Followers

Friday, August 11, 2017

ግብር ለምን ዓላማ?



በኢትዮጵያችን ገቢ ለልማት ከቴሌቪዢን ፕሮግራም ባለፈ በኢትዮጵያ ለልማት ይውላል ወይ ነው ቁልፋ ጥያቄ፡፡ በብድር ፤ በእርዳታ ፤ ኢትዮጵያዊያን ለቤተሰቧቻቸው ከስደት አገር የሚልኩት ገንዘብ እንዲሁም መንግስት የሚሰበስበው ግብር (የአገር ውስጥ ገቢ) የገቢ ምንጮች ናቸው፡፡ ገቢ ለልማት ብንልም ቅሉ ገቢው ልማት ላይ መዋል አለመዋሉን መቋጣጠር የሚችል የማህበረሰብ ተሳትፎ መፍጠር አልቻልንም፡፡ እኔ አውቅልሀለሁ የሚል ገዢ ፓርቲ ያልሁህን አምጣ የማለት የሞራልም የህግም መብት የለውም፡፡ አሳታፊ እና ተጠያቂነት ባለበት ስርዓት ግን ዜጓች ግብር መክፈል የውዴታ ግዴታቸው ነው፡፡ የሚወዶትን አገራቸው ማልማት፡፡ ቃልና ተግባር ለየቅል ሆነ እንጂ፡፡ ግብር አስፈፃሚው አካል ሙሠኛ ከሆነ እንዴት ግብር ከፋዩ ሀገርህን ስለምትወድ ብለን እናሳምነው? የተጣለብኝ ግብ ፍትሀዊ አይደለም ሲል የይግባኝ ስርዓት ከሌለን ወይንም ሁሉንም ነጋዴ በእኩል አይን የምናይበት ፍትሀዊ አሰራር ግብር ሰብሳቢው አካል ላይ ከሌለ እንዴት ግብር መሠብሠብ ይቻላል፡፡ ኢትዮጵያ የግብር ተደራሽነት ከሌሎች አፍሪካ አገሮች አንፃር ሰፊ መሠረት እንደሌለው መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ለዚህም ነው በየአመቱ የሚታወጀው በጀት 50% በላይ በብድርና ዕርዳታ ይሸፈናል እየተባለ ቃል የሚገባው፡፡ ነገር ግን በዕርዳታ የሚመጣውም ገንዘብ ሆነ ብዙ ዳፋ ለትውልድ እያስተላለፍንለት ያለው ብድር በሙስና ይባክናል፡፡ የኦዲት ባለሙያዎች ምስጋና ይግባቸውና በሪፖርታቸው ከቅርብ ዓመታት ወዲህ እየገለፁት ነው፡፡ የግብር መሠረት ለማስፋት አሳታፊና ፍትሀዊ ስርዓት ያስፈልገናል፡፡ በግብር የተማረረው ዜጋም እንደዚህ ነው ብሷቱን በስነ-ቃል እየገለፀ የመጣነው፡፡
******ዓፄ ቴዎድሮስ ጎጃ ዘምተው ሕዝቡን በዘረፉበት ጊዜ ጉዳት የደረሰባት አንዲት ሴት እንዲህ ብላ አለቀሰች፡፡
ልብሴንም ገፈፈው፤ ለበሰው እርዘኛ፤
በሬየንም ነዳው አረደው ነፍጠኛ፤
እህሌን ዘረፈው በላው ቀለብተኛ፤
ንጉሥ የቀረዎ ጥቂት አማርኛ፣
 ምነው ሆድ አይዘርፉ አርፌ እንድተኛ፡፡

*****
ራስ ኃይሉ በዘመኑ የጎጃምን ሕዝብ (የኔ ቢጤ ደሀን ለማኙን ሳይቀር) “ግብር ክፈልእያለ በአስጨነቀበት ወቅት ሕዝቡ እንዲህ ብሎ ስሜቱን ገለጠ፡፡
ጎመኑን ቀርድጄ ጥሬውን በላሁት፣
 እንዳላበስለውም የጭሱን ፈራሁት፡፡
ራስ ኃይሉ ጭስ የሚጨስባትን እያንዳንዷን ጎጆ እያስቆጠሩ፣ ግብር ያስከፍሉ ስለነበር በጎጃም ሚስት ያገቡ ወጣቶች ጎጆ አይወጡም ነበር፤ ትልቁ ቤት እየተዘረጠጠ በታዛ ውስጥ ይኖሩ እንደነበር አባቶቻችን ይናገራሉ፡፡
አሁንስ እንዲህ ብለን ብንቃኝ አይቻል ይሆን?

ገቢ ለልማት መሆኑን አውቃለሁ፤
ኢትዮጵያ አገሬንም በጣም እወዳለሁ፤
የቄሳርን ለቄሳር ቅዱስ ቃሉ ይላል፤
ኮረጆ ገልብጠህ ድምጤ የሰረቅከኝ በብር ማን ያምንካል፡፡ 

Thursday, August 3, 2017

ቀይ ባህር የኢትዮጵያ ወይስ የማንም መራኮቻ?

ኢትዮጵያ የባህር በር ባለቤት በነበረችበት ጊዜ በቀይ ባህር ላይ ያላትን ቁጥጥር  አለም አቀፍ ተቀባይነት የጎላ ነበር፡፡ ኢትዮጵያ ጂኦፖለቲካል አቀማመጦ ምክንያት እና ምስጋና ለነገሰስታቶቾ ታሪካዊ የባህር በር ባለቤት  አድርገዎት ቢያልፉም ይኸ ትውለድ ግን ማስቀጠል አልቻለም፡፡ 
ዛሬ የአትዮጵያ ህዝብ ከ100 ሚሊዮን በላይ ሲሆን ይህም በዓለም ብቸኛ በህዝብ ቁጥር አንደኛ ሁና የባህር በር የሌላት አገር ያደርጋታል፡፡ በአፍሪካ ኢትጵያን ጨምሮ 15 አገሮች የባህር በር የሌላቸው ሲሆን ነገር ግን 14ቱ የአፍሪካ አገሮች የህዝብ ብዛታቸው ከ20 ሚሊዮን በታች ነው፡፡
ይህን ማስታዎሻ እንድፅፍ ያስገደደኝ በቅርቡ ከአሰብ ወደብ ተነሳ በተባለ ንብረትነቱ በየመን ሁቱ ሚሊሻዎች ላይ ዘመቻ የከፈተው ጥምር ጦር የሆነ መርከብ  በሁቱ ሚሊሻዎች አደጋ ተጣለበት የሚለው ዜና ነው፡፡
የቀይ ባህር አካባቢ የቄሳርን ለቄሳር እንዲሉ ታሪካዊት እና ቀደመት የሆነችው ኢትዮጵያ በበላይነት መምራት ሲገባትና ለዓለም አገራት ምሳሌነቶን ማሳየት ሲገባት ዛሬ ከእጃችን አፈትልኮ የወጣበት ምክንት ታሪካዊ ውርደት መሆኑን መጠቆም እወዳለሁ፡፡

ኤርትራ ሲያሻት ለኢራን (ሺአ ተከታይ)፤ ሲያሻት ለሳዉድ አረቢያ (ሱኒ ተከታይ) እያከራየች እርጥባን ብታገኝበትም ተጨማሪ ግን አካባቢዉን የስጋት ቀጠና ሁኖል፡፡  የእኛ ደካማ መሪዎችም  ግን ኤርትራ ብትፈልግ ግመሎን ውሃ ታጠጣዉ ብለው ቢያጣጥሉትም ለኢትዮጵያዊያን ግን አጥጋቢ መልስ አይደልም፡፡ 

ግመሎ እያለችው ከቀየው ከቀይ ባህር አፋር(አፈር)፤
ላሟን ካልጫንኩ አለ ተሻግሮ በብድር፡፡

ላሙ (ኬንያ)፤ በርበራ(ሰማሊያ)፤ሱዳን ፖርት (ሱዳን) አሉን እያሉ ከማላዘን ግመሎ ያለችበትን ቀይ ባህር ጠበቅ ማድረግ አማራጭ የለውም፡፡ቀይ ባህር ተፈጥሮዊ የአፋር (አፈር) ህዝብ ሀብት እንደሆነ ይኸም በአለም አቀፍ ህግ ተቀባየይነት እንዳለው(Law of intimacy) የምዳስስበት ፅሑፍ ይኖራል፡፡ ሱልጣን አሊ ሚራህ ሰለአፋር ኢትዮጵያዊነት ሲያስረግጡ ግመሉ ሳትቀር የኢትዮጵያን ሰንደቅ ዓላማ ትለያለች ነበር ያሉት፡፡ 
የአፍርን ህዝብ ለሁለት የከፈሉት የእኛ መሪዎች (ጎረምሷች እንደ ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም አገላለፅ) በሰንደቅ ዓላማችን እንደቀለዱ ወደ ግብዓተ መሬት ወረዱ፡፡ ስለ ቀይ ባህር የእኛነት ዳጉ ካደረግሁ በኃላ እመጣለሁ፡፡
አንድ ቀን ግን ኢትዮጵያ ዳግማ በቀይ ባህር አካባቢ ታንሰራራለች፡፡ ኢትዮጵያ በክብር ለዘላለም ትኑር!!! አብራሃም ለቤዛ


Monday, January 23, 2017

አምባገነኖች ባሉበት የአገርም ክብር ከፍ አይልም፡፡


በአሃጉራችን አፍሪካ በሚጥጥየዎ ጋምቢያ ምርጫ በተደረገ ማግስት 22 ዓመት የገዙት መሪ ያህያ ጃሜህ ሽንፈታቸውን መቀበላቸው አጀብ አሰኝቶ ነበር፡፡ በዚህ አምባገነን መሪ የተገረሙትም አድናቆታቸውን ችረዎቸው ነበር፡፡ የጃሜህ ቃል ግን ቀናትን አልፎ ሳምንታት መቆየት አልቻለም ምርጫው ተጭበርብሮል ይጣራልኝ ብለው አረፉት፡፡
ምንም እንኳን የምርጫው ሂደት ከጅምሩ ነፃ እና ገለልተኛ አይደለም የአምባገነኑ መሪ ረጅም እጅ አለበት እየተባለ ቢብጠለጠልም፤ በተጨማሪም የኢኮዎስም ሆነ የአውሮፓ ህብረት የታዛቢዎች ቡድን ለመታዘብ ባይችሉም የጋምቢያ ተፎካካሪዎች ግን ልዩነታቸውን ወደ ጎን በማድረግ ከመቼዉም ጊዜ በላይ ተጠናክረው ነበር ያህያ ጃሜህን የተፋለሙት፡፡
በድጋፍ ህዝባዊ ሰልፍ ቲያትራቸውን ለዓለም መንግስታት የሚተዉኑት ያያህ ጃሜህ በወሳኞ የምርጫ ቀን ይህ በድጋፍ ሲያስፈነድቃቸው የነበረ ህዝብ አይቀጡ ቅጣት ቀጣቸውና ድምጹን ከዝቅተኛ አመራር የመጣ የተቀናቃኝ ፖለቲካ ዕጩው አዳማ ባሮው ሰጠ፡፡
ያህያ ጃሜህ በአፍሪካ እየተወገዱ እነዳሉት አብዛኞቹ ፕሬዜዳንቶች በመፈንቅለ መንግስተ የመጡ ሲሆን የእሳቸውም መጨረሻ ውርደትን ተከናንበው መሰናበት ሁኖል፡፡ እስቲ ያሳያችሁ 22 ዓመት በላይ ስንት ዓመት ሊገዛ ነው?
አምባገነኖች ባሉበት የአገርም ክብር ከፍ አይልምና፤ አዲሱ ተመራጭ ፕሬዘዳንትም ቃለ መሃላ የፈፀመው በአገሪቱ ስታዲየም በጦሩ አጀብ በማርሻል ባንድ ታጅቦ ሳይሆን በስደት በሴኔጋል በሚገኘው የጋምቢያ ኤምባሲ ነው፡፡ በአንጻሩ የልዕለ ሃያሎ አሜሪካ የስልጣን ሽግግር በሰላማዊ መንገድ 250 ዓመታት በላይ መዝለቁ በቅናት ልብን ያበግናል፡፡ መንፈሳዊ ቅናት፡፡
አዳማ ባሮው ለአገራቸው መልካም ምኞት እንዳላቸው በበዓለ ሲመታቸው ላይ ተናግረዎል፡፡ የሃብት ክፍፍል ፍትሃዊ እንደሚሆን፤ ስልጣናቸውም ገደብ እንደሚኖረው፡፡ እንደ ቃልዎ ብያለሁ፡፡ የአፍሪካ መሪዎች ቃላቸውን አይጠብቁም ያያህ ጃሜህ በመፈንቅለ መንግስት ወደ ስልጣን ለተገደበ ሰልጣን ዘመን እንደሚቆይ ቃል ገብቶ ነበር ፡፡

በአፍሪካችን ሰላማዊ የስልጣን ሽግግር ምሳሌ የሚሆኑ አገሮች አሉ፡፡ ጋና፤ ቦትሰዎና፤ደቡብ አፍሪካ፤ ዛምብያ በምሳሌነት ይጠቀሳሉ በአንፃሩ ደግሞ በአብዛኞቹ የአፍሪካ አገሮች የስልጣን ሽግግሩ መቆራቆስ  እንደሆነ ቀጥሎል፡፡ ለዜጎች መፈናቀል ምክንያት ነው፡፡ መቼ ነው አፍሪካ ከዚህ አዙሪት የምትወጣዉ?