ወያኔ/ህወሓት የዱላ ቅብብል ሩጫው ላይ ተግቶል፡፡ ወርቁን ለማግኘት የቡድን ስራውን ተግቶ እየሰራ ነው፡፡ መለስ ዜናዊ የጥቅለላውን ዱላ አሁን አለሁ አለሁ ለሚለው ቡድን አስረክበው ከመሮጫ ትራኩ ወጥተዋል፡፡ ዱላ ሰቅለዋል፡፡ የትግራዩ ቡድን በኤርትራም በጎንደርም ልምምዳቸውን ያደርጉ የነበሩ ሮጮችን ምንም አይነት የዱላ ቅብብል ሩጫ ውድድር ፊሽካ ሳይነፋ ለልምምድ በተሰጠውና በያዘው ዱላ እየሰነዘረ፤ እየፈነከተ ሮጮችን ከልምምድ ብሎም ከውድድር ውጭ እያስወጣ ከዚህ ደርሶል፡፡ የዱላ ቅብብል ሩጫ ቡድኑ በጥብቅ ማዕከላዊነት ስለሚመራ ዱላውን የያዘ ሮጭ ሸምጥጥ ከተባለ ይሸመጥጣል ፤ ምናልባትም ተቀናቃኝ ሮጭ ከተገኘ በቻለው አቅም እርምጃ እንዲወስድ መመሪያ ይሰጠዋል፡፡ የዱላ ቅብብል ሩጫው ቡድን የመሠረተው ከሌላ ቡድን ከድቶ ከመጣ በኀላ ነው፡፡ ወያኔ/ህወሓት ሻብያ ከተባለው ቡድን ጋር በአንድ ቡድንም በመታቀፋም በተናጠልም ተወዳድረዋል፡፡ ነገር ግን ውድድሩ ደርቢ ሲሆንበት ነው የተነጠለው ፡፡ ባስበው ባስበው ደከመኝ እንዳለው ገበሬው ፤ ደርቢው ይቅርብኝና ብቻየን ነው የምሮጠው ፤ የምን አሮሮጭ ነው ብሎ ዱላው ተቀብሎ ተቀየሰ፡፡ አሁን ይኸን ዱላው ይዞ አስሩጦቸው የሚሮጡለት ደርቢ ሳይሆኑ መደበሪያ የሆኑ የቡድን አባለት ሲያፈላልግ ነው ይኸ ጉደኛ ቡድን ያደራጀው፡፡ የዱላ ቅብብል ሩጫው ተጀምሮል፤ ወያኔ/ህወሓት ዱላውን ይዞ እየተንሳቀሰ ነው ፤ብዙም አይሮጥም ዋናው እቅዱ ማሮሮጥ ይመስላል፡፡ ሩጥ ስትለው የሚሮጥ ተኛ ስትለው የሚተኛ እያለ፡፡ አቀበለው፤ ለብአዴን ሰጠው ፤ብአዴን አቤት ሩጫ ሲችል ፤ እንዲያውም በመጨረሻ እንደተገመገመው ለቡድኑ ወርቅ ማግኘት ከፍተኛ አስተዋፆ አርጎል፡፡ ብአዴን ለኦህዴድ አቀበለ፡፡ኦህዴድ ተቀብሎ ሽምጥ እየጋለበ ነው፡፡ ከመሮጫ ትራኩ ላይ የተገኙትን ተወዳዳሪዎች አንዴ በግል መወዳደር አይቻልም እያለ እያወናበደ ሌላ ጊዜ በያዘው ዱላ እየቀጠቀጠ ያስወጣል፡፡ የዱላ ቅብብሉ ሩጫ ከኦህዴድ ወደ ሶዴፓ ሲሄድ ፍሰቱን አሌጠበቀም፡፡ በዚህ መዘናጋት ኦህዴድ በያዘው በያዘው ዱለ አንድ ጊዜ ሶዴፓን ነርቶ ዱላውን ያቀብለዋል ፡፡ ሮጩ ሶዴፓም የዱላ ቅብብሉ ስለገባው ዱላውን ተቀብሎ አፈተለከ እግረመንገዱን በያዘው ዱላ ሞራል አልሰጡኝም የሚለውን ያገኘውን ተመልካች እየጨረገደ ይሄዳል፡፡ የዱላ ቅብብሉ ሩጫ በህገ-አራዊት ስለሚመራ እንሮጣለን ብለው ሩጫ የጀመሩ የሌሎች ቡድን ሮጮች ዱላቸው አስረክበው ከውድድር ትራኩ ወጥተዋል፡፡ ሶዴፓ ዱላውን ይዟ የመጨረሻ ዙሩን አክርሮ እየሮጠ የወርቅ ዋንጫውን ለማንሳት ቆምጦል፡፡ የዱላ ቅብብል ህጉ በህገ-አራዊት የሚመራ በመሆኑ ሁሉም የዱላ ቅብብል ሩጫ የቡድኑ አባላት እኩል ናቸው ነገር ግን አንዳንዶቹ ደግሞ የበለጠ እኩል ናቸው የሚል ህግ ስላለው የወርቅ ዋንጫው በክቡር ትሪቡኑ ቀርቦ የተቀበለው እና ከፍ አርጎ ወደ ደጋፊዎችና ተመልካች እየደነፋ ያነሳው ወያኔ/ህወሓት የተባለው ዱለኛ ሮጭ ነው፡፡ ከክቡር ትሪቡኑ ላይ ሆኖ ዋንጫውን ከፍ ሲያደርግ በስታዲየሙ የተሰበሰበው ህዝብ በአንድ ድምፅ ነጎድጎዳማ የማጉረምረም ድምፅ ሲያወጣ ዋንጫውን የያዘው ዱለኛ ሮጭ የጨው ሰማዕታት ሀውልት ሆኖ ቀረ፡፡ ይኸው ከዚያ ወዲህ የሰማዕታት ሀውልት እናቆማለን፡፡
አብራሃም ለቤዛ