Followers

Saturday, March 21, 2026

ወድቃ በተነሳችው ባንዲራ ይዣችኋለሁ?

 

ወድቃ በተነሳችው ባንዲራ ይዣችኋለሁ?

 

ይኸን ይግባኝ የሚያሰሙት ከነፃነት በኋላ (ከአምስት አመት የጣሊያን ፋሺስት ዓመታት በኋላ) የወረራው ትዝታው ያላቸው ትውልዶች ይመስሉኛል፡፡  እና እኔም  ይኸን ለመጥቀስ የተገደድኩት ስለ ወያኔ ህገ-መንግስት ፤ የህገ-መንግስቱ ዋልታና ማገር የሆነው ብያኔው  የኢትዮጵያ ባለቤቶች ብሄር ብረሰሰብና ህዝቦች በማለት ለዜጎች ደንታ ቢስ የሆነው ህገ-መንግስት ዋቢ ማድረግ ስለፈለግሁ ነው፡፡

 

ዋናው ጉዳይ የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 43 ፤ ንኡስ አንቀፅ 2 የመልማት መብት በሚለው ስር ማናኛውም ዜጋ፤ ሲቪል ማህበረሰብ ፤ እንዲሁም ማንኛውም ባለድርሻ አካል በኢትዮጵያ በሚወጡ ህጎች ላይ ሃሳብ የመስጠት፤ የመምከር መብት ፤ የመደመጥ መብት እንዳለው ይደነግጋል፡፡ በሰኔ 2017 ፀድቆ ቅርቡ መተግበር የጀመረው የደረቅ ቆሻሻ  አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383_2017 Proc.No 1383-2025 Solid Waste Management and Disposal.pdf ላይ የፌስታል አምራች ኩባንያዎች ምንም እንኳን ባለድርሻ አካለል ብንሆንም ህገ-መንግስታዊ የመሳተፍ ፤ የመምከር መብታችን አልተከበረም የሚል ፅኑ ተቃውሞቸውን አቅርበዋል፡፡  ነገርግን ከህገ መንግስቱ በተጨማሪ የንገግድና ዘርፍ ማህበራት በመንግሰት ፖሊሲ ላይ የሚወያዩበትና ሃሳብ የሚያቀቡበት በንግድና ዘርፍ ማህበራት አዋጅ ቁጥር 341-2003 Chambers of Commerce and Sectorial Association Establishtrient Proclamation No. 341/2003.የንግድና የዘርፍ ማህበራት ምክር ቤቶች ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 341/1995.የተደገፈ ነው፡፡

 

በምላሹ ስለ-ህገ መንግስታዊ መብት ጥያቄ ሃሳብን በሀሳብ ከመሞገት፤ የግል ባለሃብቱን የሚሻማቅቅ የካድሬ ድንፋታ መስማት በጣም ያሳምማል፡፡ ጉዳዩን መርምሮ ከመረዳትና በሃሳብ የበላይነት ከማሸነፍ ይልቅ ካድሬዋች ባለአደራ መንግስት (public choice theory-Public choice - Wikipedia) እኛ ነን፤ ከእኛ በላይ ለህዝብ እና ለአካባበቢ የሚቆረቆር የለም እያሉን ነው፡፡ ማስፈራሪያው ሲሰፋ ፤ እነዚህ ባለሀብቶች እየተጠቀሙት ያለው ዘመኑን ያልዋጀ ቴክኖሎጂ ነው፤ ኢትዮጵያን ያረጀ ቴክኖሎጂ ማራገፊያ እያደረጉት ነው፤ ሜዲያ እየገዙ አዋጁ ተራዝሞል ወዘተ እያሉ መንግስት ህግ እየሸረሸሩ ይገኛል ይላል ውንጀላው፡፡(465) ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በደረቅ ቆሻሻ አያያዝና አወጋገድ አዋጅ ቁጥር 1383/2017 እና በድምጽ ብክለት እርምጃ አወሳሰድ ላይ ዉይይት ሲያደርግ - YouTube የግሌ አመለካከት የደረቅ ቆሻሻ አየያዝና አወጋገድ አዋጅ ከፖሊሲ ረቂቅ ሃሳብ እስከ ትግበራው ጉድለት ያለበት ነው፡፡ ለዚህ ደገሞ ዋና ማሳያው የዝግጅት ጉድለት ነው፡፡ ፖሊሲን በቁጥጥር (በደንብ ማስከበር) ብቻ እተገብራለሁ የሚል ድንዛዜ ያለበት ስርዓት ፤ የባለድርሻ አካላትን ተሳትፎ ዘንግቶል፤ አማራጭ ምርቶችንም ለማቅረብ አልተታሰበትም፡፡ ሱሪ በአንገቴ ነው፡፡ ቆጮም የሸንኮራ አገዳም ለአማራጭ ከረጢት ይውላሉ ከሚለው የካድሬ ወሬ በስተቀር አፍታቶ መሬቴት ላይ ወረደ ነገር የለም፡፡ እናም ትልቁን የአካባቢ ጥበቃ አጀንዳ የጨረባ ሆኖል፡፡ ፖሊሲን በቁጥጥር ማስከበር ወጪው ከባድ ነው፤ ለተቋጣጣሪ አካላትም የሙስና በር ይከፍታል፡፡ የመልካም አስተዳደደር ችግር መቆለል ማለት ይኸ ነው፡፡

የአካባቢ እንክብካቤ ህግም  ሆነ ምርጫን የማራዘም ህግ የህዝብ ተሳትፎ፤ የባለ ድርሻ አካላት ተሳትፎ በግልፅ በህገ-መንግስቱ ሰፍሮል፡፡ በርግጥም ይኸን ምርጫም ካለው ነባራዊ ሁኔታ አንፃር  ማራዘም ያስፈልጋል ባይ ነኝ፡፡ ነፃ፤ ገለልተኛ እና ርትኡ ምርጫ ቀላል ነገር አይደለም፡፡ በኮቪድ የተራዘመ ምርጫ ዛሬ ኦሮሚያ፤ አማራና ትግራይ  ውስጥ ባልተሞላ የምርጫ ቅድመ ሁኔታ እንዴት ይሆል፡፡ በሚቀጥለው ጦማሬ በዚህ ጉዳይ እመለስበታለሁ፡፡