን አጠናከሮል፡፡  የመቀሌ  ምሽግን ለመስበር በወገን ጦር ላይ ከፍተኛ የሆነ የህይወት መስዋትነት አስከፍሎል ፡፡ በዚህ መሃል በከአውደ ውጊያው ያሉት እቴጌ ጣይቱ  ከጠላት ጦር የተገኘ የስለላ መረጃ ይደርሳቸዋል፡፡ ይኸውም የጠላት ጦር ከወገን ጦር አልፎ ከሚሄድ ምንጭ ውሃ እንደሚጠጣ፡፡
እቴጌ ጣይቱ ለጠላት ጦር የሚሄደው የምንጭ ውሃ የማገድ  እቅዳቸውን ምንጩ በማስጠለፍ እና ምንጩን በተጠናከረ የወገን ጦር በማስጠበው የጠላትን ጦር ከውሃ እቅረቦት ውጭ አደረጉት፡፡ የጠላት ጦር ለራሱም ሆነ ለጋማ ከብቶቹ ውሃ ማግኘት ስለልቻለ ፤ ተደላልድሎ የያዘውን ምሽግ ሊለቅ ችሎል፡፡ ሴት አያቶቻችን ከመቶ አመት በፊት እንደዚህ ብለጠት በተሞላበት ሁኔታ አመራር እየሰጡ የአገርን ነጻነት ጠብቀዎል፡፡ እቴጌ ጣይቱ የወገን ጦርን ስንቅ በበላይነት እያስባበሩ ከአንድ ሺ ኪሎ ሜትር ባለይ በእግር ተጉዟ ለውጊያ የሚሰለፍ ሰራዊት ማፍራት ችለዎል፡፡
ዛሬም በኢትዮጵያ በመቀሌ የመሸገው  ትህነግ/ህወሓት በኢትዮጵያ ለይ ያቀደውን የጦርነት እቅድ የሚያከሽፍ እንደ ጣይቱ ያሉ ብልህ የዘመናችን ሴቶችን እንሻለን፡፡  ሴቶች የጦርነትን አሰከፊነት ያውቁታል ፤ የነፃነትን ጥቅምም እንደዚሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ጣይቱን ፈለግ በመያዝ በኢትዮጵያ የመጣውን የነፃነትት የእኩልነት የተስፋ ጉዞ በሙሉ ልብ ሊደግፉት ይገባል፡፡ ይኸ ማለት ያለፈውን የጭቋና ስርዓት ፤ አግላይ ስርዓት ለመመለስ በመቀሌ የመሸገው ስርዓት ማውገዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የትገራይ እናቶች የጦርነትን አስከፊነት በደንብ ያውቁታል፡፡ ትህነግ/ህወሓት ትግራይ ተደፍራለች ፤ ተከባለች ለሚለው ጥሪ  ትህነግ/ህወሓት ሰከን ብሎ በእኩልነት ላይ ለምትመሰረት ኢትዮጵያ ተገዢ እንዲሆን ሊያሳስቡት ይገባል፡፡
‹‹የጎበዝ እናት ታስታውቃለች
፤አፋፍ ላይ ሆና በለው ትላለች››
የዘመናችን ሴቶች /እናቶች ከጦር ሜዳ ውለው የሞራል  ሆነ የአካል ስንቅ   መስጠት ላይጠበቅባቸው ይችላል፡፡  የሞራልም ሰንቅ ማዘጋጀትም ሆነ የአካል ስንቅ ማዘጋጀት  ፤ ምናልባትም ዘመናዊ  መንገድ  መስራት አስፈላጊ ስለሆነ፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ሴቶች/እናቶች  አበክረው ስለ ሰላም  መስበክ ይኖርባቸዋል ፡፡ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ሰላም፡፡ አንዱ አንዱ ደፍጥጦ፤ ጭጭ አድርጎ የሚመጣ ሰላም  (Like the peace maker bomb) ሳይሆን በመከባበር የሚመጣ ሰላም፡፡ አርቲስ ማሪቱ ለገሰ  ስለ ሰላም ጥሩ አድርጋ ተጫውታለች፡፡ 
ሰላም ሰላም ቢሉት  ሰላም ለአፍ ይሞቃል፤ 
በትግል ያልተገኘ ከጦርም ይልቃል ፤
የሽንፈት ሰላም ግን ከሽብር ይከፋል፤
የሽንፈት ሰላም ግን ከሽብር ይከፋል፡፡
የኢትዮጵያ ሴቶች/እናቶች  የትግራይ  ሴቶች/እናቶች  ስለ ሰላም መስበክ አለባቸው፡፡ የተገኘውን መድረክ መጠቀም አለባቸው፡፡  የሰላም ሚኒስቴር  አቋቁመናል፤ አስር ሴት የካቤኔ ሚኒስቴር ሰይመናል፤ ወዘተ፡፡ ሴቶች ስለ ሰላም በተግባር አሁኑኑ ያስፈልጋል፡፡




Tuesday, February 12, 2019

የመስኩ ላይ ቁርሾ! !!!ጃኖ Mengistu Zegeye



ሲጀምሩ ፤
ሁለቱም ቆርኬዎች ፤
አብረው ከኖሩበት ፤
ከሚያምረው መስክ ዳር ፤
እየጋጡ ነበር ፤
ከጨፌው ማሳ ላይ ፤ እየፈነደቁ ፤
ድንገት ሳይታሰብ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ወዳጅ ዘመድ መስለው ፤ ወደዚያ ዘለቁ ።
ቆርኬዎቹ ዘንተው ፤
ሳር ከሚግጡበት ፤
ደረሱ ተኩላዎች ፤ እየተፋነኑ ፤
ውሃ በሞላው አፍ ፤
የጨፌውን ማማር ፤
የጋጮቹን ገላ ፤ እያስተነተኑ ፤
የተኩላ መንጎች ፤
እንኳን በስጋቸው ፤
በተቆላለፈው ፣ በቀንዳቸው ቀኑ ።
ቆርኬዎቹ ጠግበው ፤ እስኪፈነጥዙ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ሳሩ ላይ ዋሉበት እየተሟዘዙ ።
ጀመሩ ቆርኬዎች ፤
በጥጋብ ጀመሩ ቀጠሉ ማስካካት ፤
ተኩላ ተናቃ ፤
በጨዋታ መሃል ሸር ለማስገባት ።
እንደዚህ አላቸው ተኩላ አባ ሴራ ፤
ከአያት ቅም አያቶች ታሪክ ስናጣራ ፤
አለቃ ሚሆነው የቆርኬዎች አውራ ፤
ታግሎ የጣለ ነው ፤
ተፋልሞ ሚገዛ ከገጠሙት ጋራ ።
ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ጠቅልሎ ፤
በቀንዱ ጀመረው ፤
ካንደኛው ትከሻ አንዱ ቆርኬ ዘሎ ።
ተኩላ ዳር ቆማ ፤
በጭብጨባ በአጀብ ፤
በል በለው ትላለች ፤ በክፋት አንደበት ፤
ጀግና ማለት በኛ ፤
የጫካው አርበኛ ፤ የሚዘመርለት ፋኖ እየተባለ ፤
ቀንድን በቀንድ ይዞ ፤
አንገቱን ጠምዝዞ መሬት ላይ የጣለ።
በግብግብ መሃል ፤
ገራገር ቆርኬዎች ፤
የተኩላን ፊሽካ ፤ ሰምተው ተናነቁ ፤
ቀንዳቸው ተጣልፎ ፤
ሁለቱም ሜዳው ላይ ዘፍ ብለው ወደቁ ።
በተጠለፈ ቀንድ ፤ በተገመደ አንገት ፤ ወድቀው ተጋጠሙ ፤
ራስ በራሳቸው በጀመሩት ትግል ማንም ሳያሸንፍ ሁለቱም ደከሙ ፤
በተኩላ ተንኮል አብሮ አደግ ቆርኬዎች ሞትን ተሸለሙ ።
ይህን ያየ ቆርኬ ፤
የወንድሞቹ ሞት ፤ በተኩላዎች ሴራ መሆኑን ተረድቶ ፤
ከሞቱበት ሳር ላይ ፤
ካለው ትልቅ ዛፍ ላይ ፤
እንዲህ ብሎ ጻፈ ብእሩን አውጥቶ ።
ሰፊ መስክ ሳለ ፤
ሰፊ ጨፌ ሳለ ፤ በዚህ በመንደሩ ፤
ያንዲት እናት ልጆች ፤
አንተ ወግድልኝ
እኔ ነኝ አለቃ ፤
እኔ ነኝ ባለ ሹም በሚሉት አምቡላ ስለተሳከሩ ፤
ሞሰቡ ሳይቸግር ፤
እኔ በሚል እሳት ፤ ተበላልተው ቀሩ ።

የመስኩ ላይ ቁርሾ! !!! ጃኖ Mengistu Zegeye

የመስኩ ላይ ቁርሾ! !!! ጃኖ Mengistu Zegeye
ሲጀምሩ ፤
ሁለቱም ቆርኬዎች ፤
አብረው ከኖሩበት ፤
ከሚያምረው መስክ ዳር ፤
እየጋጡ ነበር ፤
ከጨፌው ማሳ ላይ ፤ እየፈነደቁ ፤
ድንገት ሳይታሰብ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ወዳጅ ዘመድ መስለው ፤ ወደዚያ ዘለቁ ።
ቆርኬዎቹ ዘንተው ፤
ሳር ከሚግጡበት ፤
ደረሱ ተኩላዎች ፤ እየተፋነኑ ፤
ውሃ በሞላው አፍ ፤
የጨፌውን ማማር ፤
የጋጮቹን ገላ ፤ እያስተነተኑ ፤
የተኩላ መንጎች ፤
እንኳን በስጋቸው ፤
በተቆላለፈው ፣ በቀንዳቸው ቀኑ ።
ቆርኬዎቹ ጠግበው ፤ እስኪፈነጥዙ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ሳሩ ላይ ዋሉበት እየተሟዘዙ ።
ጀመሩ ቆርኬዎች ፤
በጥጋብ ጀመሩ ቀጠሉ ማስካካት ፤
ተኩላ ተናቃ ፤
በጨዋታ መሃል ሸር ለማስገባት ።
እንደዚህ አላቸው ተኩላ አባ ሴራ ፤
ከአያት ቅም አያቶች ታሪክ ስናጣራ ፤
አለቃ ሚሆነው የቆርኬዎች አውራ ፤
ታግሎ የጣለ ነው ፤
ተፋልሞ ሚገዛ ከገጠሙት ጋራ ።
ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ጠቅልሎ ፤
በቀንዱ ጀመረው ፤
ካንደኛው ትከሻ አንዱ ቆርኬ ዘሎ ።
ተኩላ ዳር ቆማ ፤
በጭብጨባ በአጀብ ፤
በል በለው ትላለች ፤ በክፋት አንደበት ፤
ጀግና ማለት በኛ ፤
የጫካው አርበኛ ፤ የሚዘመርለት ፋኖ እየተባለ ፤
ቀንድን በቀንድ ይዞ ፤
አንገቱን ጠምዝዞ መሬት ላይ የጣለ።
በግብግብ መሃል ፤
ገራገር ቆርኬዎች ፤
የተኩላን ፊሽካ ፤ ሰምተው ተናነቁ ፤
ቀንዳቸው ተጣልፎ ፤
ሁለቱም ሜዳው ላይ ዘፍ ብለው ወደቁ ።
በተጠለፈ ቀንድ ፤ በተገመደ አንገት ፤ ወድቀው ተጋጠሙ ፤
ራስ በራሳቸው በጀመሩት ትግል ማንም ሳያሸንፍ ሁለቱም ደከሙ ፤
በተኩላ ተንኮል አብሮ አደግ ቆርኬዎች ሞትን ተሸለሙ ።
ይህን ያየ ቆርኬ ፤
የወንድሞቹ ሞት ፤ በተኩላዎች ሴራ መሆኑን ተረድቶ ፤
ከሞቱበት ሳር ላይ ፤
ካለው ትልቅ ዛፍ ላይ ፤
እንዲህ ብሎ ጻፈ ብእሩን አውጥቶ ።
ሰፊ መስክ ሳለ ፤
ሰፊ ጨፌ ሳለ ፤ በዚህ በመንደሩ ፤
ያንዲት እናት ልጆች ፤
አንተ ወግድልኝ
እኔ ነኝ አለቃ ፤
እኔ ነኝ ባለ ሹም በሚሉት አምቡላ ስለተሳከሩ ፤
ሞሰቡ ሳይቸግር ፤
እኔ በሚል እሳት ፤ ተበላልተው ቀሩ ።