Followers

Friday, October 20, 2017

ፀጉራም ዉሻ አለ ሲሉት ይሞታል፡፡ አብራሃም ለቤዛ


እንደ ኢቢሲ አገላለፅ ኢትዮጵያ የአረንጎዴ ኢኮኖሚ ፖሊሲን በመተግበር ከዓለም አገራት ልዩ ያደርጋታል፡፡ የት አለ ውጤቱ፡፡ ኸረ ጎበዝ አረንጎዴ ልማት ምን ማለት ነው፡፡ እስቲ የራሳችሁን ትርጉም አካፍሉኝ፡፡ ጣና ሃያ ሺ (20000) ሄክታር በእንቦጭ ተሸፈነ ሲባል ይኸ አረንጎዴ ልማት ፖሊሲ ምን ምን ዝርዝር ተግባርት አከናወነ?  ነው ወይስ አረሙን አረንጎዴ ነው ብለችሁ አለፋችሁት፡፡ ምን አሁን እኳ በዚች አገር ፖለሲ አውጭ እና ሚኒስቴር ለመሆን ልማታዊ ካድሬ ሆኖል መስፈርቱ፡፡ እዚች ላይ የተጠቅላዩን ሚኒስተር እስፖርት ተኳር ምክር ተግባራዊ ብትሆን እንዴት ጥሩ ነበር፡፡ ምን አሉ መሰላችሁ “ ብስክሌት ፌዴሽንን ለመምራት ብስክሌት አሽከርክሮ የሚያዉቅ እንዲሁም ዋና ፌዴሬሽንን ለመምራት ዋና የሚችል መሆን አለበት፡፡” መልዕክቱ  መች ከፋ ተግባር ዜሮ ሆነ፡፡
ጣና ተንተርሶ የተቋቋመው ጣና ፎረም (በቅርቡ ደግሞ ወደ ጣና ፋዉንዴሽን አድጎል) ተቋም በ2009 ሚያዚያ ወር ላይ እንኳን የመከረው «የተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር በአፍሪቃ» በሚል መሪ ርዕስ ላይ ነው፡፡  ቋይ ቋይ  ጣና አናቱ ላይ ስለ ተፈጥሮ ሀብት አስተዳደር የመከረው ጉባዔ ስለ ጣና አደጋ ላይ መውደቅ ምን አለ፡፡ አይኔን ግንባር ያርገው፡፡ ፁራም ውሻ አለ ሲሉት ይሞታል፡፡ ባህር ዳር የጣና ፈርጥ በሚል እየተሞካሸች ነው  ፤ ይኸ ስም ጣናን እስክንታደግ ቢቀመጥ ደስተኛ ነኝ፡፡ ደራሲዉም በባህርዳር የደሃ ምግብ አሳ ሲሆን አዲስ አበባ ደግሞ የደሃ ምግብ ሃሳብ ነው ብሎ ቢከትብልሽም ባህርዳር ግን ስምሽም ሊከዳሽ ከዳር ደርሰሻል፡፡ የብስ ዳር፡፡ አዋ የብስ ዳር ፡፡ኢትዮጵያዊያን ጣና እንደ ሃሮምያ ሃይቅ አይናችን ላይ ሳይጠፋ እጅ ለእጅ ተያይዘን አረሙንና አራሙቻውን ልንነቅልለት ፤ ልንደርስለት ይገባል፡፡ (ሃሮምያ ሃይቅ ከታሪካዊዎ ሃረር ከተማ መዳራሻ ሃሮምየ ከተማ የነበረ ሃይቅ ነው፡፡ )  ሃሮምየያም ታሪክ ሆነ፡፡ ለታሪክ የጎለተን፡፡
ማሪታይም አካዳሚ መርከበኛችን ባህርዳር ዩኝቨርስቲ ስር ተጠልሎ መርከበኞችን በማሰልጠል ላይ ይገኛል፡፡  ትናንት መርከበኞችን በራሶ ባህር ላይ አሰልጥና በራሶ ባህር ላይ ልጆቾን እንዲቀዝፉ ታደርግ የነበረች አገር ከቅርብ ጊዜ ወዲህ ጣናን ተንተርሳ የውጭ ምንዛሬ ለማግኘት መርከበኞችን እያሰለጠነች ትገኛለች፡፡  የውጭ ምንዛሬ መቼም ዘንድሮ ያላስገባን ቦታ የለም፡፡ ከአረብ አገራት ጋር የቤት ሰራተኛ ለመላክ ከመደራደር እስከ የአህያ ቄራ መክፈት፡፡ ለመሆኑ በባህር ዳር ዩኒቨርስቲ ስር ያለው ማሪታይም አካዳሚ ጣናን ለመታደግ ምን እየሰራ ነው፡፡  ጣና ከሌለ ያው ማሪ ታይሙም የለም፡፡
ኢትዮጵያን በፀጉራም ውሻ መስያታለሁ፡፡ ጨለምተኛ ነህ ልትሉኝ ትችላላችሁ፡፡ ለኔ አልታየኝም፡፡ እስቲ ሃሳባችሁን ጀባ በሉ፡፡

No comments:

Post a Comment