ኖሮ ኖሮ ከሞት፤ ዞሮ ዞሮ አዙሪት
በአብራሃም ለቤዛ
የሜሮን ጌትነትን ግጥም እያዳመጥኩ የፃፍኩት
------------------////----------------------
ያ ስዩም መስፍን ባድሜ ተሰጠን ፤
የጦር ሜዳ ድሉን በአደባባይ ደገምን፤
ውጣና ተደሰት ዘምባባውን ይዘህ ፤
ተሸከርክና ጨፍር ፈንዲሻህን ደፍተህ፤
የሚል ሳክስ ነበር በቲቪው የነፋው፤
ዲጂታል ሳይበዛ ካድሬና ወረፋው፤
ይኸን ሳንረሳው በዚያኛው ዘመን፤
እነቶኔ ሆነው ከወያኔ ነፃ አውጭ፤
ተረታቸው ሆነ በረጂሙ ትግል ስላደሩት እውጭ፤
ጦርነት አውርደው ደም እንዳላፈሱ፤
በአንዴ እጥፍ ብለው ጲላጦስን ሆነው፤
እኛ መቼ ለኳስን ነው ግፋ በለው ናቸው ብለው
አላከኩ ፤
ሰው እንዳለለቀ በነሱ ዳፋ ጦስ፤
እስክስ፤
ይኸው ታረቅን ኢትዮጵያ አሸነፈች፤
አራት ኪሎም አለች፤
ማንም ሳይጠየቅ የሞተ ተጎዳ፤
እንዲሆን ተረቱ የሀገሬው ፍዳ፤
ፕሪቶሪያ ሄደው ፤ሃላላ ተዝናንተው፤
ውስኪ እየተራጩ አንሶላ ተጋፈው፤
ዛሬም ተመልሰው ይኸው አየናቸው ፤
ከአዙሪቱ ወድቀው፤