Followers

Saturday, May 22, 2021

ፓርቲ፤ መንግስትና ሀገርን መለየት ያስፈልጋል

 


የአቃቂ ቃሊቲ ክፍለ ከተማ የወጣት ማሀበር ፅ/ቤት  ግቢ በብልፅግና ማስታወቂያ ደምቆለል፡፡ እኔም ዛሬ እንኳን ብዝሃ -ፓርቲ ስርዓት ለመገንባት  በምንተፋተፍበት  ሰዓት ፤ በምርጫ ዋዜማ  የመንግስት ተቋማት ፤የከተማውን ወጣት የሚወክል መስሪያ ቤት በብልፅግና ማስታወቂያ ማሸብረቁ ግርምት ፈጥሮብኛል፡፡ ገዢ ፓርቲ መሆን ማለት ከጠቅላይነት  አባዜ መቼ ነው የምንላቀቀው ስል ለራሴ የማልመልሰው ጥያቄ  መለስሁ፡፡  ኢህአዴግ በገጠር  ማዳበሪያና ምርጥ ዘር ፤ የእርዳታ እህል ሳይቀር የሚሰተው ለአባላቱና ለደጋፊዋቹ  ነው፤ ማይክሮ ፋይናንስ ጠቋማት በከተማ የሚደራጁት ደጋፊያቸውንና አባላቸውን ነው እያልን ክፉኛ ወቀስነው፡፡   ኢህአዴግ አውራ ፓርቲ ሆኖ አብጦ ያካሄዳቸው አምስት ምርጫዋች በሙሉ  (ከምርጫ 1997 ዓ/ም ውጭ) ምርጫ ሳሆኑ ኢህአዴግ  ለይስሙላ የሚያካሄዳቸው ፤ ዳኛውን የምርጫ ቦርድ  በቁጥጥር ስሩ አውሎ ወደ ምርጫ ውድድር የሚገባበት የይስሙላ ምርጫዋች እንደነበሩ የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡

ዛሬ ኢህአዴግን  በህዝባዊ አመፅ ሸኝተን ከኢህአዴግ  ታድሰን ወደ ብልፅግና ፓርቲ  አድገናል፡፡ የአጋረችን የኢትዮጵያን ትንሳኤ  ለማብሰር በኢትዮጵያዊያን ህዝብ ድምፅ የኢትዮጵያ የዴሞክራሲ ግንባታ የመሰረት ድንጋይ እንተክላለን ብሎ ቆርጦ የተነሳው ብልፅግና ፓርቲ ግን በአደባባይ እየሰራ ያለው  ከኢህአዴጋዊ አውራ ፓርቲ  እንቅስቃሴ ተለይቶ የሚታይ አይደለም፡፡   ኢህአዴጋዊ አውራ ፓርቲ  በመሪው ግለሰብ ተክለሰውነት ግንባታ ተጠምደው ፤ ተከታይ አመራር ማፍራት ተስኖቸው ፤ መሪው በሞተ ማግስት ተከታይ  (ተደማጭ አመራር ) ማፍራት ተስኖቸው በመጨረሻ የአቶ ሃይለማርያምን  “ስልጣን በቃኝ    ውሳኔ አስከትሎል፡፡  የብልፅግና ፓርቲ  ሊቀመንበር ዶ/ር አብይ አህድ  ከኢህዴግ ልምድ ባልተለየ  ፓርቲውና አብይ አህመድ እንዲቆራኙ ፤ አብይ አህመድ ከሌለ ብልፅግና የለም እስከሚመስል ድረስ እየተሰራበት ነው፡፡ የብልፅግናን የምርጫ ቅስቀሳ ቢልቦረርዶች መመልከት በራሱ  ለዚህ ድምዳሜ ማስረጃ ይሆናል፡፡ በኢዲስ አበባ እና በሌሎች ክልሎች የተተከከሉ ቢልቦርዶች  “በዶክተር አብይ ጥላ ስር የተሰበሰብን  ችግኝ እጩዎች ነን ምረጡን” የሚል  መልዕክት ይዘዋል፡፡

 አውራ ፓርቲ  እያበጠ እያበጠ  ሄዶ አምባገንን  እየሆነ የመሄድ እድሉ የሰፋ ነው ፡፡ በአገራችን በየጊዜው እየፈነዳ ያለው የሰላም መደፍረስ እና  የአካባቢያችን  ጂኦ-ፖለቲካ  ግጭት  በእንቅርት ላይ ጀሮ ደግፍ እንዲሉት  የምርጫ ፉክክሩ  ላይ   የራሱን ጥላ አጥልቶበታል፡፡  ምርጫ  ቦርድ ያወጣው የተመዝጋቢዎችን ቁጥር ተስፋ ሰጭ ቢሆንም፤ የኢትዮጵያ ህዝብ ግን መጭወን ምርጫ የሚያካሄድበት ድባብ በራሱ ነፃ ምርጫ ላይ ተፅኖ አለው፡፡ ዶክተር አብይ አብይ አህመድ  ስለ ህገ-መንግስታዊ  ለውጥ ሲጠየቁ ብልፅግና ህገ-መንግስታዊ  ማሸሻያ ለማድረግ በዴሞክራሴያዊ ምርጫ  ከኢትዮጵያ ህዝብ ጋር ቃል -ኪዳን ማሰር አለበት  (መመረጥ) ያሉት  ቃል በብልፅግና ፓርቲ ደጋፊዎች እና የመንግስት መዋቅር በያዙት  እኩል የሚደገፍ ሃሳብ ከሆነ  የምርጫ ሂደቱ የመበለጠ አሳታፊ፤ ታማኝና ዴሞክራሲያዊ ማድረግ ያስፈልጋል፡፡

ተወዳዳሪ ፓርቲዎች በተጨባጭ  በሀገራችን ፓርቲ (ገዢ ፓርቲ) ፤ መንግስትና ሀገር የሚለው የተቀላቀለ ሃሳብ መሆኑን ተረድተው የምርጫ ቅስቀሳቸውንም ከዚህ አረዳድ መቅረጽ ይኖርባቸዋል፡፡  ገዢው ፓርቲ አባላቱንና ደጋፊዎቹን የሚያሰባስበው የመንግስትን መዋቅር በመጠቀም የሀገርን ሃብት ኢ-ፍታሃዊ በሆነ መንገድ በማከፋፈል ነው፡፡  የአዲስ አበባን የቤት ችግር ለመቅረፍ የተጀመረው ፕሮጄክት በአዲስ አበባ  ለገዢው ፓርቲ  አባላት በማከፋፈል መጠናቀቁን ጥናታዊ ሪፖርቶች አማክተዋል፡፡ በተቃራኒው  ተወዳዳሪ ፓረቲዎች አባላትና ደጋፊዎቻቸው ፓርቲያቸውን ለማደራጀትም ሆነ ለምርጫ ቅስቀሳ የሚሆን የሀብት ምንጭ የሚሆን ሃብት  ማዋጣት አለባቸው፡፡ ገዢው ፓርቲ  በፓርቲ አይዲዮሎጂ ያሰባሰባቸው አባላትና ደጋፊዎች እንዳሉት ሁሉ ፤ ተወዳዳሪ ፓረቲዎችም   ውስጥ የፖለቲካ ተሳትፎን ለጠባብ የግል ፍላጎት መጠቀሚያ ለማድረግ የሚሳተፉ አይጠፉም፡፡ኢህአዴግን  ገገማ የሆኑ አባላቶቹ አስወግዶ ታክቲካል ለውጥ አድርጎ ብልፅግና በሚል የዳቦ ስም እያጠቃ ያለ ገዢ  ፓርቲ  ነው፡፡  ብልፅግና ከኢህአዴግ በባሰ መንገድ እራሱን  የኢትዮጵያ አዳኝ አድርጎ እየሳላ ያለ ፓርቲ ስለሆነ  አባላቱና ደጋፊዎቹ   ይኸንን   እምነታቸውን ለማስፈፀም የበለጠ  ኢ-ዴሞክራሲያዊ በሆነ መንገድ የመንግስትን መዋቅርና የሀገር ሃብት ለፓርቲያቸው እየጠቀሙ ይገኛሉ፡፡  ይኸነን ሁኔታ ለመለወጥ የብልፅግና ደጋፊዎችን  ማማለል እራሱን የቻለ የትግል ስልት ሆኖ መወሰድ አለበት፡፡

ተወዳዳሪ ፓርቲዎች የሀገር ውስጥ ደህንነት፤ የከተማ ልማት ፤ የትምህርት ልማት ፤የኢንዱስትሪ ልማት፤ የውጭ ጉዳይ ፖሊሲ  አማራጫቸውን ሲያቀርቡ በገዢው ፓርቲ ጥላ ስር ተጠልለው ፤ የፓርቲው መዋቅር ከገዢ ፓርቲነት ከተነጠለ የእነሱም ሕይወት ከአስትንፋሱ እንደሚነጠል ለሚያስቡ  በስም ብልፅግናዋች በተግባር ግን መዥገሮች ለሆኑ አባላትና ደጋፊዎች ማስተማመኛ መስጠት አለባቸው፡፡ ለእነዚህ መዥገሮች የሚሰጣቸው ማስተማመኛ (ይቅርታ) ተወዳዳሪ ፓርቲዎች አለን የሚሉት ደጋፊም ግምት ውስጥ ያስገባ መሆን አለበት፡፡  ጥቅም ፍለጋ የመጣ  ደጋፊ ያሰባሰቡ ፤ በተራችን “መንግስት ከሆን” ፤ ስልጣን ከአገኘን  ብለው የተሰባሰቡ ካሉም ይበተናሉ፡፡

ለመዢገር ብልፅግናዎች የሚሰጣቸው ማስተማመኛ እንደሚከተለው ሊቀርብ ይችላል፡፡

Ø  የእኛ  ፓርቲ  የህዝብ ድምፅ ቢያገኝና መንግስት ቢመሰርት ፤ በፓርቲ አባልነት የተሰበሰበ የፓርቲ ጥማጥቅም  (ቤት፤ መኪና፤ ሌሎች) መንግስት ስንሆን  በምናቋቁመው አጣሪ ኮሜቴ ተለይቶ ቢያንስ ቤት የሌላቸው ብልፅግናዎች የመንግስት ቤትን እስካልበለፀጉ ድረስ አይነጠቁም፡፡

Ø  የፖሊስ፤ የደህንነትና የመከላከያ ተቋማትን ማፍረስ ማለት አገርን ማፍረስ ማለት ስለሆነ፤ እነዚህ  ተቋማት ላይ ምንም እንኳን ያለን እምነታችን የተሞላ ባይሆንም  ፤እነዚህን ተቋማት እኛ ተወዳዳሪዎች እነዚህ ተቋማት የበለጠ ፕሮፌሽናል ኢትዮጵያዊ ተቋማት እንዲሆኑ እንሰራለን እንጂ የብልፅግና ወታደር ብለን የኢህዴግን ስህተት አንደግምም በማለት ማረጋጋት ያፈልጋል፡፡

Ø  የእኛ ፓርቲ ቢያሸንፍ  የምንገነባው ዴሙክራሲያዊ ስርዓት ሀገር በቀል  ሆኖ ፤ ብዙሃን ራሳቸውን የሚሳስተዳድሩበት ፤ ህዳጣን መብት የሚከበርበት ይሆናል እጂ (Majority rule , minority right)  ፤ በሀረሪ ፤ በድሬዳዋ (50/50 እና 40/40/20  )፤ ቤኔሻንጉል፤ ሌሎች ክልሎችም የሚሰራበት የአፓርታይድ ስርዓት አይነት  ይወገዳል፡፡ ይኸን የሚሆነው ግን ኢትዮጵያዊያን ምሁራን በሰከነ መንገድ ፤ከየአቅጣጫው ተሰብስበበውና፤ መክረው ዘክረው በሚያወጡት ህገመንግስታዊ ሰነድ ይሆል፡፡

እነዚህን ማስተማመኛዋች  ወይንም እውነታዎች ተወዳዳሪዎች ቢያፈነዶቸው አንድም  እንቅፋቶችን ለመቀነስ ብሎም ደጋፊን ለማሰባሰብ ይረዳሉ፤ ሁለትም ሃቀኛ ደጋፊዎችን ለማወቀቅና  የማይደግፉአቸውንምንም ለማወቅ ይረዳል፡፡  ገዢው ፓርቲ መንግስትና ሀገር እየቀላቀለ በሚጠቀምበት ሁኔታ እና  ውስጣዊና ውጫዊ ግጭቶች ብዙሃኑ ላይ “መንግስት አለ ፤መንግስት የለም፤ ተጠቃን” የሚል ጥያቄዋች በሚመላለሱበት ወቅት ለተወዳዳሪዎች ምርጫ ማካሄድ እጅግ ፈታኝ ነው፡፡

Friday, March 1, 2019

የመቀሌ ምሽግ! አብራሃም ለቤዛ


የመቀሌ ምሽግ!
ትህነግ/ህወሓት መቀሌ መሽጎ የተለያየ እቅድ እያወጣ የፌዴራል መንግስትን እጅ ለመጠምዘዝ እየሞከረ ነው፡፡ ጊዜ መግዣ የመሰለው አመራጭ ሁላ በመደመርና ትዕግስት ፍልስፍና ለተለጎመው ለአብይ አህመድ አስተዳደር ፈተና ሆኖል፡፡   ዛሬ ትህነግ/ህወሓት በሚመራው ክልል በጉልበት በጠቀለላቸው የወልቃይት እና ራያ አማራ ህዝብ ላይ እልቂተ እያደረሰ ይገኛል፡፡  መቀሌ የመሸገው ሃይል የመጨረሻ ካርዱን የትግራይ ህዝብን ጭዳ ለማድረግ የጦርነት ዝግጅት እደረገ ነው፡፡ በኢትዮጵያ የመጣውን አቃፊ የለውጥ ጅማሮ ከጅምሩ እያጣጣለ ፤ትህነግ/ህወሓት  የማይዘውራት ኢትዮጵያ በአፍንጫ ትውጣ እያለ ነው፡፡ እኛ የገነባባት ኢትዮጵያ ካላከበረችን ፤ የትግራይ ሪፐፕሊክ መስርተን ከጎረቤት ኢትዮጵያ በተሸለ ከጎረቤት ሱዳን  ጋር  እንወዳጃለን እያሉ ነው፡፡  በ27 ዓመት ዘርፈው ያጎጎዙት ሃብት የትግራይ ሪፐፕሊክ ለመመስረት እና በእራሳችን ለመቋም ያስችለናል እያሉ ነው፡፡  ትህነግ/ህወሓት እራሱን የትግራይ ህዝብ ጠበቃ አድርጎ ሲያቀርብ ፤ በትህነግ/ህወሓት ቀንበር ስል ያለው የትግራይ ህዝብ ስሜቱን የሚገልፅበት ምንም ምርጫ የለውም፡፡ አምባገነኖች የእራሳቸውን ድርሰት በማንበብ ስለሚፅናኑ‹‹ ትህነግ/ህወሓት ከተነካ የትግራይ ህዝብ ቀፎው እንደተነካ ንብ ሆ ብሎ ይነሳል›› በሚል ቅዠት ውስጥ ገብተዋል፡፡
እቴጌ ጣይቱ   የጦርነትን  አስከፊነት  እና የነፃነትን አስፈላጊነት ከመቶ አመት በፊት  በዚህ ሀረግ ነበር የገለፁት፡፡‹‹ እኔ ሴት ነኝ ጦርነት አልወድም፡፡ ሆኖም ይህን ኢትዮጵያን የኢጣሊያ ጥገኛ (ውጫሌ ውል) የሚያደርግ ውል ከመቀበል ጦርነትን እመርጣለሁ››   ምንም እንኳን ጦርነት አስከፊ እና አጥፊ ቢሆንም አያቶቻችን የነፃነት ትርጉም ስለገባቸው ፤ በመካከላቸው ያለ ልዩነት ትተው፤ እንዲሁም ከንጉስ ሚኒሊክ ጋር ቅራኔ የነበራቸው የጦር አበጋዞች ሳይቀር ወራሪውን ሃይ ለመመከት ተሰልፈዎል፡፡ አፄ ሚኒልክም ‹‹ አመልህን በጉያህ ፤ ስንቅህን በአህያህ  ይዘህ ተከተለኝ ›› የሚል ጥሪ ነው አቃፊ የሆነና ይቅርታ ታከለበት አርቆ አሳቢነታቸው ያሳየ አዋጅ ያስተላለፉት፡፡
በውጫሌ ውል ሸፍጥ ምክያት የተቀሰቀሰው ጦርነት በመጀመሪያው አውደ ውጊያ  አምባላጌ ተራራ ላይ የተጠላትን ጦር ካስለቀቀ በኋላ ሁለተኛው ግንባር የመቀሌን ምሽግ ማስለቀቅ ነበር፡፡ የጠላት ጦር የእንዳ እየሱስን ተራራ ደጀን አድርጎ በመቀሌ ላይ የሰራው ምሽግ በግንብ ፤ ሽቦ አጥር የተጠናከረ ሲሆን ፤ በባዶ እግሩ የዘመተውን የሃበሻን ጦር ለመመከት የጠላት ጦር በፋሽኮ ጠርሙስ ስብርባሪ ምሽጉን አጠናከሮል፡፡  የመቀሌ  ምሽግን ለመስበር በወገን ጦር ላይ ከፍተኛ የሆነ የህይወት መስዋትነት አስከፍሎል ፡፡ በዚህ መሃል በከአውደ ውጊያው ያሉት እቴጌ ጣይቱ  ከጠላት ጦር የተገኘ የስለላ መረጃ ይደርሳቸዋል፡፡ ይኸውም የጠላት ጦር ከወገን ጦር አልፎ ከሚሄድ ምንጭ ውሃ እንደሚጠጣ፡፡
እቴጌ ጣይቱ ለጠላት ጦር የሚሄደው የምንጭ ውሃ የማገድ  እቅዳቸውን ምንጩ በማስጠለፍ እና ምንጩን በተጠናከረ የወገን ጦር በማስጠበው የጠላትን ጦር ከውሃ እቅረቦት ውጭ አደረጉት፡፡ የጠላት ጦር ለራሱም ሆነ ለጋማ ከብቶቹ ውሃ ማግኘት ስለልቻለ ፤ ተደላልድሎ የያዘውን ምሽግ ሊለቅ ችሎል፡፡ ሴት አያቶቻችን ከመቶ አመት በፊት እንደዚህ ብለጠት በተሞላበት ሁኔታ አመራር እየሰጡ የአገርን ነጻነት ጠብቀዎል፡፡ እቴጌ ጣይቱ የወገን ጦርን ስንቅ በበላይነት እያስባበሩ ከአንድ ሺ ኪሎ ሜትር ባለይ በእግር ተጉዟ ለውጊያ የሚሰለፍ ሰራዊት ማፍራት ችለዎል፡፡
ዛሬም በኢትዮጵያ በመቀሌ የመሸገው  ትህነግ/ህወሓት በኢትዮጵያ ለይ ያቀደውን የጦርነት እቅድ የሚያከሽፍ እንደ ጣይቱ ያሉ ብልህ የዘመናችን ሴቶችን እንሻለን፡፡  ሴቶች የጦርነትን አሰከፊነት ያውቁታል ፤ የነፃነትን ጥቅምም እንደዚሁ፡፡ የኢትዮጵያ ሴቶች ጣይቱን ፈለግ በመያዝ በኢትዮጵያ የመጣውን የነፃነትት የእኩልነት የተስፋ ጉዞ በሙሉ ልብ ሊደግፉት ይገባል፡፡ ይኸ ማለት ያለፈውን የጭቋና ስርዓት ፤ አግላይ ስርዓት ለመመለስ በመቀሌ የመሸገው ስርዓት ማውገዝ ይጠበቅባቸዋል፡፡ የትገራይ እናቶች የጦርነትን አስከፊነት በደንብ ያውቁታል፡፡ ትህነግ/ህወሓት ትግራይ ተደፍራለች ፤ ተከባለች ለሚለው ጥሪ  ትህነግ/ህወሓት ሰከን ብሎ በእኩልነት ላይ ለምትመሰረት ኢትዮጵያ ተገዢ እንዲሆን ሊያሳስቡት ይገባል፡፡
‹‹የጎበዝ እናት ታስታውቃለች
፤አፋፍ ላይ ሆና በለው ትላለች››
የዘመናችን ሴቶች /እናቶች ከጦር ሜዳ ውለው የሞራል  ሆነ የአካል ስንቅ   መስጠት ላይጠበቅባቸው ይችላል፡፡  የሞራልም ሰንቅ ማዘጋጀትም ሆነ የአካል ስንቅ ማዘጋጀት  ፤ ምናልባትም ዘመናዊ  መንገድ  መስራት አስፈላጊ ስለሆነ፡፡ ነገር ግን የኢትዮጵያ ሴቶች/እናቶች  አበክረው ስለ ሰላም  መስበክ ይኖርባቸዋል ፡፡ በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ሰላም፡፡ አንዱ አንዱ ደፍጥጦ፤ ጭጭ አድርጎ የሚመጣ ሰላም  (Like the peace maker bomb) ሳይሆን በመከባበር የሚመጣ ሰላም፡፡ አርቲስ ማሪቱ ለገሰ  ስለ ሰላም ጥሩ አድርጋ ተጫውታለች፡፡ 
ሰላም ሰላም ቢሉት  ሰላም ለአፍ ይሞቃል፤ 
በትግል ያልተገኘ ከጦርም ይልቃል ፤
የሽንፈት ሰላም ግን ከሽብር ይከፋል፤
የሽንፈት ሰላም ግን ከሽብር ይከፋል፡፡
የኢትዮጵያ ሴቶች/እናቶች  የትግራይ  ሴቶች/እናቶች  ስለ ሰላም መስበክ አለባቸው፡፡ የተገኘውን መድረክ መጠቀም አለባቸው፡፡  የሰላም ሚኒስቴር  አቋቁመናል፤ አስር ሴት የካቤኔ ሚኒስቴር ሰይመናል፤ ወዘተ፡፡ ሴቶች ስለ ሰላም በተግባር አሁኑኑ ያስፈልጋል፡፡




Tuesday, February 12, 2019

የመስኩ ላይ ቁርሾ! !!!ጃኖ Mengistu Zegeye



ሲጀምሩ ፤
ሁለቱም ቆርኬዎች ፤
አብረው ከኖሩበት ፤
ከሚያምረው መስክ ዳር ፤
እየጋጡ ነበር ፤
ከጨፌው ማሳ ላይ ፤ እየፈነደቁ ፤
ድንገት ሳይታሰብ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ወዳጅ ዘመድ መስለው ፤ ወደዚያ ዘለቁ ።
ቆርኬዎቹ ዘንተው ፤
ሳር ከሚግጡበት ፤
ደረሱ ተኩላዎች ፤ እየተፋነኑ ፤
ውሃ በሞላው አፍ ፤
የጨፌውን ማማር ፤
የጋጮቹን ገላ ፤ እያስተነተኑ ፤
የተኩላ መንጎች ፤
እንኳን በስጋቸው ፤
በተቆላለፈው ፣ በቀንዳቸው ቀኑ ።
ቆርኬዎቹ ጠግበው ፤ እስኪፈነጥዙ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ሳሩ ላይ ዋሉበት እየተሟዘዙ ።
ጀመሩ ቆርኬዎች ፤
በጥጋብ ጀመሩ ቀጠሉ ማስካካት ፤
ተኩላ ተናቃ ፤
በጨዋታ መሃል ሸር ለማስገባት ።
እንደዚህ አላቸው ተኩላ አባ ሴራ ፤
ከአያት ቅም አያቶች ታሪክ ስናጣራ ፤
አለቃ ሚሆነው የቆርኬዎች አውራ ፤
ታግሎ የጣለ ነው ፤
ተፋልሞ ሚገዛ ከገጠሙት ጋራ ።
ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ጠቅልሎ ፤
በቀንዱ ጀመረው ፤
ካንደኛው ትከሻ አንዱ ቆርኬ ዘሎ ።
ተኩላ ዳር ቆማ ፤
በጭብጨባ በአጀብ ፤
በል በለው ትላለች ፤ በክፋት አንደበት ፤
ጀግና ማለት በኛ ፤
የጫካው አርበኛ ፤ የሚዘመርለት ፋኖ እየተባለ ፤
ቀንድን በቀንድ ይዞ ፤
አንገቱን ጠምዝዞ መሬት ላይ የጣለ።
በግብግብ መሃል ፤
ገራገር ቆርኬዎች ፤
የተኩላን ፊሽካ ፤ ሰምተው ተናነቁ ፤
ቀንዳቸው ተጣልፎ ፤
ሁለቱም ሜዳው ላይ ዘፍ ብለው ወደቁ ።
በተጠለፈ ቀንድ ፤ በተገመደ አንገት ፤ ወድቀው ተጋጠሙ ፤
ራስ በራሳቸው በጀመሩት ትግል ማንም ሳያሸንፍ ሁለቱም ደከሙ ፤
በተኩላ ተንኮል አብሮ አደግ ቆርኬዎች ሞትን ተሸለሙ ።
ይህን ያየ ቆርኬ ፤
የወንድሞቹ ሞት ፤ በተኩላዎች ሴራ መሆኑን ተረድቶ ፤
ከሞቱበት ሳር ላይ ፤
ካለው ትልቅ ዛፍ ላይ ፤
እንዲህ ብሎ ጻፈ ብእሩን አውጥቶ ።
ሰፊ መስክ ሳለ ፤
ሰፊ ጨፌ ሳለ ፤ በዚህ በመንደሩ ፤
ያንዲት እናት ልጆች ፤
አንተ ወግድልኝ
እኔ ነኝ አለቃ ፤
እኔ ነኝ ባለ ሹም በሚሉት አምቡላ ስለተሳከሩ ፤
ሞሰቡ ሳይቸግር ፤
እኔ በሚል እሳት ፤ ተበላልተው ቀሩ ።

የመስኩ ላይ ቁርሾ! !!! ጃኖ Mengistu Zegeye

የመስኩ ላይ ቁርሾ! !!! ጃኖ Mengistu Zegeye
ሲጀምሩ ፤
ሁለቱም ቆርኬዎች ፤
አብረው ከኖሩበት ፤
ከሚያምረው መስክ ዳር ፤
እየጋጡ ነበር ፤
ከጨፌው ማሳ ላይ ፤ እየፈነደቁ ፤
ድንገት ሳይታሰብ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ወዳጅ ዘመድ መስለው ፤ ወደዚያ ዘለቁ ።
ቆርኬዎቹ ዘንተው ፤
ሳር ከሚግጡበት ፤
ደረሱ ተኩላዎች ፤ እየተፋነኑ ፤
ውሃ በሞላው አፍ ፤
የጨፌውን ማማር ፤
የጋጮቹን ገላ ፤ እያስተነተኑ ፤
የተኩላ መንጎች ፤
እንኳን በስጋቸው ፤
በተቆላለፈው ፣ በቀንዳቸው ቀኑ ።
ቆርኬዎቹ ጠግበው ፤ እስኪፈነጥዙ ፤
እነ ተኩላዎች ፤
ሳሩ ላይ ዋሉበት እየተሟዘዙ ።
ጀመሩ ቆርኬዎች ፤
በጥጋብ ጀመሩ ቀጠሉ ማስካካት ፤
ተኩላ ተናቃ ፤
በጨዋታ መሃል ሸር ለማስገባት ።
እንደዚህ አላቸው ተኩላ አባ ሴራ ፤
ከአያት ቅም አያቶች ታሪክ ስናጣራ ፤
አለቃ ሚሆነው የቆርኬዎች አውራ ፤
ታግሎ የጣለ ነው ፤
ተፋልሞ ሚገዛ ከገጠሙት ጋራ ።
ብሎ ንግግሩን ሳይጨርስ ጠቅልሎ ፤
በቀንዱ ጀመረው ፤
ካንደኛው ትከሻ አንዱ ቆርኬ ዘሎ ።
ተኩላ ዳር ቆማ ፤
በጭብጨባ በአጀብ ፤
በል በለው ትላለች ፤ በክፋት አንደበት ፤
ጀግና ማለት በኛ ፤
የጫካው አርበኛ ፤ የሚዘመርለት ፋኖ እየተባለ ፤
ቀንድን በቀንድ ይዞ ፤
አንገቱን ጠምዝዞ መሬት ላይ የጣለ።
በግብግብ መሃል ፤
ገራገር ቆርኬዎች ፤
የተኩላን ፊሽካ ፤ ሰምተው ተናነቁ ፤
ቀንዳቸው ተጣልፎ ፤
ሁለቱም ሜዳው ላይ ዘፍ ብለው ወደቁ ።
በተጠለፈ ቀንድ ፤ በተገመደ አንገት ፤ ወድቀው ተጋጠሙ ፤
ራስ በራሳቸው በጀመሩት ትግል ማንም ሳያሸንፍ ሁለቱም ደከሙ ፤
በተኩላ ተንኮል አብሮ አደግ ቆርኬዎች ሞትን ተሸለሙ ።
ይህን ያየ ቆርኬ ፤
የወንድሞቹ ሞት ፤ በተኩላዎች ሴራ መሆኑን ተረድቶ ፤
ከሞቱበት ሳር ላይ ፤
ካለው ትልቅ ዛፍ ላይ ፤
እንዲህ ብሎ ጻፈ ብእሩን አውጥቶ ።
ሰፊ መስክ ሳለ ፤
ሰፊ ጨፌ ሳለ ፤ በዚህ በመንደሩ ፤
ያንዲት እናት ልጆች ፤
አንተ ወግድልኝ
እኔ ነኝ አለቃ ፤
እኔ ነኝ ባለ ሹም በሚሉት አምቡላ ስለተሳከሩ ፤
ሞሰቡ ሳይቸግር ፤
እኔ በሚል እሳት ፤ ተበላልተው ቀሩ ።

Friday, September 14, 2018

History 101: Fiction and Facts on Oromos of Ethiopia

(a guide for foreign journalists on Oromos and Ethiopian history)
Oromo, Ethiopia
Courtesy: ayyaantuu.com

(ADAMA, Ethiopia) - Recently, the Qatar-based media al Jazeera has published several articles concerning the Oromo people of Ethiopia. (http://www.aljazeera.com/indepth/opinion/2013/07/2013714133949329934.html) It is the first international media outlet to extensively report on our people and it should be praised for bringing our cause to the world stage.
One of the benefits of this exposure is it forces Ethiopian authorities to address human rights abuses in the country and to let them know that the world is watching. Oromos and other Ethiopians have been struggling for equal rights and democracy for decades. While it is important to report about Oromo people' background and historical perspectives, it is however vital that we report accurate information. Instead of benefiting us, reporting inaccurate or biased information can actually harm our struggle for democracy. Instead of creating national consensus and peace, it can instigate bitterness and anger.
One of the reasons al Jazeera reported inaccurate information about Oromo history is because it depended on one-sided sources, especially from members or supporters of Oromo groups outside of Ethiopia (diaspora OLF, OFDM etc). But nobody can blame al Jazeera media because most people inside Ethiopia would be too scared to speak or contribute. The only option al Jazeera or any foreign media has is to use diaspora/refugee/external sources outside Ethiopia. This is a dilemma all foreign media outlets face while reporting about third-world countries like Ethiopia.
For educational purposes, some corrections are provided below to fix inaccuracies reported on al Jazeera media regarding Oromo history and our struggle for democracy. The corrections below are supported by non-political scholars, but they might be rejected by biased politicians (both from ruling party and from opposition party) for the obvious reasons. However, they are based on historical textbooks, European authors and scholarly accounts.


Fiction #1:

"Between 1868 and 1900, half of all Oromo were killed, around 5 million people"

Fact #1: 
This is one of the most repeated inaccuracies, usually told by Secessionist Oromos, radical ethno-nationalist politicians outside the country or pro-OLF history revisionist websites like gadaa.com et al. However, the undisputed fact is that even the total Ethiopian population (the sum of dozens of ethnic groups) was much less than 5 million in the late 1800s, let alone one ethnic group being 10 million. So claiming that 5 million ethnic Oromos were killed by Emperor Menelik's forces does not add up. The truth is several thousand Oromos were in fact killed during battles of that era. It was not a "genocide" as some politicians claim but it was a massacre of the ill equipped southern forces defeated by the Shewan military of Emperor Menelik which had more European weapons. Throughout those decades, the truth is more Oromos were killed by other Oromos than by non-Oromos because competing Oromo Clans often traded for weapons to have an upper hand against their local competitors, who were often their fellow Oromo and Sidama neighbors.  And it was not the first lop sided victory of that era in Africa because various communities from all corners of Ethiopia had attacked one another during the "resource battles" and whichever group had more modern weapons had the upper hand. To summarize, Professor Mengistu Paulos of Jimma University said it best when describing right-wing Oromo liberation philosophy:-- 

"Most fictional accounts of 'Oromo history' blindly accepted as facts by some misled people are manufactured by former politicians turned Pseudo-historians  like OLF writer Asafa  Jalata, who is renowned for abuse of paraphrasing, often with out-of-context citations. For example, while quoting the 19th century Russian Alexander Bulatovich (who provided an 'educated guess' of annihilation of almost half Ethiopian population by disease, famine and war, including internal conflict between Oromo clans and with Abyssinians), the OLF-writer Asafa Jalata infamously claimed half Oromo population was killed by 'evil' Amharas.  This was purposely done by Mr. Jalata to create a foundation for ethnic hatred between Oromos and Amharas. Ironically, even Mr. Bulatovich himself never had the capacity nor the legitimacy to do a reliable census, as he spent just a couple of months walking around Oromia and hunting elephants in 1890s."


Fiction #2:

"…. largely Muslim Oromo people"


Fact #2:

This is a phrase seen in some media outlets but not most. Oromo people have never been a predominantly muslim people. In fact, both Christianity and Islam is not our ancestral religion because we have practiced an indigenous traditional religion for centuries before. Gradually, Islam and Christianity were both adopted (during Oromo migrations) by us and imposed (during conquest of our lands by Abyssinian/Christians & Somalis/Islam)  on us thru out history. Even today, both the two major religions have equal representation among Oromos. The latest official 2007 census showed that around 48% of Oromos practice Christianity (Both Orthodox & Protestant) while around 47% of Oromos practice Islam. Yet, word on the ground is that the Islam population might soon surpass Christianity among Oromos in the future because Orthodox Christianity is decreasing inside Oromia. 

Fiction #3

"Abyssinians labelled Oromos the derogatory word 'Galla'"

Fact #3:

For many decades, this false statement has been used by Oromo separatists to create emotional resentment among Oromos against Semitic Abyssinians (Amharas, Tigrayans and Gurages).  The fact is the derogatory word "Galla" was first used by Arab and muslim Somalis to describe Oromos as "gal" meaning "outsiders" and "Pagans." Muslims used this label during Oromo migration because Oromo people had their own religion which the Muslims believed was paganism. Nonetheless, this derogatory word was gradually adopted and used by other Ethiopians. 

Fiction #4:

"Oromos were colonized by Emperor Menelik"

Fact: #4

Another popular claim made by secessionist Oromo politicians (and usually repeated by foreign journalists) is the fiction that Oromo people (as a whole ethnic group) were colonized by another ethnic group. Usually, the slogan goes "Abyssinians colonized Oromos" etc. This claim is popular among the Oromo Liberation Front (OLF) organization and consequently among some Diaspora Oromo nationalists living in America and Europe.  While a different version or a re-arrangement of the wording might still be true…in general, the Oromo nation as a whole was never colonized by another Ethiopian ethnic group. To start with, even a united one Oromo nation did not exist at those times. All non-political historical textbooks show the existence of battles between multi-ethnic BUT monolingual communities for many centuries through out Ethiopia. Even in northern Ethiopia (traditional "Abyssinia") Oromos have migrated and mixed so much with Tigrayans, Amharas, Afars etc for centuries that the "Abyssinia" state itself was never a one-ethnic state. In fact, even around the 1700s, Rayya Oromos and Yejju Wallo Oromos conquered and dominated a portion of Amharas and Tigrayans; and thus made Afan Oromo the official language of Abyssinia for that brief period. Meaning: clans and ethnic groups have mixed up in Ethiopia for over a millennium but the dominant ethnic group always imposed its language since it was convenient. This linguistic domination however was not always as exploitive and as vilified as it is today; because many of the ethnic groups living along trade centers and trade routes often spoke the languages of other ethnic groups already, because there was financial or commercial incentive to do so. This is the background of the region. Therefore, when it comes to the Emperor Menelik era, all historians have argued that it is more factual to say a predominantly Amharic language speaking community gradually conquered a predominantly Afan Oromo language speaking community in the 1800s. So this does not mean an Oromo ethnic group was conquered by an Amhara ethnic group. In fact, just like Amharas of the north were divided,Oromos were also divided and in conflict among themselves. The obvious evidence for this comes from the fact that the Amhara Emperor Menelik was imprisoned by other Amhara regional kings when he was younger. And when he was freed, Oromo clans were also in fierce battles amongst each other, so much so that the Tullama Oromo, Limmu and Macha Oromos created an alliance with the Shewan Amharas of Menelik, leading to the infamous battles of 1880s that led to this said alliance easily crushing the non-allied Oromos in various bloody wars. In short, Oromos as a one whole were never colonized by exclusively non-Oromos. In fact, the original founders of the OLF organization themselves never believed it so they did not emphasize the word "colonization" in the beginning. But in the mid-1970s, OLF leaders needed to mobilize Oromos against Emperor Haile Selassie (who was half Oromo himself) and to justify the call for "Oromia independence" from "colonial Ethiopia." Therefore OLF had to create a bad cop-good cop scenario for their convenience and simplified history for their people to create national resentment. This helped OLF to portray Oromos as suddenly being colonized by this foreign ethnic group (Amhara) that we (Oromos) have never came in contact with before.  This is common tactic used by national liberation movements around the world. The truth that most Ethiopians know is that Shewa based Oromos and Amharas (ethnically mixed Ethiopians) were the main creators of modern Ethiopia. In his book "Who are the Shoans," the historian and anthropologist, Dr. Gerry Salole once summarized that: "In terms of descent, the group that became politically dominant in Shewa (and subsequently in Ethiopia) was a mixture of Amhara and Oromo."   


In Conclusion, the above are 4 of the main issues that create confusion for foreign journalists who report on Oromo people and Oromo politics in Ethiopia.  While it is vital that al Jazeera and other media outlets cover the current suffering of Oromos and other Ethiopians, it is necessary to report responsibly. Otherwise, creating confusion and resentment between the younger Ethiopian population causes more problems than solutions. In reality, not just Oromos, but all Ethiopians have suffered under several governments and the only way they can achieve freedom and lasting democracy is when united, not when divided by tribes or not when being polarized by historical lies presented as truth.  It is important that foreign media outlets make corrections or report accurate information to avoid inflammatory statements that are destructive and counter productive against Oromos and all Ethiopian people' ongoing struggle for democracy, development and justice.


Feqadu Lamessa is a former Adama University professor and writer

Friday, August 24, 2018

መርዙን በመርዙ – “የብሄሮች ጥያቄ” በዛሬይቷ ኢትዮጵያ (በሃያሬ ተንለሱ)






መርዝን በመርዝነት ስለመርዝ መመረዝ፣
የመርዙን ለመርዙ በመርዙ ማስመረዝ።
(
ሃይሉ /ዮሃንስገሞራው)
በሃገራችን ኢትዮጵያ የችግሮችን አንገብጋቢነትና ጥልቀት በመረጃና በማስረጃ ሣይጠናከር የሚቀርቡትን መንደርደሪያዎች የማያግዙ የተሳሳተና መደበኛ ያልሆነ ሃሳብ /Informal Fallacy/ በችኮላ ማጠቃለያ /Hasty Generalization/ ላይ የተመሰረቱ ግንዛቤዎችን በማሽከርከር ከምላሹ ይልቅ ብዥታው ጎልቶ የሚወጣው ዱባ ድፍን መሣዩ ይህየብሄሮች ጥያቄየተሠኘው ነው። በዚህ መጣጥፍ ላይ ፀሃፊው ለማነፃፀር እንዲረዳው የስታሊንን ትንታኔ መጠቀሙ ትንታኔውን በመቀበሉ ሣይሆንየብሄሮች ጥያቄትርክት መነሻ ሀሳብ የሚያጠነጥኑ ሃይሎች መነሻና መድረሻቸው ይህ የስታሊን መርሆ በመሆኑም ነው። ተግባሩም የጎሣ ፖለቲካ መርዝን በመርዝነቱ በመመደብ፤ መርዙን በመርዙ ለማክሸፍና በመርዙ ለማስመረዝ እንዲቻል ሲባል ነው። ወደዚህ ጥያቄ ውስጥ ከመግባታችን በፊት በአንድ ወይም በሌላ ማህበረሰብ ውስጥ ያሉትን ማህበራዊና ባህላዊ ክፍፍሎችና ስብስቦች /Social stratification & groups/ መቃኘት የግድ ይላል።
). ቤተሠብ /family & kinship/
ይህ በተወላጅነት፣ሥጋና በጋብቻ ዝምድና ላይ የተዋቀረ አደረጃጀት ነው።
). ነገድ /Clan/
መሠረቱን በጋብቻ፣ በዝምድና ላይ ያደረገ በጋራ ቅድመ አያት መስመር የተሳሰሩ ቤተሰባዊ የሰዎች ስብስብና የሠፋ ቤተሰብ ነው።
). ጎሣ /Tribe/
በእድገት ደረጃ ከነገድ ላቅ ያሉ፤በተለያየ መልከዐ-ምድር ሰፍረው በድንበር ዘለል ጋብቻ፣አንፃራዊ አንድነት፣ የጋራ መግባቢያ ቋንቋ፣ ባህልና ስነልቦና ያዳበሩና በዝምድናና ጉርብትና ሃረግ የተቆላለፉ የተለያዩ ነገዶች ውህደት ነው።ጎሣዎች የጋራ ኢኮኖሚያዊ ትሥስርና የዳበረ ኢኮኖሚ አይኖራቸውም።
). ብሄር (ትርጉሙ ከታች ተካቷል)
A. “የብሄር ጥያቄ
). ታሪካዊ መሠረት
ዓለም በሶሻሊዝም ጎርፍ ልትጥለቀለቅ በተቃረበችበት .. 1917 የራሲያ ቦልሼቪኮች ዐቢዮት ሶስት አመት ቀደም ብሎ .. 1913 “ማርክሲዝምና የብሄር ጥያቄበሚል እርዕስ የተፃፈው የጆሴፍ ስታሊን መፅሃፍ ይህን ጥያቄ ለማስተናገድ የቀረበ የጊዜው ሶሻሊስታዊ መጣጥፍም ነበር። የዚህም መጣጥፍ አይነተኛ ተለዕኮ ወይም የትኩረት አቅጣጫ በሩሲያና በምስራቅ አውሮፓ ውስጥ የነበሩና የካፒታሊስት ኢንደስትሪያል ኢኮኖሚ በአንፃራዊነት ያዳበሩ እንደ ፖላንድ፣ ቼክ፣ ስላቭስ፣ ፓልስ፣ ኦስትሪያ፣ ጆርጂያ፣ አርሜኒያ፣ ዩክሬን፣ ሃንጋሪ .. አስመልክቶ የተቀመረ የቦልሼቪኮች እይታም ነው።
B). የብሄር ትርጉም በጆሴፍ ስታሊን
ስታሊን ብሄር ትርጉም የሠጠው በሚከተሉት ግን በማይነጣጠሉ አምስት መስፈርቶች አማካይነት ነው። የብሄር መለያ መስፈርቶች
1. ‹
የዘር ወይም የጎሣ ያልሆነ ነገር ግን በታሪክ ሂደት በአንድ ላይ የተቆራኙ የተለያየ ህዝብ ስብስብነው።
በስታሊን ትንታኔ መሠረት የጣሊያን ወይም የጣሊያን ብሄር የምንለው የተመሰረተው በሮማውያን፣ ኢትረስከን፣ቱተን፣ግሪክስ፣አረብ .. እንዲሁም የፈረንሣይ ብሄር የተዋቀረው ከጎል፣ ሮማንስ፣ ብሪተን፣ቱተን .. መሆኑን በማስገንዘብ ብሄር የተለያዩ ህዝብ ቁርኝት እንደሆኑ በምሳሌ አሳይቷል።
2. ‹የጋራ ቋንቋ
የጋራ ቋንቋ አንዱ የብሄር መለያ ነው። በርግጥ የተለያየ ቋንቋ የሚናገር ብሄር የለም። ነገር ግን አንድ አይነት ቋንቋ የሚናገሩ የተለያዩ ብሄሮች ልክ እንደ እንግሊዝና አሜሪካ ወይም ኖርዌጃንና ዳኒሽ ይኖራሉ ይላል። አንድ አይነት ቋንቋ መናገር በራሱ የብሄርን የተሟላ ትርጉም ለመስጠት አያስችልም።
3. ‹የጋራ የሆነ የግዛት አካል
4. ‹የጋራ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ግኑኝነትና ኢኮኖሚያዊ ጥምረት /economic cohesion/
የጋራ ግዛት አካል ብቻውን በቂ ባለመሆኑ በዚህ አካል በብሄሩ ውስጥ ያሉ የተለያዩ ክፍሎች አንድ ላይ የሚያመጣና ወጥ የሚያደርጋቸው የጋራ ኢኮኖሚያዊ ትሥስርና የዳበረ ኢኮኖሚ መኖር አለበት።
5. ‹የጋራ ስነልቦናዊ ቅንብር /psychological make-up/›
ይህ ማለት በጋራ ቋንቋ፣ የግዛት አካል/common teritories/ ፣በዳበረ የኢኮኖሚ እድገት የተፈጠረ ኢኮኖሚያዊ ትሥስርና በባህል የሚገለፅ ተመሣሳይ የስነልቦና ቀመር ያላቸው ዘር ወይም ጎሣ ያልሆነ ስብስብ ነው።
C). “የብሄር ጥያቄትርክትና የብሄር ደረጃ
ምደባ በኢትዮጵያ
የብሄር ጥያቄ በኢትዮጵያ ውስጥ መውገርገር በተለይ የጀመረው የሶሻሊዝምን ቅኝት የተላበሰው .. 1960 የተማሪዎች እንቅስቃሴና በተለይምየብሄሮች ጥያቄበሚል እርዕስ .. 1969 . በዋለልኝ መኮንን በቀረበ ፁህፍ ላይ ነው። በዚህ ፁህፍ ዋለልኝ እንዲህ ይላል።
« … የሶሻሊስት ረዕዮተ ዓለም የተማሪው ረዕዮተ ዓለም የሆነበት አዲስ ምዕራፍ ላይ ደርሰናል። ተፃራሪ ሃይሎች የምንላቸውም በአብዮትና በጥገና ለውጥ መሃል ያለው ሣይሆን በሳይሣዊ ሶሻሊዝምና ጤናማ ያልሆነና ወረተኛ /perversion & fadism/ አስተሳሰብ መካከል ነው። ዋለልኝየብሄሮች ጥያቄበሶሻሊዝም መነፅር መቃኘቱን ሲቀጥል « ኢትዮጵያ የአንድ ብሄር አገር አይደለችም። የራሣቸው ቋንቋ፣አለባበስ፣ ታሪክ፣ማህበራዊ አደረጃጀትና የግዛት አካል ያላቸው የተለያዩ ብሄረሠቦች ሃገር ናት። ታዲያ ከዚህ ሌላ ብሄር ምንድነው? ስለዚህ የኦሮሞ ብሄር፣የትግራይ ብሄር፣የአማራ ብሄር፣ጉራጌ ብሄር፣ሲዳማ ብሄር፣ወላይታ ብሄር፣አደሬ ብሄር አለ። ለመሆኑ ሐሰተኛ ብሄረተኝነት /Fake Nationalizm/ ምንድነው? ይህ ሐሰተኛ ብሄረተኝነት የአማራ ብሄረተኝነት ወይም በተወሠነ መልኩ የአማራ-ትግሬ ብሄረተኝነት ነው። የአማርኛ ሙዚቃ፣የአማራና የትግሬ የሆነው የኦርቶዶክስ ሃይማኖት፣የአማራ-ትግሬ ሸማ/ልብስ/ መልበስ ወይም ኢትዮጵያዊ ለመሆን ስም መቀየር፣ በህገ-መንግስቱ /ቤት ለመሄድ፣ ስራ ለማግኘት፣ ዜና ለመስማት፣ መፅሓፍ ለማንበብ አማርኛ መናገር የግድ ነው።የባህል ወረራው በደቡብ ያለው የአማራ፤ በከተማ ያለው የአማራ-ትግሬ ኢኮኖሚያዊ ጭቆና ነው። ያለው የበላይነት የአማራ-ትግሬ ነው።» ይለናል።
D). ጆሴፍ ስታሊንና የዋለልኝ እይታ
የዋለልኝ ፁሕፍ መሠረት ያደረገው ሶሻሊዝምና የስታሊንማርክሲስምና የብሄር ጥያቄየሚለው መጣጥፍ ነው። ዋለልኝ ለትንታኔው የሚጠቅመውን የስታሊን ትንተናን ጥራዝ በመንጠቅ ቢሆንም የስታሊን አምስት የብሄር መስፈርቶች በቅጡ የገቡት አይመስልም። ዋለልኝ «የራሣቸው ቋንቋ፣ አለባበስ፣ታሪክ፣ማህበራዊ አደረጃጀትና የግዛት አካል ያላቸው የተለያዩ ብሄረሠቦች ሃገር ናት»፡ይለንናታዲያ ከዚህ ሌላ ብሄር ምንድነው? ስለዚህ የኦሮሞ ብሄር፣የትግራይ ብሄር፣የአማራ ብሄር፣ጉራጌ ብሄር፣ሲዳማ ብሄር፣ወላይታ ብሄር፣አደሬ ብሄር አለ።ሲል እራሱን ጠይቆ ለራሱ ይመልሳል። በተለይም አንድን ብሄር ብሄር የሚያሰኙት መስፈርቶች ውስጥየጋራ የሆነ ኢኮኖሚያዊ ግኑኝነትና ኢኮኖሚያዊ ጥምረት /cohesion/ የሚለውን በተለይ የአንድን ብሄር የላቀ አደረጃጀትና ቅንብር፣የበለፀገ ኢኮኖሚን ገላጩን ቁምነገር ይዘነጋና የችኮላ ማጠቃለያ /Hasty Generalization/ ላይ ይደርሳል። ለዋለልኝ 183,415 የሚሆን ህዝብ ያለው ሃረሪ ሳይቀር ብሄር ነው። የቀረው ነገር ቢኖር የሃገሪቱን የጋማ ከብቶች በብሄር መሸንሸን ብቻ ነበር። ለርሱ ፁህፉን ከገለበጠበት የስታሊን መፅሃፍ ላይ ዕንኳን ብሄርዘር ወይም ጎሣ አይደለምየሚለውን ሃረግ እንኳ ዘንግቶታል ዋለልኝ የብሄርን ጭቆና የሚገልፀው በልብስ፣በዘፈንና በኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማራና ትግሬነት ነው። እነዚህን መሠረታዊ ጥያቄዎች እናንሣ። እርሱ በነበረበትም ሆነ በአሁኑ ዘመን ከበዓላት ውጭ የተባለውን ሸማ በከተማዎች፤በመላው ገጠር አይለበስም። ብዙው ኢትዮጵያዊ የሚውለውና የሚታየውም የአማራ ባህላዊ ልብስ ተላብሶ ሳይሆን በእርዛትና ነው። አማርኛ በታሪክ አጋጣሚ የሃገሪቱ ብሄራዊ ቋንቋ ሆኗል። ይህ ማለት የሌሎች ጎሣዎች ቋንቋ ላይ ተፀእኖ ቢኖረውም ጨፍልቋቸዋል ለማለት አይቻልም። በኢትዮጵያ ውስጥ 34.4% የሚሆነው ህዝብ ኦሮሚኛ፣ 27% አማርኛ ተናጋሪ ነው። መቶ ሚሊዮን ከሚገመተው የኢትዮጵያ ህዝብ ውስጥ አሁን እንኳ አማርኛን ከአማራ ውጭ የሚናገር ህዝብ አራት ሚሊዮን አካባቢ ነው። 98% ፐርሰንት የትኛውም ጎሣ አባል የራሱን ቋንቋ ይናገራል። አማርኛ የከተማ ነዋሪውና የአማራው ቋንቋ ብቻ ነው። ሃይማኖትን በተመለከተ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት አማራው የተቀበለው ሃይማኖት እንጂ የግል ንብረቱ አይደለም። በኢትዮጵያ ውስጥ 43.5% ኦርቶዶክስ፣ 18.6% ፕሮቴስታንት፣ 33.9% ሙስሊም ሲሆን በኦሮሚያ ብቻ 47.6% ህዝብ ሙስሊም ነው። ዋለልኝና የርሱንና የስታሊንን ንድፈ-ሃሣብ ከነባራዊው ሁኔታ ጋር ሳያቆራኙ የሚያላዝኑ የዘመናቸን አክራሪ የጎሣ ፖለቲከኞች ትርክት ውጭ 2010 በዓለም አቀፉ የሃይማኖት እድገት የመረጃ ቋት መሠረት የኢትዮጵያ የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮች .. 1910 ቁጥራቸው 3,290,000 እንደነበረ ይህም .. 2010 ወደ 35,710,000 ማደጉን ነው።ከላይ በሰፈሩት መረጃዎች በህዝብ ላይ ተጫነ የሚሉት ቋንቋና ሃይማኖትና ልባሣት ከንቱና በምኞት ላይ የተመረኮዘ ቅዠትም ነው።
E). “የብሄር ጭቆናውትርክት ሚስጥር
ዋለልኝም ይሁን አክራሪ የጎሣ ፖለቲከኞች ኢትዮጵያ ውስጥ ብሄር እንደሌለ አሣሳምረው ያውቃሉ። ኢትዮጵያ ቤተሠብን፣ የነገድና የጎሣ ስብስቦችን አቅፋ የያዘች ሃገር ናት። እነዚህ ስብስቦች በነጠላም ይሁን በቡድን በዳበረ የእርስ በርስ ግኑኝነት ተቆላልፈው፣ ወጥ በሆነ ቋንቋ ተጣምረው፣በስነልቦና የተገመደ ባህልን ይዘውና የብሄራዊ ማንነት/National Identity/ ተላብሰው ባለመገኘታቸው ብሄር ብለን ልንሰይማቸው ከቶውንም አንችልም። ኢትዮጵያ ውስጥ የነበረውም በፊውዳሊዝም ስርዓት ሣቢያ የነበረ የመደብ ብሄራዊ ጭቆና እንጂ የብሄር ጭቆና አይደለም። ይህ የፊውዳሊዝም ስርዓትም ከሁሉም ዘር በታማኝነትና በጋብቻ ትሥስር የተቆራኙ ግለሰቦችን ያቀፈ ልክ በሌላው ዓለም የነበሩ ተመሳሳይ ስርዓተ ማህበራት ጋር የቅርጽ እንጂ የይዘት ልዩነትም ያልነበረው ነው። በስታሊንም መስፈርትለብሄር ጭቆናውመፍትሄ ላይ የተቀመጠውንየብሄሮች የራስን እድል በራስ መወሰን መብት እስከ መገንጠልስለሚል አንድ ጎሣ የመገንጠል ጥያቄን ለማንሣት እራሱን ወደ ብሄር ደረጃ በፈቃዱ ማድረስና ማደናገር ብቻ ነው። ጎሣዎች በዚሁ መፅሃፍ የሚፈቀድላቸው የውስጥ የራስ ገዝ አስተዳደርም በመሆኑ ነው።
ኢትዮጵያ ዋለልኝና አክራሪ የጎሣ ፖለቲከኞች እንዳላዘኑትየብሄሮች እስር ቤትሣትሆን የተጨቆነ ህዝብ መታጎሪያ ሃገር ናት። ኢትዮጵያ ውስጥ ብሄር የለም። ብሄር ከሌለ ስለብሄር ጭቆትናማውራት አንችልም። ኢትዮጵያ ውስጥ ጥንትም የነበረው ብሄራዊ ጭቆና ነው።ዛሬ ያለው ወያኔያዊ የአፓርታይድ ስርዓት ነው። ይህም ስርዓት የአንድ ጎሣ ስብስብ ሆኖ የፖለቲካ
ስልጣን በመያዝ ኢኮኖሚያዊ ብዝበዛን በመላው ህዝብ ላይ የሚፈፅም ወራሪ የሽፍታ ቡድንም ነው። ወያኔያዊ የአፓርታይድ ስርዓትንም የጨቋኝ ብሄር መዋቅር ለማለት የማንችለው፡-
1. ትግራይ ብሄር አይደለችም። ወራሪው ወያኔም የጎሣ ጥርቅም ነው።በቋንቋ ፌደራሊዝም ስም የተቃኘ የአፓርታይድም ስርዓት ነው።
2. ይህ ወያኔያዊም ጎሣ ባህሉንም ሆነ ቋንቋውን በሌሎች ላይ አልጫነም።
3. የወያኔ የጎሣ የበላይነት የሚገለፀው በተቆጣጠረው ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊና አስተዳደራዊ መዋቅሮች በጠቀጠቃቸውና አግላይና ብቸኛ ተጠቃሚ ባደረጋቸውም የጎሣ አባላቱ ነው።
የህዝብን ችግር መፍታት የሚቻለው የችግሮቹን መንስኤና ባህርይ መረዳት ሲቻልና ለችግሮቹ የፈጠራ ትርክት ሣይሆን ተጨባጭ መፍትሄ ይዞ በመገኘት ብቻ ነው።
‘ETHNIC POLITICS AND PORK” TEND TO GO TOGETHER’
James D. Fearon