ብሄር ማለት አገር ማለት ነው፤
ብሄረሰብ ደግሞ የአገር አባላት ፡፡ ልክ ቤት ብለን ቤተሰብ እንደማለት፡፡ ታዲያ ይኸ በኢትዮጵኛ እንጂ በአልባኒያኛ አይደለም፡፡
የአልባንያው ደብተራ በዚህ አይስማማም፡፡
ብሄራዊ ቡድን፤ ብሄራዊ ባንክ፤
ብሄራዊ ሎተሪ፤ ብሄራዊ ትያትር፤ ብሄራዊ ሊግ፤ ብሄራዊ በዓል፤ ብሄራዊ የሃዘን ቀን፤ ብሄራዊ መዝሙር፤ብሄራዊ ጂን ሳይቀር ኢትዮጵያዊያንን
ማዕከል አድርገው የተቋቋሙ ተቋሞቻችን እና እሴቶቻችን ናቸው፡፡ እነዚህ ተቋሞቻችን እና እሴቶቻችን
ታዲያ አንድ አካል አንድ አምሳል ሁነው ነው የኢትዮጵያችን (የአገራችን)
ሊሆኑ የሚችሉት፡፡ ከአንድ በላይ ሊኖሩ አይችሉም፡፡ ብሄር ከፍ ያለ የዳበረ ማንነት ያለው ፤ ብሄረሰብ ደግሞ አነስ ያለ ወደ ብሄር
ደረጃ በመንደርደር ላይ ያለ ማንነት የሚለው አልባኒያዊ ትርጎሜ ፉርሽ ነው፡፡
ከዛሬ 22 ዓመት ወዲህ በኢትዮጵዊያን
መታወቂያ ብሄር የሚል ጥያቄ ይቀርባል ፡፡ በርግጥ በ19 87 ዓ/ም በወጣው ህገ-መንግስት ኢትዮጵያ የብሄር ፣ብሄረሰቦች ህዝቦች
ሉዓላዊ ግዛት ነች ይላል፡፡ በጣም አደገኛ የሆነው የህገ-መንግስቱ ግልባጭ ወደ ክልሎች ሲወርድ ክልላችን የእንቶ ፈንቶ ፤ ቡራ
ከረዩ እና ስልቻ ቀልቀሎ ቀልቀሎ ስልቻ ብሄረሰቦች ሉዓላዊ ግዛት
ብቻ ነው ሲል ነው፡፡ ኢትዮጵያዊ ብሄርተኝነት አሁኑኑ አትሉም፡፡ የጎሳ ማንነታችንን ኢትዮጵያ (ብሄር-አገር) በሚለው እየተካን
በቋንቋ ላይ ደባ እየፈጸምን እንገኛለን፡፡ ብሄር አገር ነው ካልን ዘንዳ ዜግነት ከሚለው ጋር ይስተካከልል፡፡
United Nations የሚለው
የተባበሩት አገሮች የሚል አቻ ትርጉም ይኖረዋል፡፡ ቢያንስ ዓለም ሉዓላዊነታቸውን ያወቀላቸው አገሮች ትብብር ነው፡፡ ወደ እኛ ሰንመጣ
ይኸው በአልባንያኛ ኢትዮጵያ የምትባል አገር የብዙ ብሄሮች ስምምነት (ትብብር) ውጤት ዕንጂ አንድ አገር አይደለችም ነው፡፡ አንድ
አገር ፤አንድ ህዝብ ፤ አንድ ሰንደቅ ዓላማ አትሉም፡፡
ይኸን ሃሳብ የቋንቋ ባለሙያዎች
የበለጠ ልታዳብሩት ትችላለችሁ፡፡ ለውይይት ክፍት ነው፡፡
No comments:
Post a Comment