Followers

Thursday, September 7, 2017

ሁሉም መብቶች ለሁሉም!!!


ሁሉም መብቶች ለሁሉም!!!
----------------//---------------
ዘር ፤ቀለም ፤ሃይማኖት በሰብዓዊነትን ተተክቶ
ሕይወት ክቡር ሁና ደህንነቶ ፀንቶ
ብዝበዛ፤ ጭቆና ፤ ሽኩቻ ከአገር ተወግዶ
አገር ሰላም ሁና ፍትህ እኩልነት ሁሉን ተዋህዶ
በእምየ ኢትዮጵያ መቼ ነው የማየው?
ዴሞክራሲ ሰፍኖ ህግ የበላይ ሁኖ
በሰላማዊ ትግል ስልጣን ከህዝብ መጥቶ
ገደብ ተቀምጦ ተጠያቂነት ጎልቶ
ፍርድ ነፃ ሁኖ ጣልቃ ገብነት ቀርቶ
በእምየ ኢትዮጵያ መቼ ነው የማየው?
ሃይማኖት ፤ ባህል፤ቋንቋ ሆነው ጌጦቻችን
አንዱ አንዱን ሳይኮንን ሳይሆኑ ሳንካችን
ሰብዓዊነትን ሰብከው እውቀትን አስፋፍተው
ፍቅርን አጎልብተው ሰላምን አፍርተው
በእምየ ኢትዮጵያ መቼ ነው የማየው?
ዛሬ ሌላው ዓለም ተራቆ  ዲሞክራሲ ጎልብቶ
ሰላም ደህንነቱን ለህግ አደራ ሰጥቶ
ህግ የበላይ ሁኖ ፍትህ አስገኝቶ
ሰርተው ይኖራሉ አደራቸው ወጥቶ
በኢትዮጵያ ምድር በአፍሪካችን አህጉር
የዴሞክራሲ እጦት የፍትህ ባይተዎርነት
ልማትም ህልም ሁኖል ደህነትም ቅዠት
ረሃብ፤በሽታ፤ ድንቁርና፤ ጦርነት ሆነውናል ሕይወት
ይህ ሁል ተወግዶ ሰብዓዊነት ለምልሞ
በእምየ አፍሪካ  መቼ ነው የማየው?

አብራሃም ለቤዛ ህዳር 21/ 19 99 ዓ/ም

No comments:

Post a Comment