 |
Praising the traitor!!! |
ባለራዩ መሪ ፣ባለራዩ መሪ
፣ ዛሬ ድረስ የሚደመጥ የካድሬዎች የአፍ ማሞሻ ሀረግ ነዉ ፡፡ ከዚያማ
ሌጋሲ ምናምን ፣ የማይሰቀጥሉት ነገር እንደሌለ ይነግሩን ነበር ፣ አሁን ድረስ ጠቅላይ ሚኒስተር ሃይለማሪያም ደሳለኝ ጭምር የሚሉት
ነዉ፡፡
ሌጋሴ
ወደ አማርኛ ስንገለብጠዉ ቀሪ መታዎሻ ግለታሪክ የእኔም ፣ የአንቺም በአጠቃይ የአገር መሪ የነበረ ብቻ ሳይሆን የተራዉ ሞችም ይኖረዎል፡፡ ዎናዉ
ጉዳይ ምን አይነት ቀሪ መታዎሻ ታሪክ ጥለን አለፍን ነዉ፡፡
አቶ
መለስ ዜናዊ ምን አይነት ቀሪ መታዎሻ ትተዉልን አልፈዎል ? ኢህአዴግን ከእሳቸዉ ዉጭ ማየት
አንቺልም ለምን 21 ዓመት መርተዉታል፡፡ ኢህአዴግ በሙስና የነቀዘ ድርጅት ነዉ፣ አቶ መለስ በራሳቸዉ አንደበት ድርጅታቸዉ በሚመራዉ መንግስት
ዉስጥ (ኢ.ፌ.ዲ.ሪ.) የመንግስት ሌቦች እንዳሉ ለህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ገልጸዉ ነበር፡፡
ኢህአዴጎች
መጪዉ ጊዜ ከኢህአዴግ ጋር ብሩህ ነዉ ይሉናል ምርጫ በመጣ ጊዜ፤ የኢህአዴጎች በመሬት ንግድ መክበር፤የፓርቲ ንግድ ማጦጦፍ፣ ከደሆች
በተሰበሰበ ግብር በኢህአዲጋዊ ምቾት መኖር ደሃዉ ኢትዮጵያዊ እነሱን
ብቻ እንዲያኖኑር የተፈጠረ ስለሆነ ለእነሱ ብሩህ ነዉ፡፡
ኢህአዲጋዊ
እስከሆንህ ድረስ እስከፈለገህ ትዘርፋለህ፣ የፈለግከዉንም መሬት በወረራ ትይዛለህ ፣ግፋ ቢል ኢህአዴጋዊነትህ ከቀነሰ በወረራ የያዝከዉን
መሬት እንድትመልስ ይደረጋል፡፡ አንተ ላይ አንዳች ህጋዊ እረምጃ መዉሰድ ሌሎችን ኢህአዴጎችን ማስበርገግ ስለሆነ በማስተማር ትታለፋለህ
፡፡
ከኢህአዲጎች
አንዱ በነበሩት ሰዉ፣ በአቶ መለስ ዜናዊ የበኩር ልጅ ፣ ሰመሃል መለስ ዜናዊ ስም የተመዘገበ አምስት ቢሊዮን ዶላር ቼክ (የህዳሴ
አባይ ግድብን በእኛዉ በኢትዮጵያዊያን ተጀምሮ በእኛዉ በኢትዮጵያዊያን የሚያስጨርስ ገንዘብ ያህል)
በዉጭ አገር ባንክ እንደተንቀሳቀሰ ዶ/ር መኮንን ወንድሙ የተባሉ ኢትዮጵያዊ ለእንግሊዝ ምክር ቤት አቤት ማለታቸዉ የአደባባይ ሚስጢር
ነዉ፡፡ ይህ ጉዳይ ልማተዊ ነኝ ለሚል መንግስት አሳስቦት ማስተባበያ ሊሰጥበት የሚገባዉ ሲሆን ጀሮ ዳባ ልበስ መባሉ ያስገርማል፡፡
ምዕራብያዊያን ለደሃ አገራት ከሚሰጡን እርዳታና ብድር በላይ ከደሃ አገራት ሙሰኛ ባለስልጣናት የሚመዘበሩትን ሃብት በታማኝነት በማስቀመጣቸዉ የበለጠ ደሃ አገራት እንዲቆረቁዙ፣
ዜጎቹም ከሰዉ በታች እንዲኖሩ ምክንያት ሁነዎል፡፡ ለዚህ ደግሞ እንደምሳሌ ስዊዘርላንድን (Switherland) ብንወስድ ካላት
አመታዊ ምርት (GDP) አንጻር ከከፍተኛ ለጋሽ አገሮች ተርታ የምትመደብ ሲሆን በተቃራኒዉ እንደዚህ የምትጨነቅላቸዉ አገራት ዜጎች
ገንዘብ ተዘርፎም ሲመጣ አንጀቶ አይጨክንም፤ በሚስጢር በባንኮቾ ታስተናግዳለች፡፡
ምዕራብያዊያን
አገራት የዲሞክራሲ ስርዓት ቱርፋት ተጠቃሚዎች ቢሆኑም ለእኛ ለአፍሪካዊያን ግን የዴሞክራሲ ቱርፋት እንዲደርሰን እየረዱን አይደለም
፤ ምናልባትም እኛ አፍሪካዊያን ለአቅመ መብላት እንጂ ለአቅመ ዴሞክራሲ የደረስን አይመስላቸዉም፡፡ በእርግጥ እኛ አፍሪካዊያን
(ኢትዮጵያዊያን) ሰልፋችንን ማስተካከል አለብን፡፡ ለዴሞክራሲ የሚደረግ ትግል ከምእራብያዊያን ጉልበት አያገኝም ፤ ዎናዉ ጉልበት
ያለዉ በኢትዮጵያ ህዝብ ላይ ነዉ፣ነገር ግን ልምድ ከነሱ መቅሰም ይቻላል፡፡
ምዕራብያዊያን
ጥቅማቸዉን እስከተጠበቀ ድረስ ሰልፋቸዉን አይለዉጡም ፣ ነገር ግን
ህዝብ ከተነቃነቀ ፣ ህዝቡ የድል ችቦዉን ሊለኩስ ሲዘጋጅ በቅጽበት አቆማቸዉን ይለዉጣሉ፡፡ እዚህ ላይ አንድ ምሳሌ ማንሳት
ይቻላል፡፡ የፈረንሳይ መንግስት በወዳጁ የቤንአሊ የቱንዚያ መንግስት ላይ በ2011 ዓ/ም (እ.አ.አ) ሕዝባዊ አመጽ በተነሳበት ሰዓት
ቤንአሊን ለመታደግ አድማ በታኝ ተሽከርካሪዎች ለመላክ በተዘጋጀበት ሰዓት ፋታ የማይሰጠዉ ሕዝባዊ አመጽ በተቀጣጠለበት ሰዓት ቤንአሊ
ሆየ እንደለመዱት በአዉሮፕላናቸዉ ወደ ፈረንሳይ ሲበሩ ምእራባዊቶ ፈረንሳይ የአየር ክልሎን ዘግታ እንትንህን ላስ ብላቸዎለች፡፡
የዚህች
መልዕክት አላማ ትግላችንን በህዝብ፣ለህዝብ፤ከህዝብ ብቻ ከሆነ አምባገነኑን የኢህአዴግ
ስርዓት አሰወግዶ በምትኩ ሰፊ መሰረት ያለዉ ህዝባዊ ስርዓት ማምጣት እንደሚቻል ለመጠቆም ያህል ነዉ፡፡ ቸር እንሰንብት፡፡
ለአስተያየተዎ
(anethiopian@yahoo.com)
ኢትዮጵያንና ህዝቦቾን እግዚአብሄር ይባርክ!!!!