Followers

Tuesday, August 12, 2014

ኢህአዴግ ፣ እኛ እና ምዕራባዊያን (አብራሃም ለቤዛ)



Praising the traitor!!!
ባለራዩ  መሪ ፣ባለራዩ መሪ ፣ ዛሬ ድረስ የሚደመጥ የካድሬዎች የአፍ ማሞሻ ሀረግ ነዉ ፡፡  ከዚያማ ሌጋሲ ምናምን ፣ የማይሰቀጥሉት ነገር እንደሌለ ይነግሩን ነበር ፣ አሁን ድረስ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጭምር የሚሉት ነዉ፡፡
ሌጋሴ ወደ አማርኛ ስንገለብጠዉ ቀሪ መታዎሻ  ግለታሪክ የእኔም ፣ የአንቺም  በአጠቃይ የአገር መሪ የነበረ ብቻ ሳይሆን የተራዉ ሞችም ይኖረዎል፡፡ ዎናዉ ጉዳይ ምን አይነት ቀሪ መታዎሻ ታሪክ ጥለን አለፍን ነዉ፡፡
አቶ መለስ ዜናዊ  ምን  አይነት ቀሪ መታዎሻ ትተዉልን አልፈዎል ? ኢህአዴግን ከእሳቸዉ ዉጭ ማየት አንቺልም ለምን 21 ዓመት መርተዉታል፡፡ ኢህአዴግ በሙስና የነቀዘ ድርጅት ነዉ፣ አቶ መለስ በራሳቸዉ አንደበት ድርጅታቸዉ በሚመራዉ መንግስት ዉስጥ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.) የመንግስት ሌቦች እንዳሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልጸዉ ነበር፡፡
ኢህአዴጎች መጪዉ ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነዉ ይሉናል ምርጫ በመጣ ጊዜ፤ የኢህአዴጎች በመሬት ንግድ መክበር፤የፓርቲ ንግድ ማጦጦፍ፣ ከደሆች በተሰበሰበ ግብር በኢህአዲጋዊ ምቾት መኖር  ደሃዉ ኢትዮጵያዊ እነሱን ብቻ እንዲያኖኑር የተፈጠረ ስለሆነ ለእነሱ ብሩህ ነዉ፡፡
ኢህአዲጋዊ እስከሆንህ ድረስ እስከፈለገህ ትዘርፋለህ፣ የፈለግከዉንም መሬት በወረራ ትይዛለህ ፣ግፋ ቢል ኢህአዴጋዊነትህ ከቀነሰ በወረራ የያዝከዉን መሬት እንድትመልስ ይደረጋል፡፡ አንተ ላይ አንዳች ህጋዊ እረምጃ መዉሰድ ሌሎችን ኢህአዴጎችን ማስበርገግ ስለሆነ በማስተማር ትታለፋለህ ፡፡
ከኢህአዲጎች አንዱ በነበሩት ሰዉ፣ በአቶ መለስ ዜናዊ የበኩር ልጅ ፣ ሰመሃል መለስ ዜናዊ ስም የተመዘገበ አምስት ቢሊዮን ዶላር ቼክ (የህዳሴ አባይ ግድብን በእኛዉ በኢትዮጵያዊያን ተጀምሮ  በእኛዉ በኢትዮጵያዊያን የሚያስጨርስ ገንዘብ ያህል) በዉጭ አገር ባንክ እንደተንቀሳቀሰ ዶ/ር መኮንን ወንድሙ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ለእንግሊዝ ምክር ቤት አቤት ማለታቸዉ የአደባባይ ሚስጢር ነዉ፡፡ ይህ ጉዳይ ልማተዊ ነኝ ለሚል መንግስት አሳስቦት ማስተባበያ ሊሰጥበት  የሚገባዉ ሲሆን  ጀሮ ዳባ ልበስ መባሉ ያስገርማል፡፡
ምዕራብያዊያን  ለደሃ አገራት ከሚሰጡን እርዳታና ብድር በላይ ከደሃ አገራት ሙሰኛ ባለስልጣናት  የሚመዘበሩትን ሃብት በታማኝነት በማስቀመጣቸዉ የበለጠ ደሃ አገራት እንዲቆረቁዙ፣ ዜጎቹም ከሰዉ በታች እንዲኖሩ ምክንያት ሁነዎል፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደምሳሌ ስዊዘርላንድን (Switherland) ብንወስድ ካላት አመታዊ ምርት (GDP) አንጻር ከከፍተኛ ለጋሽ አገሮች ተርታ የምትመደብ ሲሆን በተቃራኒዉ እንደዚህ የምትጨነቅላቸዉ አገራት ዜጎች ገንዘብ ተዘርፎም ሲመጣ አንጀቶ አይጨክንም፤ በሚስጢር በባንኮቾ ታስተናግዳለች፡፡
ምዕራብያዊያን አገራት የዲሞክራሲ ስርዓት ቱርፋት ተጠቃሚዎች ቢሆኑም ለእኛ ለአፍሪካዊያን ግን የዴሞክራሲ ቱርፋት እንዲደርሰን እየረዱን አይደለም ፤ ምናልባትም እኛ አፍሪካዊያን ለአቅመ መብላት እንጂ ለአቅመ ዴሞክራሲ የደረስን አይመስላቸዉም፡፡ በእርግጥ እኛ አፍሪካዊያን (ኢትዮጵያዊያን) ሰልፋችንን ማስተካከል አለብን፡፡ ለዴሞክራሲ የሚደረግ ትግል ከምእራብያዊያን ጉልበት አያገኝም ፤ ዎናዉ ጉልበት ያለዉ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ነዉ፣ነገር ግን ልምድ ከነሱ መቅሰም ይቻላል፡፡
ምዕራብያዊያን ጥቅማቸዉን እስከተጠበቀ ድረስ ሰልፋቸዉን አይለዉጡም ፣ ነገር ግን  ህዝብ ከተነቃነቀ ፣ ህዝቡ የድል ችቦዉን ሊለኩስ ሲዘጋጅ በቅጽበት አቆማቸዉን ይለዉጣሉ፡፡ እዚህ ላይ አንድ ምሳሌ ማንሳት ይቻላል፡፡ የፈረንሳይ መንግስት በወዳጁ የቤንአሊ የቱንዚያ መንግስት ላይ በ2011 ዓ/ም (እ.አ.አ) ሕዝባዊ አመጽ በተነሳበት ሰዓት ቤንአሊን ለመታደግ አድማ በታኝ ተሽከርካሪዎች ለመላክ በተዘጋጀበት ሰዓት ፋታ የማይሰጠዉ ሕዝባዊ አመጽ በተቀጣጠለበት ሰዓት ቤንአሊ ሆየ እንደለመዱት በአዉሮፕላናቸዉ ወደ ፈረንሳይ ሲበሩ ምእራባዊቶ ፈረንሳይ የአየር ክልሎን ዘግታ  እንትንህን ላስ ብላቸዎለች፡፡
የዚህች መልዕክት አላማ ትግላችንን በህዝብ፣ለህዝብ፤ከህዝብ ብቻ ከሆነ አምባገነኑን የኢህአዴግ ስርዓት አሰወግዶ በምትኩ ሰፊ መሰረት ያለዉ ህዝባዊ ስርዓት ማምጣት እንደሚቻል ለመጠቆም ያህል ነዉ፡፡ ቸር እንሰንብት፡፡


ለአስተያየተዎ (anethiopian@yahoo.com)


ኢትዮጵያንና ህዝቦቾን እግዚአብሄር ይባርክ!!!!

Sunday, July 20, 2014

ኢትዮጵያዊነትን መረዳት ወይስ በተስፋፊዎች ቅዠት መነዳት(አብራሃም ለቤዛ)


ኢትዮጵያ በረዥም ዘመን ታሪኳ አባጣና ጎርባጣዉን የታሪክ ምንጣፍ አልፋ ዛሬ ደርሳለች፡፡  ይህን የታሪክ አካላችንን ኢትዮጵዊያን ከፊሉን በንጉሳዊያን ዜና መዎዕል ፤ እንዲሁም ሌሎች የታሪክ ድርሳናትን አቆይተዉናል፡፡ ከኢትዮጵያዊያን በተጨማሪም ኢትዮጵያን የጎበኙ አሳሾችም ሆነ ሚሺነሪዎቸ ስለኢትዮጵያ ታሪክ  ጥናቶቸን አድርገዎል፡፡  ነገር ግን ከምእራብያዊያን መስፋፋት ጋር በተገናኘ ከፊሎች የዉጭ ሃገር ጸሃፊዎች የኢትዮጵያን ህዝብ አንድ ያልሆነ ህዝብ ፤ የባሪያ ፍንገላ የሚከናወንበት ፤ በሃገሩ ንጉሶችችቆና የሚደርስበት የእራሳቸዉን ሃገር በወረሪነት በመምጠት ሊታደጋቸዉ እንደሚገባ ወትዉተዎል፡፡  ይህ የታሪክ ትርክት እዉነትነት ቢኖረዉ እንኳን በጸሃፊዎች ድብቅ አጀንዳ ምክንየት ተጋኖና ተዘብቶ እንደሚቀርብ መረዳት አያዳግትም፡፡
ታዲያ እነዚን የመሳሰሉ የታሪክ ጸሃፊዎች የጻፉትን የታሪክ መጸሃፈት በመያዝ ነዉ አንዳንድ ልሂቃን እንወክለዎለን የሚሉትን ህዝብ ሲያወናብዱት የሚታዩት፡፡ ኢትዮጵያ ዉስጥ ያሉ የተለያዩ ዘዉጌ ማህበረሰቦችን የተለያዩ እና እራሳቸዉን የቻሉ ብሄራዊ ህዝቦች በማድረግ ለዘመናት በጋራ የኖረዉን ህዝባችንን እያመሱት ይገኛሉ፡፡ ኢትዮጵዊያን በረዥም ዘመን ታሪካቸዉ በተለያዩ በጎም ሆነ አጥፊ መንገዶች ተጉዘዉ የተቀላቀሉ ህዝቦች ናቸዉ‹፡፡ ቢያንስ በነዚህ ሁለት ምክንያቶች የተዎሃድን ህዝብ መሆናችንን ማየት ይቻላል፡፡  
ጦርነት
የኢትዮጵያ ታሪክ የጦርነት ታሪክ እንደሚበዛዉና ኢትዮጵያዉያንም ሰላም ያገኙበት ዘመን የቅንጦት ዘመናቸዉ እንደነበር አንጋፋዉ የኢትዮጵያዊነት አርአያ ፕሮፌሰር መስፍን በመጽሃፋቸዉ (መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ) ይገልጻሉ፡፡  ኢትዮጵያዊያን አንድ ጊዜ እርስ በእርሳቸዉ ሌላ ጊዜ ከወራሪዎችና ከተስፋፊዎች ጋር የሚያደርጎቸዉ ጦርነቶች የሰላም ህይወትን ቅንጦት እንዲሆን አድጎታል ፡፡ በእርስ በእርስ ጦርነቶች ጊዜ በጦርነት ያሸነፈዉ ወገን ተሸናፊዉን በምርኮ በመያዝ ፡ ምርኮኛዉ ካቆየ በሆላ የራሱን ባህልና ቋንቋ እንዲላመድ አድርጎ የጎሳዉ አካል አድርጎ ይቀበለዎል፡፡ የቅርቦቹን ነገስታት ታሪክ ከተመለከትን ደግሞ በተለያዩ አካባቢዎች የሚነሱባቸዉን ተቀናቃኝ የልዑላን ቤተሰብ ለማለዘብ ሴት ልጆቻቸዉን በመስጠት ተቀናቃኞቻቸዉን ታማኝ ለማድረግ በሚፈጥሩት መላ ኢትዮጵያዊያን የመቀላቀል እድላቸዉ ሰፊ ነዉ፡፡ አንድ የንጉስ ልጅ ወደ ተቀናቃኙ መሳፍንት ስትሄድ ደንገጡሮቾን ጨምራ ብዙ ጋሻጃግሬዎች እንደሚኖራት ጥርጥር የለዉም ፤ ታዲያ  ይህ ሁሉ የስኮዱ አባላት የቀቅልቅሉ አካል ናቸዉ፡፡
በሌላ መልኩ ኢትዮጵያዊያን እርስ በርሳችን ተናቁረን ተናቁረን የዉጭ ወራሪ ወይም ተስፋፊ ሲመጣ በጋራ የመከትንባቸዉ አጋጣሚዎች ከታሪካችን ማህደር ይመዘዛሉ፤ ይህ ማለት ደግሞ በየጎበዝ አለቃዉ የሚመራዉ የኢትዮጵያ ጦር ረዥሙን የዘመቻ ጉዞ ሲያካሄድ በሚንቀሳቀስባቸዉም ሆነ ስንቁን ለመቆጠር በሚያርፍባቸዉ አካባቢዎች ከአካባቢዉ ህዝቦች ጋር የመቀላቀል እድሉ ሰፊ ነዉ፡፡ ይህ ጉዳይ ክብደት የሚሰጠዉ ኢትዮጵያዊያን በተደጋጋሚ ወረራዎች ይሞከሩብን ስለነበረ ነዉ፡፡
በቅርብ ጊዜ ታሪካችን እንኳን ብንመለከት በኢትዮጵያ ጦር ሰራዊት መቆያነት ያገለገሉት አዘዞ (ጎንደር)፡ አሰብና ነገሌ ቦረናን የመሳሰሉ ቦታዎች የኢትዮጵያዊያን ቅልቅልነት የሚያሳዩ ቦታዎች ናቸዉ፡፡
ገበያ
የኢትዮጵያ ወዳጅ የሆነዉ ተማራማሪዉ ፕሮፌሰር ዶናልድ ሌቪን ታላቋ ኢትዮጵያ በሚለዉ መጽሃፋቸዉ ኢትዮጵያ የህዝቦችና የባህሎች ሙዚየም መሆኖን ጠቅሶ ኢትዮጵያዊያን ህዝቦች በጋራ የሚወራረሶቸዉ በጣም ብዙ ነገሮች በመኖራቸዉ ኢትዮጵያዊያን የተለያዪ ህዝቦች ሳይሆኑ አንድ እንደሆኑ የቋንቋ፤ ባህልና እሴቶች ዉርርሶችን እያጣቀሱ ያብራራሉ፡፡ ኢትዮጵያዊያን አሞሌ ጨዉ፤ ቡና፡ ሸማ፡ እደ ጥበቦች፡ የእርሻ ቁሳቁሶችና የመሳሰሉትን  በሲራራ ነጋዴዎቻቸዉ አማካኝነት በጋራ የሚገበያዩባቸዉ ትላልቅ ገበያዎች እንደነበሩ ይጠቅሳሉ፡፡ በእነዚህ ትላልቅ ገበያዎች ለመሳተፍ  ከኢትጵያ ሰሜን ጫፍ እስከ ደቡብ ጫፍና ከምዕራብ ጫፍ እስከ ምስራቅ ጫፍ ሁሉም ያለዉን ይዞ የሌለዉን ለማምጣት ስለሚሄድ ሃገረዊ ቅልቅል ለመፈጠሩ አንዱ ማሳያ ነዉ፡፡