Followers

Tuesday, August 9, 2016

ከስርዓት በአድሎዊነት የሚጠቀሙ አድርባዮች እንጂ ህዝብ አይደለም፡፡



የኢትዮጵያን የጦርነት ታሪክ  ወደ ኋላ ስንመረመር የእርስ በእርስ ጦርነቶችን ጨምሮ በወራሪዎች የተሰነዘሩብን ጭምር ተደምረው በሰሜኑ የአገራችን ክፍል ላይ ያሳረፉት ጫና ቀላል አይደለም፡፡ ራስ አሉላ አባ ነጋ አንዴ ከግብጽ አንዴ ከጣሊያን ወራሪ ሃይል ጋር የኢትዮጵያን የቀይባህር ድንበር በአልሞት ባይ ተጋዳይነት እየታገሉ እስተ እርጅና እድሜአቸው ድረስ ታግልዎል፡፡ በአድዎ ጦርነት ጊዜ የአውዳሚ መሳሪያዎች ጫና ቀላል ቢሆንም ደካማ ኢኮኖሚ ላላት አገራችን በሰውና በንብረት ላይ የደርሰው ጉዳት ቀላል አይደለም፡፡ ምንም እንኳን አንዳን የትግራይ ወንድሞቻችን በባንዳነት ቢሰለፉም እዉነተኛ የትግራይ ልጆችም የተዎደቁለት ድል ነው፡፡  በማይጨው ሽንፈት በተጠናቀቀው የጣሊያን ወረራም ጊዜ ፋሺሰት ጣሊያን የመርዝ ገዝ የሚረጭ ቦምብ በኢትዮጵያዊያን ላይ ሲያዘንብ የትግራይ ህዝብም  ተጠቂ ነበር፡፡ የኢትዮጵያን ዳር ድንበር ለማስከበር እና ንጉሳዊ አስተዳደሮ እንዳይገረሰስ እና ሃይማኖት እንዳይረክስ በትግሬ አባቶቻችን የተከፈለው መስዎእትነት ግን ዛሬ በዘመናችን ከትግራይ በመጡ ገዣዎቻችን ተዛብቶ እየተተረጎመ ነው፡፡
አጼ ሚኒሊክ  የሳህለ ስስሴን ንግስና ቆጥረው አንድ ቀን በአያቶቻቸው ዙፋን እንደሚቀመጡ እያሰቡ ቀደም ብሎ ላልቶ የነበረውንና ፤ንጉስ ሳህለስላሴ ያጠነናከሩትን ግዛት የበለጠ እያስፋፉ ንግስናቸው ይጠባበቁ ነበር፡፡ በኋላም የሸዎው ንጉስ የሚለው በአጼ ዮሃንሰ ፀደቀላቸው ፡፡ ኢትዮጵያዊያን መሳፍንት የአገኙትን የሃይል ሚዛን ተጠቅመው ፤ በአብዛኛው ጊዜም ከውጭ ሃይል የሚደረግን ድጋፍ ተገን አድርገው ተቀናቀኞቻቸዉን በማስወገድ የነገሱበት የታሪክ ሂደት አለ፡፡ አፄ ዮሃንስ የእንግሊዘን ጦር መቅደላ በመምራት በአጼ ቴዎድሮስ ሞት እና በመቅደላ በተዘረፉ ቅርሶች ዋጋ በታጠቀዉ መሳሪ  ዋግ ሹም ጎበዜን (እራሳቸውን አጼ ተክለጊዮርጊስ ብለው አንግሰው ነበር) ድለ በማድረግ መንገስ ችለዋል፡፡ ዋግ ሹም ጎበዜ በጊዜው ያላቸውን የሰራዊት ብዛት ለመግለጽ እና አናሳ ሰራዊት ያለው ደጃች ካሳ ምርጫ ጦርነት እንዳሞክር ለማስፈራራት በቁና ሙሉ ጤፍ  አስይዘው ለመልክተኛቸው ቢልኩም ደጃች ካሳ ምርጫ  ቁና ሙሉ ጤፉን አስፈጭተው መልሰው ላኩላቸው፡፡ ዋግ ሹም ጎበዜ ማስፈራራት ቢሞክሩም በምላሹ ግን ሰረዊትህ ቢበዛ እንደ ጤፉ እቆላዎለሁ የሚል መልስ መጣላቸው፡፡ ይህን ታሪክ ተክለፃዲቅ መኩሪያ የኢትዮያ ታሪክ ከአጼ ቴዎደሮስ እስከ አጼ ሃይለስላሴ በሚለው መጽሃፋቸው መዝግበውታል፡፡
ደጃች ካሳ  በኋላ አጼ ዮሃንስ አጼ ተክለጊዮርጊስን፤ የእህታቸውን ባል ድል አርገው ይዘው በወረንጦ አይናቸውን ያወጦቸው በዘመኑ የነበረውን ጭካኔ መገለጫ እንጂ በሙሉ በዎግ ህዝብ ላይ የተካሄደ የዘር ማጥፋት ሊሆን አይችልም፡፡ አፄ ሚኒሊክ ከአድዎ ድል ማግስት በባንዳነት ተሰማርተው የነበሩት የትግራይ ተወላጆች ላይ እርምጃ ወስደዎል፡፡ ምንም እንኳን የአፄ ሚኒሊክ ቸርነተት በአደባባይ የሚታዎቅ እና በታሪክ ደርሳናትም የተመዘገበ ቢሆንም ፤ ንጉሱ በተሰየሙበት የአደባባይ ወታደራዊ ፍርድ ቤት የትግራይ ባንዶች እጃቸው እንዲቋረጥ ተደርጓል፡፡ የአፄ ሚኒሊክ ዘመን በወታደራዊ ፍርድ ቤት የተወሰደ እርምጃ በመላው የትግራይ ህዝብ ላይ የተወሰደ አድርጓ መውሰድ አንድም በጊዜው የነበረውን ዘመን አለመረዳት ወይም የባንድነትን ታሪክ ለመሸፈን የሚደረግ ሙከራ ነው፡፡

ወታደራዊ ደርግ በተማሪዎች ትግል እና በሰራተኛ ማህበራት አመፃ ኣና ውክቢያ ይላጋ ከነበረውን ንጉሳዊ መንግስተ ስልጣን በመመንተፍ ወደ ስልጣን ሲመጣ፤ በተማሪዎች ትግል ውስጥ አብረው ይሳተፉ የነበሩት ከፊል የትግራይ ልጆች ኢትዮጵያ ብሄርተኝነትን በማቀንቀን ከኢትዮጵያ ወንድሞቻቸው ጋር አንድ በመሆን የጋራ ትግል ለማካሄድ ቃል በመግባት ሕዝባዊ መንግስት ለመመስረት ብዙ ደክመዎል፡፡ ዓለም አቀፍ የፖለቲካ ቁማር ፤ ቀዝቃዛው ጦርነት እና እርስ በርሰ የመጠላለፍ ፖለቲካ ኢህአፓንና እና መኢሶንን የመሰሉ ኢትጵያዊ ድርጅቶችን ከመስመር አስወጥቶ ሕወሃት ለተባለ ጠባብ ዘረኛ ቡድን መንገድ ጠርጎለታል፡፡
ተኃሕት ቆይቶም ሕወሃት የተባለው ፤ ማገብት፤ ሻብያ እና ጀብሃ በሚባሉት ድርጅቶች ጥላ ስር የተሰበሰቡት የሰሜን ኢትዮጵያ ልጆች የሄዱበት መንገድ ግን ከመጀሪያዉ የኢትዮጵያን መሰረት የናደ ነበር፡፡ ለረዥም ዘመን ሉዓላዊነቶን ጠብቃ ፤ እንደ ሃገር በንጉሶቾ በማእከላዊ አስተዳደር እየተመራች የቋየችን ሃገር ታሪክ ወደጎን በማደረግ የኢትየጵያ ታሪክ የ100 ዓመት ታሪክ ነው ፤ ህዳሴዎ ዛሬ እራሱን ኢህአዴግ ብሎ የሚጠራው እንዳበሰረላት ገዢው ቡድን ይናገራል፡፡
በተለያዩ ሃገራት ታሪክ የህዝቦች የጭቋና ታሪክ የባርነት ፍንገላን ጨምሮ የታሪካችን አካል ቢሆንም ፤ የኢትዮጵያን ህዝብ ያለፈ ታሪክ እስረኛ እንድንሆን ከጥዎት ጀምረው በዘር ላይ የተመሰረተ ፖሊሳቸውን እየተገበሩ ይገኛሉ፡፡ ለኢትዮጵያ ህዝብ ነጻነት የሚደክም ማንኛዉም ግለሰብ እንደሚረዳው በገዢዎቸ ጭቋና ምክንያት ታፍነው የነበሩ ሰብዓዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብቶች ዛሬ ባለንበት በ21 ኛው ክፍለ ዘመን በዲሞክራሲ መንግስት ምስረታ ፤ የግለሰቦችን ነፃነት የሚያከብር እና የህዝብን እኩልነት የሚገነዘብ መንግስት ሲኖር መልስ የሚያገኙ እንጂ አንድ ጠባብ ቡድን የሚያሽከረክራቸውን የየአካባቢውን ቋንቋ ተናጋሪ ልሂቃን ብቻ ወንበር ላይ በማስቀመጥ በማስቀመጥ በፌዴራሊዝም በመቀለድ (ፌዝራሊዝም በመመስረት) የሚሆን ነገር አይደለም፡፡
ወያኔ ለ25 ዓመታት ያለፉት ስርዓት በትግራይ ህዝብ ላይ የጭቋና ቀንበር ዘርግተው ነበር ሲል፤ አማርኛ ቋንቋ ተናጋሪ የነበረው ስርዓት የአማራ ህዝብ ወኪል አድርጎ ያቀርባል፡፡ ይህንንም ስብከቱን በየክልሎቹ ባቋቃማቸው ወኪሎቹ አማካኝነት ባለፉት የጭቋና ስርዓት እኩል ተጎጂ በነበረው የአማራ ህዝብ ላይ ጥፋት እንዲታወጅበት አድርጓል፡፡ የአማራ አርሶ አደር እና ጭቁን ማህበረሰብ ጉልበቱ እስኪዝል እና ላቡን አንጠፍጥፎ በኢትዮዮጵያዊነት ከሚኖርበት ቀየ እንዲፈናቀል እየተደረገ ይገኛል፡፡ ቡንዝልፎ
ወያኔ የተባለው ትግርኛ ተናጋሪ ገዢ መደብ ግን እራሱን ብቸኛ የትግራይ ህዝብ ወኪል አድርጎ በማቅረብ የትግራይ ገበሬ ለእኩይ አላማው በማሰለፍ፡ በደረግ ግፋዊ አመራር የተማረረን የአማራ ህዝብ የእርካብ መወጣጫ አድርገገጓ ለስልጣን በቅቶል፡፡ ወያኔ ደርግን በማሸነፍ እና 25 ዓመት እኩይ አላማውን እንዲያስፈፅም የተከፋፈሉት ኢትዮጵያዊያን ምቹ ሁኔታ የፈፈጠረለትን አጋጣሚ ወያኔ በመታበይ የህዝብ ድጋፍ ያለው አስመሰለው፡፡ የኦሮሞን ህዝብ ከአማራው ጋር ለማጋጨት እና የኢትዮጵያ ህዝብ አንጡራ ሃብት እየዘረፈ በመቶ አመት በስልጣን ለመቆየት እና ለመፈንጨት የቆመጠው የዘረኛው ወያኔ ቡድን የወያኔ ተላላኪና ቡችላዎችን እንደነ አባዱላ ፤ ሙክታር  ከኦሮሚያ በማስቀደም ከአማራዉም ድንበር የሚሸጠው ደመቀ፤ ካሳ ተክለብርሃን የመሳሰሉትን በማሰለፍ የቆመጠለት አላማ መክሸፍ አለበት፡፡የወያኔ አኖሌ የማን ውጤት እንደሆነ ታሪክ በቅርቡ ፍረርድ ይሰጣል፡፡ በህዘባዊ የተቃዉሞ እንቅስቃሴዎች  የፈሰሰው የወንድሞቻችን ደም በቅርቡ  የወያኔዎች መጨረሻ እንደጋዳፊ ስለሚሆን ፈሶ አይቀርም፡፡ ኦሮሞ እና አማራ ወንድማማች እና አንድ ህዝብ እንጂ  የወያኔ 25 ዓመት የደገሰላቸው እርስ በእርስ እልቂት ተቀልብሶ አሁን የደረሱበት የትብብር መንፈስ መቀጠል አለበት፡፡

ወያኔ በአንድ በኩል አገሪቱን ተቋጣጥሮ ኢኮኖሚዉን እንዳሻው እየመዘበረ በሌላ በኩል ደግሞ የትግራይ ሪፐፕሊክን የወደፊት ግዛት ማስፋፋት አቅድ እየተገበረ ይገኛል፡፡ የወልቃይት ጠገዴን እና ራያ እና አዘቦን ግዛት በጠመንጃ ወደራሱ ግዛት ካደረገ በኋላ ተከዜ ማዶ ያለ ግዛቱን ለማስፋፋት ተጨማሪ ወረዳዎችን በቅርብ ጊዜ በህዝባዊ ሪፈረንደም ለመጠቅለል እየቃዠ ያለ ገዢ መደብ ነው፡፡ የወልቃት የማንነት ጥያቄ ለ25 ዓመታት መስዎዕትነት የተከፈለበት ቢሆንም በአሁኑ ሰዓት ሁነኛ ምዕራፍ ላይ ደርሶል፡፡
ወያኔ ኢትዮጵያዊ አስተሳሰብ ስለሌለው በትግራይ ድርቅ ማግስት የደርግ መንግስተ በድርቅ የተጓዱ የትግራይ ገበሬን  ወደ ሌላ የኢትዮጵያ ግዛት ሲያሰፈር  በወቅቱ አማፂው የወያኔ ቡድን የትግራይን ህዝብ ከቀየው ተፈናቀለ ቢልም በድርቅ ለተጓዱት የተላከለትን እርዳታ ግን እታገለለታለሁ ለሚለው ህዝብ አንድም ሳያሸት መሳሪያ ታጥቋበታል፡፡ የጭቁን ገበሬዎች  ጥያቄን አንግቦ የተነሳው ወያኔ ዛሬም ከገባሬው ጋር እንደተቃቃረ ይገኛል፡፡

በትግራይ ህዝብ ስም እየማለ በተግባር ግን የትግራይን ህዝብ እንደህዝብ ከሚጎራበታቸው ወንድም ህዝብ ጋር ለማቃቃር እየሰራ ያለው ወያኔ/የትግራይ ነፃ አውጭ ቡድን ነው፡፡ ጦር ሰራዊቱን ፤ የሃገር ደህንነት መስሪየ ቤቱን፤ ቢሮክራሲዉን እና ኢንቨስትመንቱን አንድ አናሳ ቁጥር ካለው የኢትዮጵየያ ህዝብ አካል ከሆነው ከትግራይ የመጡ ፤ ክህሎቱ እና እዉቀቱ የሌላቸው እንደተቋጠጠሩት የአደባባይ ሀቅ ነው፡፡ ይህን ሀቅ የትግራይ ምሁራንም ሆነ ወጣትም በዝምታ ማለፋቸው ምን ይሆን፡፡
የትግራይ ምሁራን እና ወጣቶች ዛሬ ትግሬ እንደ አንድ ታታሪ ህዝብ በላቡ እና በጥረቱ የተሻለ ደረጃ ሊደርስ እና የተሸለ ህይወት ሊኖር የሚችለው በኢትዮጵያ አገራችን በእኩልነት ላይ የተመሰረተ ዲሞክራሲያዊ ስርዓት መገንባት ስንችል ነው፡፡ ይህ ስርዓት እውን ሲሆን ነው የትግራይ ህዝብ እውነተኛ ልጆች የሚፈጠሩት ፤ ትግሬም እንደ ህዝብ በኢትዮጵያ ውስጥ ያለው ታሪክ በሌሎች ወገኖቹ የሚወደሰው፡፡  የትግራይ ነፃ አውጭ የቀድሞውን የደርግ መንግስት ስለ ወጋ እና ስላጣን ስለያዘ የትግራይ ህዝብ ብቻ መስዎዕትነት የከፈለ የሚመስላቸው የዎሆች፡ አለፍ ሲልም የትግራይ ህዝብ ብቻ ጀግና የሚመስላቸው የወያኔ ጠባብ ፖለቲካ ሰላባ የሆኑ የትግራይ ወጣቶች ማወቅ ያለባቸው  ሰው ሁሉ እኩል ነው የሚለው ሃቅ ብቻ ነው፡፡ በአሁኑ ሰዓት ኢትዮጵያዊያን እያካሄዱት ያሉት ህዝባዊ አመፃ የጋራ ቤታችንን ኢትዮጵያ ሁላችንንም በእኩልነት እንድታስተናግደን ያለመ፤ የኢትዮጵያ አንጡራ ሃብት ከስግብግብነት ወጥተን የጋራ ማድረግ ከቻል በቂ ነው፡፡ ህዝባዊi አመፃዉን የትግራይ ወንድሞቻችን እንዲደግፉት እና ደፍረው እንዲወጡ ጥሪየን አቀርባለሁ፡፡ኢትዮጵያ በመስዎዕት ልጆቾ በክብር ለዘላለም ትኖራለች፡፡

Saturday, May 14, 2016

የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ ፤ አሰራት ወልደየስ

የታንዛኒያዉ የነፃነት ታጋይ ፖለቲከኛ እና መምህር (ሙዎሊሙ) ጁሊየስ ኔሬሬ በአንድ ወቅት “I am a schoolmaster by choice and a politician by accident “እንዴት ከሚወደውና ከሚያከብረው ሙያው ተገፍቶ ወደ ፖለቲካ ትግሉ እንደገባ በመግለፅ እንደተናገር ድርሳናት ይጠቅሳሉ፡፡ በነገራችን ላይ ጁሊየስ ኔሬሬ ከአለማችን የትምህርት ፈላስፋዎች ውስጥ ይመደባሉ፡፡

ከላይ ያለዉን ታሪክ ያነሳሁት የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ የሆኑት ፐሮፈፌሰር አሰራት ወልየስ  ታሪክ  ከእዉቅ የቀዶ ጥገና ሃኪምነት ዘው አድርጎ  ወደ ፖለቲካዉ እንዲገቡ እንዴት እንዳስገደዳቸው  ለመተረክ ነው፡፡
አገራችን ኢትዮጵያ በግንቦት 1983 ዓ/ም ማግስት በብሄርተኛ ሃይሎች ተወጥራ ለ3000 ዓመት የገነባችዉ አጋራዊ ድር እየተበጣጠሰ ፤ ዜጎች በሚናገሩት ቋንቋ እየተመዘኑ ከቀያቸው ሲፈናቀሉ፣ ሲታረዱ ፣ ወደ ገደል ሲጣሉ ፤ አንጋፋዉ የህክምና ሊቅ ደራሽ  ያልነበራቸውን ወገኖቻችንን ሰቆቃ ስላንገበገባቸው የህክምና ጋወላቸውን አዉልቀዉ የአባቶቻቸውን ጋሻ እና ጎራዴ አንስተው ተነሱ፡፡ የትግል አጋሮቻቸውን በማሰባሰብ በወገኖቻችን ላይ የሚደርሰውን እልቂት ለመታደግ ብርቱ ጥረት አድርገዎል፡፡
አስራት እሩህሩህነትንና ደግነትን ከጥልቅ የሙያ አውቀት ጋር የቀሰሙ ሲሆን፤ በሙያቸው ብዙ ሜዳሊያዎችን ከተለያዩ ተቋሞች ተሸልመዎል፡፡ (You can refer the link: Professor Asrat Woldeyes Biography)
አስራት ገና በስምንት ዓመታቸው ወላጅ አባታቸውን በፋሽስት አረመኔያዊ ጭፍጨፋ የተነጠቁት አስራት ፤ የኢትዮጵያ ባህላዊ ትምህርትም የቀሰሙት ከአለቃ ለማ ሃይሉ የኔታነት ነው፤ ድሬደዎ፡፡
ፐሮፌሰር አስራት ያደራጁት መ.አ.ህ.ድ. (መላዉ አምሃራ ህዝብ ድርጅት) አማራን የማዳን አላማ እንግቦ ጠናካራ መሰረት እየያዘ ሲሄድ ፤ ወያኔ/ኢህአዴግ ሰላማዊ ታገዎች ዛሬም ወደ እስር እያጓረ እንደሚገኘዉ አስራትም የእስር ሰለባ ሆነ፡፡ ከዚያማ ፍርድ ቤት ምናምን፡፡
ስንቶችን ከአልጋ ቁራኛነት ከደዌ ዳኛ እናዳልታደገ ፤ የኢትዮጵያን ህክምን ኮሌጅ (ጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ) እንዳላደራጀ፤ እስረኛው አስራት የእስረኛ አየያዝ ዓለም አቀፍ ህግ ተጥሶ ህክምና እንዳያገኝ ተከለከለ፡፡
ፐሮፌሰር አስራት በእንደዚህ ሁኔታ ነው ግንቦት 6, 1991 ዓ/ም ለህልፈተ ህይወት የተዳረገው፡፡ አስራት ህያው ነህ፡፡ ለተጨቆኑት፤ ለታረዱትና ወደ ገደል ለተወረወሩት ጩኸኻል አልፎም መስዎት ሁነሃልና ሁሌም ህያዉ ነህ፡፡ አንተ ለእኛ ሁሌም ህያው ነህ፤ ትውልዶች ያልፋሉ ነገር ግን ያንተን ፈለግ ተከትለው የሚከተሉህ እልፍ አላፍ ናቸዉና ሁሌም ህያው ነህ፡፡
የፕሮፌሰር አስራት ወልደየስን 17 ሙት ዓመት ስንዘክር ፤ የአስራትን ትክክለኛ አላማ ከግብ ለማድረስ ሁላችንም ለእራሳችች ቃል እንግባ፡፡ ጭቆና፤ አድሎዊነትንና ኢፍታህዊነት በኢትዮጵያ አስወግደን የረዥም አመት ታሪክ ባለቤት የሆነች አጋረችንን ለማየት ያብቃን፡፡ አሜን፡፡


Saturday, May 7, 2016

ማክበር ለራስ ነው



እንዳለመታደል ቀደምቶቻችን የሰሩትን መናድ ይቀለናል፡፡ ባለው ላይ መጨመር ወደከፍታ መገንባት አይሆንልንም፡፡ለዛሬ ማተት የወደድኩት የሚያዚያ 30 የነፃነት በዓላችን ላይ ነው፡፡ ደርግ የንጉሳዊውን መንግስት በመፈንቅል ስልጣን ሲቆጣጠር ሚያዚያ 30 ይከበር የነበረውን የነፃነት በዓል ወደ መጋቢት 28 ለወጠው ፡፡ የዚህ መከራከሪያ ደግሞ ንጉስ ሃይለ ስላሴ ከስደት ከመለሳቸው በፊት የኢትዮጵያ አርበኞች ቀደም ብለው መጋቢት 28 /1933 ዓ/ም የኢትዮጵያን ሰንደቅ አላማ በማውለብለብ የኢዮጵያን ነፃነት አውጀው ስለነበረ ነው፡፡

አርቲስት ተስፋዪ ገብሬ

“መጋቢት 28 የድላችን ቀን

ይከበር ዘላለም በሃገራችን

መጋቢት 28 በየዓመቱ ይምጣ

የእናንተም መሳሪያ ጦር ጋሻችሁ ይዉጣ”

(youtube link: https://www.youtube.com/watch?v=iS4tyWI6YDA) እያለ ለነጻነት ቀናችን አዚሞለታል፡፡

ብሶት የወለደው ሕወሓት/ኢህአዴግ ደርግን በጦርነት ሲያሸንፍ ጋቢት 28 የሚከበረውን የነፃነት በዓል በንጉሱ ጊዜ ይከበርበት ወደነበረበት ቀን መልሶታል፡፡ ገዢዎቻችን በዓላትን ቀናት ሲቀያይሩ ህዝብን እያማከሩ ፤ ታሪክን እያገናዘቡ ይሆን ወይስ እንዴው ያለፈውን የመለወጥ እና የማጥፋት አባዜ፡፡

ደርግ ሰፊዉን የኢትዮጵያ አርሶአደር ከርዕሰትና ጉልት ፊውዳላዊ አስተዳደር ያወጣበትን ስርዓት እንደመሰረተ በኩራት ይናገራል፡፡ በርግጥም ትልቁ የኢትዮጵያ አቢዮት ነበር፡፡ መስከረም 2/1967 ዓ/ም በየዓመቱም ይከበር ነበር፡፡

“መስከረም ሁለት አበራ ችቦ ችቦ

ኮሚኒስታችን በአንድ አሰባስቦብ ሰብስቦን “እያላን እናዜምለት የነበረው ክብረ በዓል፡ የኢትዮጵያን አዲስ ዓመት አክብረን ተጨማሪ ፌሽታ እናደርግ ነበር፡፡

ብሶት የወለደው የህወሓት/ኢህአዴግ ሰራዊት ደርግን አስወገዶ የብሄር በሄረሰቦች ህዝቦች ነጻነት የተረጋገጠበትን ቀን በማለት ግንቦት 2ዐ በየዓመቱ እያከበርነ እንገኛለን፡፡  ግንቦት 20 ይዞት የመጣው ደግሞ  የመስከረም 2 ዓመታዊ በዓልን አስወግዶ የግንቦት 20 ፍሬወች በሚል አርዕሰት በየዓመቱ በሚዘጋጁ ዶክመንታሪ እና መዝሙሮች ላይ ባለተራ እየተወነ ይገኛል፡፡



መቼ ነው እኛ ኢትዮጵዊያን በብሄራዊ በዓሎቻችንን የጋራ መግባባት የምንደርሰው፡፡ አንዱ የአንዱን የሚፍቅ ከሆነ አንዳችንም ምንም አሻራ እንዳይኖረን እያደረግን መሆናችን ይገባናል፡፡

መስከረም 2 የደለዘ ንቦት 20 ስላለመደለዙ ምን ማረጋገጫ  አለው፡፡