Followers

Saturday, May 7, 2016

ማክበር ለራስ ነው



እንዳለመታደል ቀደምቶቻችን የሰሩትን መናድ ይቀለናል፡፡ ባለው ላይ መጨመር ወደከፍታ መገንባት አይሆንልንም፡፡ለዛሬ ማተት የወደድኩት የሚያዚያ 30 የነፃነት በዓላችን ላይ ነው፡፡ ደርግ የንጉሳዊውን መንግስት በመፈንቅል ስልጣን ሲቆጣጠር ሚያዚያ 30 ይከበር የነበረውን የነፃነት በዓል ወደ መጋቢት 28 ለወጠው ፡፡ የዚህ መከራከሪያ ደግሞ ንጉስ ሃይለ ስላሴ ከስደት ከመለሳቸው በፊት የኢትዮጵያ አርበኞች ቀደም ብለው መጋቢት 28 /1933 ዓ/ም የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በማውለብለብ የኢዮጵያን ነፃነት አውጀው ስለነበረ ነው፡፡

አርቲስት ተስፋዪ ገብሬ

“መጋቢት 28 የድላችን ቀን

ይከበር ዘላለም በሃገራችን

መጋቢት 28 በየዓመቱ ይምጣ

የእናንተም መሳሪያ ጦር ጋሻችሁ ይዉጣ”

(youtube link: https://www.youtube.com/watch?v=iS4tyWI6YDA) እያለ ለነጻነት ቀናችን አዚሞለታል፡፡

ብሶት የወለደው ሕወሓት/ኢህአዴግ ደርግን በጦርነት ሲያሸንፍ ጋቢት 28 የሚከበረውን የነፃነት በዓል በንጉሱ ጊዜ ይከበርበት ወደነበረበት ቀን መልሶታል፡፡ ገዢዎቻችን በዓላትን ቀናት ሲቀያይሩ ህዝብን እያማከሩ ፤ ታሪክን እያገናዘቡ ይሆን ወይስ እንዴው ያለፈውን የመለወጥ እና የማጥፋት አባዜ፡፡

ደርግ ሰፊዉን የኢትዮጵያ አርሶአደር ከርዕሰትና ጉልት ፊውዳላዊ አስተዳደር ያወጣበትን ስርዓት እንደመሰረተ በኩራት ይናገራል፡፡ በርግጥም ትልቁ የኢትዮጵያ አቢዮት ነበር፡፡ መስከረም 2/1967 ዓ/ም በየዓመቱም ይከበር ነበር፡፡

“መስከረም ሁለት አበራ ችቦ ችቦ

ኮሚኒስታችን በአንድ አሰባስቦብ ሰብስቦን “እያላን እናዜምለት የነበረው ክብረ በዓል፡ የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት አክብረን ተጨማሪ ፌሽታ እናደርግ ነበር፡፡

ብሶት የወለደው የህወሓት/ኢህአዴግ ሰራዊት ደርግን አስወገዶ የብሄር በሄረሰቦች ህዝቦች ነጻነት የተረጋገጠበትን ቀን በማለት ግንቦት 2ዐ በየዓመቱ እያከበርነ እንገኛለን፡፡  ግንቦት 20 ይዞት የመጣው ደግሞ  የመስከረም 2 ዓመታዊ በዓልን አስወግዶ የግንቦት 20 ፍሬወች በሚል አርዕሰት በየዓመቱ በሚዘጋጁ ዶክመንታሪ እና መዝሙሮች ላይ ባለተራ እየተወነ ይገኛል፡፡



መቼ ነው እኛ ኢትዮጵዊያን በብሄራዊ በዓሎቻችንን የጋራ መግባባት የምንደርሰው፡፡ አንዱ የአንዱን የሚፍቅ ከሆነ አንዳችንም ምንም አሻራ እንዳይኖረን እያደረግን መሆናችን ይገባናል፡፡

መስከረም 2 የደለዘ ንቦት 20 ስላለመደለዙ ምን ማረጋገጫ  አለው፡፡


No comments:

Post a Comment